1. ብልፅግና/ ኦፒዲኦ /TPLF/OLF ቦለቲካ በአያሌው ስንጠየፍ ስንጠላ በግል ስቃወም መሽ ነጋ:: ክረምት ገባ::ክረምት ወጣ:: እግዚኦ! ሲረገሙ የሚፈለፈሉትና የሚበዙት ነገር ምን ይባላል!!
2. ስለ ኮሪደር በመስማት ኮሪዶር በኮሪደር ሆንላችሁ:: ኮሪደሩ ኮሪደር ብቻ አይደለም የወለደው:: ኮሪደር በልተው ኮሪደረ የሚያገሱ ስለኮሪደሩ የሚፀልዩ ስለኮሪደር የሚያመስግኑ ፖስተሮችም ምእመናን የኮሪደር ከንቲባ የኮሪደር ጠሚ የኮሪደር ሌባ የኮሪደር ፈንድ የኮሪደር ካድሬ ሁሉ ወለደ:: የኮሪዶር ኦሎምፒክ ቢኖር በኮሪደር እናሽንፍ ነበር:: የኮሪደር ቫይረስም መረጃ ፎረምን ወሮታል:: የኮሪደር ልማት ከመደመር ቅምር አልበለጠም? የኮሪደር ትዳር የኮሪደር ጉዋደኝነት የኮሪደር መብራት የኮሪደር ዎክ የኮሪደር ፎንቃ የኮሪዶር ገበያ ....የመደመር ዲግሪ ...የመደመር ትዳር... አይ በሻሻ ስው ቀርቶ ጉሬዛ የቡና ችግኝ አይብቀልብሽ! ስንቱን ጂንየስ ያልነው አዋቂ ደመርሽው ከመርሽውና ኮርደር ልማት ከተትሽው...ምላሳም ዜናዊ ደግሞ በውሃ ማቆርና በብሄር ብሄርስቦችና ክልል ለክፎን ሄደ! ውሃ ማቆር ተባለ:: ውሃ ስናቁር ስናቁር ስናቁር ሞስኪቶ ወለደ ሞስኪቶ ወባ ወለደ:: ወባ ብዙዎችን ወስደ:: ገደለ:: መለስንም አደገኛና ያልተለመደ የጭንቅላት ወባ ገደለው! የኮሪደርና የመደመሩ ከንቲባስ በምን ይሆን የሚጠራው?
ኮሪደሩ ጎዳና ተዳዳሪዎችንስ የኮሪደር ማደርያ ስጥቶ ይሆን?
3. የሜሞራንደምዋስ ነገር ደስ አትልም? ያለቀለት የስምምነት አይነት ውል አይመስልም? ከሚስት/ከፍቅረኛ ጋር MoU, ከጉዋደኛ ጋር MoU ለ ኒው ይር MoU…..ከዚያ ሶሻል ሜድያ ላይ መለጠፍ! ከዚያማ ጠላቶችህን ትጠብሳለህ ታበስላለህ...አብይ አህመድ ያረገው ይህን አይደለም? የMoU ሬድዮ ጣብያ የ MoU ቴሌቭዥን ...የMoU. ካድሬ የ MoU ዳያስፖራ...የ MoU cyber warrior ወለደ:: ልብ በሉ ባልተፈፀመ MoU የሻውያ ካድሬዎች ሲብስከስኩ ...ሶማሌማንbot, wordpad ሲያለቅስ አብሲንያ ሌዲ ጉራጌ ቦይፍሬንዷን ዳማን ሊስትሮ ስትል ለስሙዋሌ ስትዋጋ ኤርትራ ግብፅ ስትመላለስ ሶማሊያ ቱርክ ስትመላለስ አብይ ኬንያ ሲጋበዝ ጉልቻ ተፈጠረ ምጣድ ተጣደ እንደ አሻሮ አነደዱን.. ሲሳይ ጌኛ እንቅልፍ አጣ ብርሃኑ ነጋም በአብይ ስም እንደገብርኤል ስዕለት ጀመረ:: አይ MoU ነብስህ አይማር ነብስ ካለህ:: አድዋና በሻሻ እንዲህ ከአንኳር እሳቤ ያወጣችሁን ደረጃችን ያወረዳችሁት ምድረ በዳ ሁኑ ሳርና ስው አይብቀልባችሁ !!
4. እኛ መደመርም መከመርም ኮሪደርም ውሃ ማቆርም ሆነ የብሄር ብሄር ስዎች ጉዳይ ሳይጥመን ሳያገኘን ኢትዮዽያዊነታችን እንደጠበቅነ አለነ! እናንተስ? ያልደመረን በብሄር ብሄረስብ ያላዋረደን አንቀፅ 39 ያላስወደደን ውሃ ያላሳቆረን ኮሪደር ልማት ሳይከተን ከጎርፍ የጠበቀን አምላክ ይመስገን!!
5. እንድህ ውለታ የስራን አምላክ ከሻውያ ከካውያ ከወያኔ ከብልግና ከብልጥግና....የጠበቀን ከcyber warrior አማራ ፅንፈኞችም ይጠብቀናል!!