Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13206
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

እዬዬም ስደላ ነዉ፤ አሉ አባዉ ስተርቱ።

Post by DefendTheTruth » 30 Dec 2023, 14:20

Dr. ዐብዪም ይህችኑ መርሆ በመከተል፣ አይዞን፣ እዬዬዉን ና ሙሾዉን እናንተዉ ዉረዱት፣ አስወርዱት፣ እኔ ደግሞ ለዛ የምሆናችዉን ስንቅ እሰንቅላችዋለሁ እያለ የምሄድ ይመስላል።

እነሱ ሰዉ እየሞተ ብሎ ይከሱታል፣ ልማት ምን ያደርጋል ይሉታል፣ ይከሱታል፣ የሱ መልስ ደግሞ እንዴ ሆድ ከልሞላ ለእዬዬዉም አንበቃም፣ ስለዚህ እኔ ቅድማ ሁኔታዉን አሟላላችዋለሁ፣ እናንተ ደግም በሱ ላይ ቆማችዉ እዬዬዉን በደንምብ አስነኩት፣ የስራ ክፍፍል ነዉ ና። ይለዋቸዋል፣ እንደምታየዉ ከሆነ።

አረ ተዉ እባክህ እዬዬዉ ላይ እናተኩር፣ ይሉታል። አረ ተዉኝ ቅድማ ሁኔታዉን ላሟላለችዉ እንጂ ይላቸዋል። ክርክሩ ይቀጥላል።

በሙሾ አዉራጆች ና በሰራተኞች መሃል። በምያወሩ አፎች ና በምሰሩ እጆች መሃል ማለት ነዉ።