እኔ ሆረስ ቃላት አልፈልጥም።
(1) የወያኔና ኦሮሙማ አምባ ገነኖች ያሻቸውን ሕግ እያወጡ የሕዝብ ሃብትና ንብረት ይቀማሉ ፤ እነሱ መውረስ ይሉታል! ይህ ያ ሌባ መንግስቱ ኃ/ማሪያም የጀመረው ነው ። ዛሬም ቢሆን አቢይና ቡድኑ በራሳቸው ሕግ ሽፋን ያሻቸውን የነጋዴና የንጹህ ሕዝብ ንብረት ሊዘርፉ ተነስተዋል ።
(2) ላለፉት 32 አመት በተቋም ደረጃ፣ በተደራጀ መልክ ከላይ እስከ ታች ስልጣናና ሕግ ተገን በማድረግ አንዲት ቀን ሳይሰራ፣ አንዲት ቀን ጋዜጣ ሳያዞር ባለሚሊዮን እና ባለ ቢሊዮን የሆነው መንግስታዊ ሌባ ሁሉ አንድ ባንድ ተፈትሾ ንብረቱና ባንኩን መቀማት አለበት ። ግን ልብ በሉ ወደፊት የሚሆነው አዲሱ ሌባ ከድሮው ሌባ መቀማት ነው ። ከመንግስታዊ ሌቦች የተቀማው የሕዝብ ሃብት ለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለም።
(3) የ32 አመቱ የሌንበትና ዉሸት ኢኮኖሚ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፣ የማይሰሩ፣ የማይተጉ፣ የማያመርቱ፣ ለማህበረሰብ ቅንጣ ዋጋ የማይፈጥሩ አየር ባየር፣ በጉቦ፣ በቅጥፈት፣ ብሽርሙጥና አለያም በቀጥታ እገታና ራንሰም ባለሚሊዮን ባለ ቢሊዮን የሆኑ ሕዝባዊ ሌቦችና አጭበርባሪዎች ያከማቹት ሃብትና ንብረት ሁሉ መቀማት መወረሱ ትልቅ ትምህርት ነው ። ችግሩ ይህም ከሕዝባዊ ሌቦች የተቀማው ወደ መንግስታዊ ሌቦች ኪስ ነው የሚዞረው ።
(4) በኢትዮጵያ የእቃ ዋጋ ከሕዝቡ ደሞዝና ገቢ በሺና እልፍ እጥፍ ያደረገውና ኪሎ ሽንኩርት 200 ብር ያናረው የዲያስፖራ ዶላር ፣ ሕገወጥ ጥቁር ገበያ ስለሆነ በጥቁር ገበያ የተያዘ ሃብት ሁሉ ከህጋዊ ተመን በላይ ያተረፈውን ሁሉ መቀማት ያስፈልጋል ። የኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ጠላት የዲያስፖራ ጥቁር ገበያ ስለሆነ ።
(5) በአንድ ቃል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሁን ካለው የዋጋ ንረት በግማሽ መውረድ አለበት ።
(6) የማይሰሩ ፣ የማያመርቱ፣ የማይፈጥሩ ሰዎች ባለሃብት የሚሆኑበት የሌቦችና ዉሸታሞች ኢኮኖሚ መዘጋት ፣መቆለፍ አለበት ።
(7) በሌላ በኩል መንግስት ነን የሚሉት የተደራጁ ሌቦች ከቦሌ እስከ ጉለሌ የዘረጉት የዘረፋ ኔትወርክም እንዲሁ መዘጋት መቆለፍ አለበት! የነሱ ቤትና ባንክም መወረስ አለበት ።
(8) ግን ያ አይሆንም!
Re: አዲሱ ሕግ ፡ በሌብነትና ውሸት ላይ የተገነባው ኢኮኖሚ መፍረስ ጀመረ!
ያገር ኢኮኖሚ የሚገነቡ የሚሰሩ የሚፈጥሩ ሕዝብ እንጂ ሌቦች ፣ ቀማኞችና ዉሽታም ፈዳላዎች አይደሉም ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ መሰረቱ መመለስ አለበት !