በርግጥ በነ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ አገዛዝ የ ሰው ልጅ ህይወት ዋጋ ያጣ መሆኑ እርግጥ ቢሆንም፣ በ ሶስት ሳምንት በድል አድራጊነት ወደ ቤቱ ይመለሳል የተባለው የ ኦሮሚያ ልዪ ሃይል በ አማራ ሸንተረሮች ተደፍቶ በመቅረቱ፣ እየፈጠረ ያለው ድንጋጤ፣ ክልሉ ላይ እያሳደረ ያለው ድባብ አገዛዙን እየነቀነቀው ነው፣፣
በዚህ ሁሉ ሰቆቃ ውስጥ ታዲያ አፋኝና አጋች ቡድን አሰማርቶ ከተራ ዜጋ እስከ ባለ ሀብት እያሳገተ በሚሊዮኖች የሚዘርፈው አኦቦ አራርሳ፣ በ ትንሽ ደመወዙ ያሰራት ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል፣ ቦሌ ላይ ለ ሁለት ቀን መንገድ ተዘግቶ ድል ባለ የ ባለጊዜ ድግስ ተመርቋል፣፣ ኮሬ ነጌኛነት ታላቅ እና አትራፊ የግድያ ኢንዱስትሪ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፣፣