ያሸነፈ ቢረሳ የተሸነፈ ኣይረሳም ተብሎ ይሆን?
ኣስተዉዬ ለማሰላሰል ስሞክር ከአደዋ ማግስት ጀምሮ አደዋን ለመቀልበስ ወይም ለማጨናገፍ ሴራ ነበረ። ይህ የማሰላሰል ግምት ነዉ። ኣልነበረም ባይ ካለ ለማዳመጥ ጆሮዎቼ ዝግጁ ናቸዉ።
የዚህ ዐይነት ሴራ ኣራማጅን በትለር እለዋለሁ።
ኣሁን እጅግ የሚደንቀኝ ከአደዋ ግዜ ጀምሮ የኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንዴት በኣንድ አፍ ዉስጣዊ የፖለትካ ጥያቄዎች ቢኖሩንም አድዋ የማይነካ የኢትዮጵያ፣ የኣፍሪካ፣ እና የሰዉ ልጅ ነፃነት ቅዱስ ገድል ነዉ ማለት እንዳልቻሉ ነዉ።
ገተተ ማለት ግዜዉ ሳይደርስ የወጣ ወይም የወደቀ ሕይወት ኣልባ የከብት ፅንስ ማለት ነዉ።
ስለዚህ ሴራዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያልዘለቀ ከሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ ገተተ ሆኖ ተከሰተ ማለት ነዉ። እንዲህ ዐይነት ሴራ ከተገኘ ኣርቆ ይጣላል።