Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አጼ ምኒልክ ጠጅ ቤት! (1፡30 ደቂቃ ላይ ይመልከቱ) በምኒልክ ሰፈር ኬላ ከተማ!

Post by Horus » 03 Nov 2023, 15:38

ኬላ በደቡብ ሶዶ ያለ ቀስበቀስ ከተማ እየሆነ ያለ ገበያ ነው ። ያንዷ አክስቴ አገር ነው ።

ድሮ አጼ ምኒልክ ወደ ወላይታና ደቡብ ሲዘምቱ ሰራዊታቸው ይከትምበት ከነበሩት የሶዶ ጉራጌ ቦታዎች ውስጥ ቆንዳልቲቲ እና ኬላ የታወቁት ናቸው ። ሌሎችም አሉ።

እኔ ልጅ ሆኜ እዚህ አካባቢ ታዋቂ የነበረው የሱተን ሰኞ ገበያ ነበር። በኬላ መውረጃ ያሉት ተራሮች በዝንጀሮ የተሞላ ስለነበር በጣም ያስቸግሩ ነበር።

ዛሬ ኬላ ከተማ ለመሆን እየታተረች ነው ። ይህ ቪዲዮ የከተማው ቅዳሜ ገበያ እለት ነው ።

አጼ ምኒልክ ድንኳን የጣሉበት ቦታ ተከቦ ይታያል፣ የምኒልክ ሰፈር ይባላ! አጠገቡ የአጼ ምኒልክ ጠጅ ቤት ይታያል! ጉድ ነው!!!