Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15365
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

< የፕሪቶሪያው (Pretoria) ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። የሰላም ሚንስቴር እውቅና አይሰጠውም፤አለተሳተፈበትም > ታዬ ደንዳ ጉድ አፈላ።

Post by Abere » 12 Dec 2023, 10:55

< የፕሪቶሪያው (Pretoria) ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። የሰላም ሚንስቴር እውቅና አይሰጠውም፤አለተሳተፈበትም > ታዬ ደንዳ ጉድ አፈላ።
በእርግጥም የሰላም ሚንስትር የማያውቀው ማንኛውም የሰላም ውይይት ህጋዊ አይደለም። ታዬ እንዳለውም የተሳተፉት ሁሉ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ናቸው። ለነገሩ የተፈረመው ወረቀት ብዕሩ ሳይደርቅ ነው አማራ ፋኖ ቦጫጭቆ ፕሪቶሪያን ወደ ሽንት ቤት የጨመረው እነ አብይ፤ ወያኔ፤ ኦባሳንጆ እና ምዕራባዊያንን ጸጉራቸውን ያስነጫቸው።እውነት ትዘገያለች እንጅ አደባባይ መውጣቷ አይቀርም የሚለው ብሂል እንድህ ነው። ጉዳዩ ህገ-ወጥ መሆኑን አግባብ ካለው መስሪያ ቤት እና ባለስልጣን አፍ ለህዝብ ተደመጠ።

Abere
Senior Member
Posts: 15365
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: < የፕሪቶሪያው (Pretoria) ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። የሰላም ሚንስቴር እውቅና አይሰጠውም፤አለተሳተፈበትም > ታዬ ደንዳ ጉድ አፈላ።

Post by Abere » 12 Dec 2023, 11:11

በወያኔ ሰፈር -የተደለቀለት፤
በ4ኪሎ ግቢ የተጨፈረለት፤
በእነ ማይክ ሃመር የተደነቀለት፤
በእነ ኦባሳንጆ የተሞካሸለት፤
የ"ፕሪቶሪያ-ውል" እንዳ ተዘምሮለት፤
ታዬ ፉርሽ አድርጎ ጣለው ወደ ቅርጫት፥
ጽዳት ሰራተኞች ከሚንስትር ግብ አርቀው እንድያነዱት።

የሰላም ሚንስትር መች ሁክት ይሆናል፤
ግብር እና ስማችን እንደትስ ይስማማል?

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 23831
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: < የፕሪቶሪያው (Pretoria) ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። የሰላም ሚንስቴር እውቅና አይሰጠውም፤አለተሳተፈበትም > ታዬ ደንዳ ጉድ አፈላ።

Post by Fed_Up » 12 Dec 2023, 12:55

ተጨፈረ ተጠጣ..ዉስኪ ተንቆረቆረ
ወያኔም ፈነጨ ፒፒም ቀመረ
ለዘመናት ሊገዛ.. እያደናገረ
አጨናብረው ሊያልፋን ምንም እንዳልተፈጠረ
ህዝቡም በዝምታ ውስጡ እያረረ
የሞቱቱ ንጹሃንን በእህህታ እየቀበረ

እውነት እና ውሸት እያደረ ይጠራል
ፒፒም ይሞታል .. ታዬም ይፈታል
የአብይ ፍጻሜ ወይ ይሰደዳል
.... ወይ ይሞታል

Post Reply