ሆረስ! ምዕራባዊያ ፋኖ እና ኦሮሙማ ኦነግን ለማስታረቅ ተፍተፍ እያሉ ነው ይባላል። ፋኖ ከዚህ የድፍት-ወጥመድ ቢርቅስ? ምዕራባዊያን 100% ፋኖን አይፈልጉም፤ ፋኖን ደገፉ ማለት የጎሳ ክልል ይፈርስባቸዋል::
የፋኖ መሰረታዊ ጥያቄ የወያኔ እና ኦነግ የጎሳ ክልል እና ህገ-መንግስት ይለወጥ፤ የውሸት ፓርላማ እና ተወካዮች ምክርቤት በህግ ይታገድ፤ ዘር አጥፊ ወንጀለኞች ለህግ ይቅረቡ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ይህን የማይጠይቅ ደግሞ ፋኖ ሊሆን አይችልም። ይህ ጥያቄ ከባድ ሳይሆን ለኦሮሙማ ኦነግ እና ወያኔ የማይመች ነው። ምዕራባዊያንም ቢሆኑ ከወጥኑ ኦነግ፤ ወያኔ እና ሻዕብያ ምን ጊዜም ቢሆን የሚፈልጓቸው ናቸው። አንድኛው ሲዳከም ሌላውን ይደግፋሉ፤ የተደገፈው ሲዳከም ሌላውን ያነቃቃሉ እንጅ ፋኖን ወደፊት ለማምጣት ሳይሆን ባለበት ለማቆም ወይም ለመበተን የታቀደ ይመስለኛል።እንደት ታየዋለህ? የፋኖ አደረጃጀት ደግሞ ለጥላት አስቸጋሪ ሁኖባቸዋል። እጅግ እረቂቅ የሆነ አደረጃጀት ነው ፋኖ እየተከተለ ያለው።
Re: ሆረስ! ምዕራባዊያ ፋኖ እና ኦሮሙማ ኦነግን ለማስታረቅ ተፍተፍ እያሉ ነው ይባላል። ፋኖ ከዚህ የድፍት-ወጥመድ ቢርቅስ? 100% ፋኖን አይፈልጉም፤ፋኖን ደገፉ ማለት የጎሳ ክልል ይፈርስ
አበረ፣Abere wrote: ↑24 Jan 2024, 20:24ሆረስ! ምዕራባዊያ ፋኖ እና ኦሮሙማ ኦነግን ለማስታረቅ ተፍተፍ እያሉ ነው ይባላል። ፋኖ ከዚህ የድፍት-ወጥመድ ቢርቅስ? ምዕራባዊያን 100% ፋኖን አይፈልጉም፤ ፋኖን ደገፉ ማለት የጎሳ ክልል ይፈርስባቸዋል::
የፋኖ መሰረታዊ ጥያቄ የወያኔ እና ኦነግ የጎሳ ክልል እና ህገ-መንግስት ይለወጥ፤ የውሸት ፓርላማ እና ተወካዮች ምክርቤት በህግ ይታገድ፤ ዘር አጥፊ ወንጀለኞች ለህግ ይቅረቡ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ይህን የማይጠይቅ ደግሞ ፋኖ ሊሆን አይችልም። ይህ ጥያቄ ከባድ ሳይሆን ለኦሮሙማ ኦነግ እና ወያኔ የማይመች ነው። ምዕራባዊያንም ቢሆኑ ከወጥኑ ኦነግ፤ ወያኔ እና ሻዕብያ ምን ጊዜም ቢሆን የሚፈልጓቸው ናቸው። አንድኛው ሲዳከም ሌላውን ይደግፋሉ፤ የተደገፈው ሲዳከም ሌላውን ያነቃቃሉ እንጅ ፋኖን ወደፊት ለማምጣት ሳይሆን ባለበት ለማቆም ወይም ለመበተን የታቀደ ይመስለኛል።እንደት ታየዋለህ? የፋኖ አደረጃጀት ደግሞ ለጥላት አስቸጋሪ ሁኖባቸዋል። እጅግ እረቂቅ የሆነ አደረጃጀት ነው ፋኖ እየተከተለ ያለው።
አሜሪካኖችን ታቃቸዋለህ፤ አፍሪካ ውስጥ ችግር ካለ ሁልግዜ የበላይና ያገባኛል በሚል ከች ይላሉ ። ትክክል ነህ፣ አሜሪካ የፋኖ ደጋፊ አይደለም። አሜሪካ ጸረ አማራ የሆነው ገና በኃይለ ስላሴ ዘመን ነው። እርግጥ ለትህነግ ስስ ልብ ነው ያላቸው ።
ታዲያ ለምንድን ነው ድርድር ድርድር የሚሉት ካልከኝ ፒፒ ኢትዮጵያን መምራትም ሆነ ማረጋጋት እንደ ማይችል በራሳቸው መረጃ መሰረት የወሰኑ ይመስለኛል። እናም እነሱ የሚያቀርቡት መስማሚያ ሃሳብ የሆነ power sharing arrangement ነው የሚሆነው ።
አሜሪካም ሆነ ያፍሪካ ህብረት እናደራድር ብለው ፋኖን ከጠሩት ፣ ፋኖ ሙሉ የፖለቲካ መፍትሄውን ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር የሚያቀርብበት እድል አገኘ ማለት ነው። በአለም ድረጃም አንዱ የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ኃይል መሆኑን የሚወሳበት ሁኔታ ይሆናል ።
እናም ፋኖ ምን ያድርግ? ነው ጥያቄው ።
የጦርነት ሁሉ መደምደሚያው ፖለቲካ ነው ። ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደ ታጫወትነው ፋኖ ለአማራ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ፖልቲካ ችግር መፍትሄ ነው የሚለውን ጥያቄ (demands) የመደራደሪያ ነጥቦች አድርጎ ማቅረብ ብቻ ነው ያለበት ። ለምሳሌ ...
ቁጥር 1 የድርድር ነጥብ የሽግግር መንግስት ነው! ይህ ጥያቄ ተግባራዊ ሲሆን ብቻ ነው የሕገ መንግስት ለውጥ፣ የቅርጸ መንግስት ለውጥ፣ የክልሎች ተዋቀር ለውጥ፣ ወዘተ ሊነሱና ሊፈቱ የሚችሉት ።
ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ የሚሊታሪ እና ድርጅታዊ ኃይል ሚዛን የበላይነት መያዝ የግድ ነው። ስለሆነም ፋኖ በጦሩ ሜዳ የበላይነት አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ ፒፒ በሽግግር መንግስት ሊስማማ ይችላል ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፒፒ የሚሊታሪ በላይነት አለኝ፣ ፋኖ በጦር ኃይል አይጥለኝም ብሎ የሚያምን ከሆነ በፍጹም በሽግግር መንግስት አይስማሙም ።
የሚሆነው ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ነገሩ ሁሉ ወደ ፋይዳ ቢሱ የምክክር ኮሚሽን ይገፋና አቢይ የለመደውን ዝባዝንኬ ያቀርባል ፤ ያም ማለት ፋኖን ከኢትዮጵያ ሰራዊት ይቀላቀል፣ የቀረው ወደ ሲቪል ሕይወት መመለሻ ድጎማ ይሰጠው፣ የተወሰ መቀመጫ ፓርላማ ውስጥ ይሰጠው ተብሎ በፒፒ አሸናፊነትና የበላይነት ፋኖ እንዲፈርስ ይደረጋል ማለት ነው ። ይህ ደም በፍጹም የማይታሰብ ነው ።
ስለዚህ ፋኖ ማድረግ ያለበት ነገር ...
(1) አንድ ወጥ የፖለቲካ ክንፍ ባስቸኳይ ማቆም (የዲፕሎማሲ ክንፍም)
(2) የፋኖ ፖለቲካ ፕሮግራም ተባለ የፖለቲካ መፍትሄ ረቂቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረብ፤ ማለትም ፋኖ ነገ 4 ኪሎ ቢረከብ ምን አይነት መንግስት ይሆናል የሚለውን ብቸኛ ቁልፍ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ማወጅ አለበት ።
(3) በዚህ የፖለቲካ ረቂቅ ዙሪያ መላ ኢትዮጵያን መቀስቀስና ማስተባበር
(4) እነዚህን 3 የፖለቲካ ስራዎች በፖለቲካ ክንፉ አማካይነትና በአጋሮቹ እያሰራ ጦርነቱን ወደ ሙሉ ማጥቃት ከፍ ማድረግ ነው ያለበት ።
ያለ ወታደራዊ የበላይነት ፖለቲካውን ማሸነፍ አይቻልም! ይህን ማለት ግን ድርድር አልቀመጥም ማለት አይደለም ። የድርድር ስብሰባ ሄዶ ከላይ የላውን የሽግግር መግስት ጥያቄ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ማድረግ ነው ያለበት ። ይህ ሲሆን የመግስት መለወጥ እራሱ ያገሪቱ ቁጥር 1 አጀንዳ ይሆናል !!
Re: ሆረስ! ምዕራባዊያ ፋኖ እና ኦሮሙማ ኦነግን ለማስታረቅ ተፍተፍ እያሉ ነው ይባላል። ፋኖ ከዚህ የድፍት-ወጥመድ ቢርቅስ? 100% ፋኖን አይፈልጉም፤ፋኖን ደገፉ ማለት የጎሳ ክልል ይፈርስ
ሆረስ፤
እንደ እኔ ሽምግልናው ከእውነተኛ ልብ የመነጨ ስለማይማስለኝ ነው። አንተ እንዳልከው በእርግጥ የሽግግር መንግስት 1 ቁጥር ሊቀርብ የሚችል ጉዳይ ነው። ይህ እኮ ድህረ ፕሪቶሪያ መደረግ የነበረበት እና በወቅቱ ሊቀርብ የሚገባው ነበር። ነገር ግን የኦነግ እና ወያኔ ነባራዊነት ይፈልጉት ይመስለኛል። አሁን ከግምታቸው በላይ ሁኖ ፋኖ የእነኝህን ዘላቂነት ዶግ አመድ ስላደረገ በምን ሁኔታ ማስተካከል ይሻላል የሚል ስልት ይመስለኛል። ምክንያቱም ፋኖ በዚህ እርምጃው በጥቂት ጊዜያት ኦነግ ብልጽግናን ሙሉ በሙሉ ሊያንበረክከው ይችላል - ፋኖ የበላይነት ስለሚኖረው የሚጠይቀውን ቅድመ ሁኔታዎች ሊያገኝ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ግን ከወዲሁ በመሸንገል ፋኖን ማስጨንገፍ የሚፈለግ ይመስለኛል። እስካሁን ያልተሰማ ድምጽ ይህን ያህል ዘመን ዘግይቶ አሁን ሲሰማ ያጠራጥራል። ሌላው አብይ አህመድ አሁን የሶማሊላንድ ጉዳይ እንድያነሳ ያደርገው ፋኖ ነው። ስለጨነቀው አጀንዳ በማስቀየር ህዝብን ለመደለል። ይህ የሶማሊላንድ ትኩሳት ደግሞ ለጊዜው ምዕራባዊያን ከአልሸባብ ሁኔታ ጋር ያሳስባቸዋል - ምንም እንኳን እንደ እኔ ግምት ሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት ዘላቂ ፍላጎት ሊኖራቸው ቢችልም። ምዕራባዊያን ፋኖን ለአብይ ካቀዘቀዙለት አብይም ስለ ሶማሊላንድ ምንም ማለት አይፈልግም። ጉዳዩ በተዘዋዋሪ ፋኖን ለሶማልያ ትኩሳት ማብረጃ ለማድረግ የታሰበ ይመስለኛል እንጅ ለአማራ ህዝብ እና ለፋኖ አሁን ድንገት አስበው አይሆንም።
ለማንኛውም ፋኖ መልካም ሁኔታ ላይ ነው። 1ኛ ፋኖ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያቀፈ ነው። 2ኛ) በጦር ሃይል እና ድርጅት ከፍተኛ አካባቢያዊ ተገዳዳሪ ሁኗል
3ኛ) ፋኖ በአብይ አህመድ የሶማሊላንድ-ግብጽ ንትርክ ውስጥ አንዳችም አልተነፈሰም - ወጥመድ አልገባም
Horus wrote: ↑24 Jan 2024, 21:08አበረ፣
አሜሪካኖችን ታቃቸዋለህ፤ አፍሪካ ውስጥ ችግር ካለ ሁልግዜ የበላይና ያገባኛል በሚል ከች ይላሉ ። ትክክል ነህ፣ አሜሪካ የፋኖ ደጋፊ አይደለም። አሜሪካ ጸረ አማራ የሆነው ገና በኃይለ ስላሴ ዘመን ነው። እርግጥ ለትህነግ ስስ ልብ ነው ያላቸው ።
ታዲያ ለምንድን ነው ድርድር ድርድር የሚሉት ካልከኝ ፒፒ ኢትዮጵያን መምራትም ሆነ ማረጋጋት እንደ ማይችል በራሳቸው መረጃ መሰረት የወሰኑ ይመስለኛል። እናም እነሱ የሚያቀርቡት መስማሚያ ሃሳብ የሆነ power sharing arrangement ነው የሚሆነው ።
አሜሪካም ሆነ ያፍሪካ ህብረት እናደራድር ብለው ፋኖን ከጠሩት ፣ ፋኖ ሙሉ የፖለቲካ መፍትሄውን ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር የሚያቀርብበት እድል አገኘ ማለት ነው። በአለም ድረጃም አንዱ የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ኃይል መሆኑን የሚወሳበት ሁኔታ ይሆናል ።
እናም ፋኖ ምን ያድርግ? ነው ጥያቄው ።
የጦርነት ሁሉ መደምደሚያው ፖለቲካ ነው ። ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደ ታጫወትነው ፋኖ ለአማራ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ፖልቲካ ችግር መፍትሄ ነው የሚለውን ጥያቄ (demands) የመደራደሪያ ነጥቦች አድርጎ ማቅረብ ብቻ ነው ያለበት ። ለምሳሌ ...
ቁጥር 1 የድርድር ነጥብ የሽግግር መንግስት ነው! ይህ ጥያቄ ተግባራዊ ሲሆን ብቻ ነው የሕገ መንግስት ለውጥ፣ የቅርጸ መንግስት ለውጥ፣ የክልሎች ተዋቀር ለውጥ፣ ወዘተ ሊነሱና ሊፈቱ የሚችሉት ።
ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ የሚሊታሪ እና ድርጅታዊ ኃይል ሚዛን የበላይነት መያዝ የግድ ነው። ስለሆነም ፋኖ በጦሩ ሜዳ የበላይነት አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ ፒፒ በሽግግር መንግስት ሊስማማ ይችላል ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፒፒ የሚሊታሪ በላይነት አለኝ፣ ፋኖ በጦር ኃይል አይጥለኝም ብሎ የሚያምን ከሆነ በፍጹም በሽግግር መንግስት አይስማሙም ።
የሚሆነው ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ነገሩ ሁሉ ወደ ፋይዳ ቢሱ የምክክር ኮሚሽን ይገፋና አቢይ የለመደውን ዝባዝንኬ ያቀርባል ፤ ያም ማለት ፋኖን ከኢትዮጵያ ሰራዊት ይቀላቀል፣ የቀረው ወደ ሲቪል ሕይወት መመለሻ ድጎማ ይሰጠው፣ የተወሰ መቀመጫ ፓርላማ ውስጥ ይሰጠው ተብሎ በፒፒ አሸናፊነትና የበላይነት ፋኖ እንዲፈርስ ይደረጋል ማለት ነው ። ይህ ደም በፍጹም የማይታሰብ ነው ።
ስለዚህ ፋኖ ማድረግ ያለበት ነገር ...
(1) አንድ ወጥ የፖለቲካ ክንፍ ባስቸኳይ ማቆም (የዲፕሎማሲ ክንፍም)
(2) የፋኖ ፖለቲካ ፕሮግራም ተባለ የፖለቲካ መፍትሄ ረቂቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረብ፤ ማለትም ፋኖ ነገ 4 ኪሎ ቢረከብ ምን አይነት መንግስት ይሆናል የሚለውን ብቸኛ ቁልፍ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ማወጅ አለበት ።
(3) በዚህ የፖለቲካ ረቂቅ ዙሪያ መላ ኢትዮጵያን መቀስቀስና ማስተባበር
(4) እነዚህን 3 የፖለቲካ ስራዎች በፖለቲካ ክንፉ አማካይነትና በአጋሮቹ እያሰራ ጦርነቱን ወደ ሙሉ ማጥቃት ከፍ ማድረግ ነው ያለበት ።
ያለ ወታደራዊ የበላይነት ፖለቲካውን ማሸነፍ አይቻልም! ይህን ማለት ግን ድርድር አልቀመጥም ማለት አይደለም ። የድርድር ስብሰባ ሄዶ ከላይ የላውን የሽግግር መግስት ጥያቄ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ማድረግ ነው ያለበት ። ይህ ሲሆን የመግስት መለወጥ እራሱ ያገሪቱ ቁጥር 1 አጀንዳ ይሆናል !!
[/color][/b]
Re: ሆረስ! ምዕራባዊያ ፋኖ እና ኦሮሙማ ኦነግን ለማስታረቅ ተፍተፍ እያሉ ነው ይባላል። ፋኖ ከዚህ የድፍት-ወጥመድ ቢርቅስ? 100% ፋኖን አይፈልጉም፤ፋኖን ደገፉ ማለት የጎሳ ክልል ይፈርስ
አበረ፣
ድርድር ማለት አንድ የጦርነት አይነት ነው፤ የትግል አይነት ነው፤ የፖለቲካ አይነት ነው ። የብረት ዉጊያ በአመጽ የሚካሄድ ፖለቲካ ሲሆን ድርድር (የንግግር ዉጊያ) በቃላትና ሃሳብ የሚካሄድ ጦርነት ነው ። ሁለቱም አይነት ጦርነቶች የሚደረጉት ተለይተው ለታወቁ፣ ግልጽ ለሆኑ ምክንያታዊ ጥቅሞችና አላማዎች ነው ።
ስለሆነ የአንድ ድርድር ተካፋዮች ሁሉም የራሳቸው የሆነ አላማ፣ ግብ፣ ጥቅምና መድረሻ አላቸው ። የሚደራደሩበት ውጤት አላቸው። ስለዚህ አሜሪካ የራሱ ጥቅም ሳይኖረው የድርድሩ አካል አይሆንም ። ነገር ግን አሜሪካ ፋኖን አጥፍቶ አቢይና ሸኔን ማንገስ ይፈልጋል የሚለው ድምዳሜ በመረጃ መረጋገጥ አልበት ።
ማለትም አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለው ጥቅም ምንድን ነው? አሜሪካ ከኢትዮጵያ የሚፈልገው ምንድን ነው የሚለውን በውል ማወቅ ይገባናል። የፋኖ መሪዎች በተለይ ይህን ጥያቄ ጥርት አድረገው ማወቅ አለባቸው ። ያኔ ብቻ ነው ከስህትተ ነጻ የሆነ ትግልም ሆነ ድርድር ማድረግ የሚችሉት ።
አሜሪካ ፋኖ እንዲሸነፍ ከፈለገ ድርድር አይጠራም፤ ዝም ብሎ አቢይን ይረዳል ። እየሆነ ያለው ያ አይደለም ። በኔ እምነት አሜሪካ ኢትዮጵያን ከራሺያ፣ ቻይና፣ ቱርክና ወዘተ እንዳትጠጋ አድርጎ ብቸኛ የኢትዮጵያ ጌታና ዘዋሪ መሆን ነው የሚፈልገው ። ያን በማድረግ መላ ቀጠናውን ስለሚቆጣጠር! ስለዚህ ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመን በብዙ ጦርነቶች ታምሳ በቀጠናው ቴረሪስቶች ወዘተ እንዳንሰራፉ ለማድረግ ነው፣ ታረቁ ተስማሙ የሚለው ።
እርግጥ ይህን መሰል ድርድር ሲያዘጋጅ የአሜሪካ ወድጅና እሺ ባይ ይሆናሉ ለሚላቸው ተደራዳሪዎች ያጋድላል ። ይህ ሁልግዜ የታወቀ ሃቅ ስለሆነ ፋኖም ሆነ ሌላ ተደራዳሪ ድርድሩ ካልተመቸው ጥሎ ይወጣል ማለት ነው ።
ማንም ፋኖን ይዞ በግድ እንዲሳሳት ወይም በጨዋታው እንዲሸነፍ ማድረግ አይችልም፤ እራሱ የፋኖ መሪ ካልሆነ በተቀር ። ከላይ እንዳልኩት የፋኖ ተደራዳሪ ጥርት ያለ አጀንሳ እና ጥያቄ ይዞ ካልገባ ያኔ ነው ሌሎች እነአሜሪካ የነሱን አጀንዳ በማር ቀብተው የሚያቀርቡለት!!!!
ድርድር ጦርነት ነው! ልክ ዛሬ አንድ የደጋ ዳሞት ዉጊያ ፕላን እንደ ሚያደርገውና በጥንቃቄ እንደ ሚዋጋው እያንዳንዱ የድርድር እርምጃው የሚታቀደውና የሚፈጸምው በዚያ ልክ ነው!