Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethioscience
Member
Posts: 4100
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

Oromuma army yield to Fano!!!

Post by ethioscience » 18 Oct 2023, 16:58


ethioscience
Member
Posts: 4100
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

Re: Oromuma army yield to Fano!!!

Post by ethioscience » 18 Oct 2023, 17:20


Horus
Senior Member+
Posts: 42666
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Oromuma army yield to Fano!!!

Post by Horus » 18 Oct 2023, 17:37

ethioscience wrote:
18 Oct 2023, 17:20
የላይኛው ፋኖ አዛዥ ንግግር ማለት ይህ ነው!!!!
እያንዳንዱ ግለሰብ ከሌላው ግለሰብ እኩል ፍጡር ስለሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ እኩል መብት፣ ነጻነትና ሃይል አለው ። ይህን ፍጹም መሰረታዊ የስነ ፖለቲካና ስነ መንግስት ሕግ የማይቀበል የሕዝብ መሪ የአገር አስተዳዳሪ የመሆን ምንም አይነት ብቃት የለውም ። ከማንኛውም ያገርና ሕዝብ አስተዳደር ሃላፊነት መወገድ አለበት ።

የአንድ አገርም ሆነ ማንኛውም ማህበራዊ ድርጅት የግለሰቦች ፖለቲካዊና ሕጋዊ እኩልነት የአንድ ስነ መንግስትና ስነ ስርዓር የመጨረሻው የማይጣስ የፍትህ ዶግማ ነው ። በፍትህ ዶግማ ላይ ያልተመሰረተ ስነ መንግስት የግፍና የሕገ አራዊት ስርዓት ነው ። ነጻ ሕዝብ ይህን በመሰለ ስነ መንግስት ውስጥ በፍጹም መኖር ወይም ይህን ለሰው ልጆች የማይመጥን አገዛዝ እምቢ ማለት የተፈጥሮ መብትና ግዴታቸው ነው ።

ፍትህ በሌለበት ሁሉ ግፍ አለ ።

ሌላው ከፍትህ ቀጥሎ ያለው የማንኛውም ስነ ፖለቲካና ስነ መንግስት የማይጣስ ዶግማ ፖለቲካዊ ፍኖተ ርትዕ ነው። በዘመናችን መልካም አስተዳደር (good governance) የተባለው ጽንስ በፖለቲካ ደላሎችና ዲክታተሮች የረከሰ ቃል ቢሆንም በትክክለኛ ኦሪታዊ (ኦሪጂናል) ትርጉሙ የስነ መንግስት ፍኖተ ር ት ዕ ማለት ነው ። ርትዕ እውነት፣ እውነተኛ ማለት ሲሆን ሌላ ትርጉሙ ጥሩ፣ መልካም፣ ያልቆሸሸ፣ በውሸት፣ በሙስና፣ በግፍና ብልግና ያላደፈ ንጹህ ማለት ነው ።

ስለሆነም የስነ መንግስት፣ የስርዓተ አስተዳደር የእውነት መንገድ ምን እንደ ሆነ የማያውቅና ይህን የሚጥስ የሚገድፍ የስነ መንግስት ፍኖተ ርትዕ የማይከተል የሰዎች መሪ ሊሆን አይችልም ። በታሪክ አጋጣሚና አደጋ የመንግስት ስልጣን ይዞ ከሆነም አንድም በሰላም ካልሆነም በጉልበት ከስልጣኑ መወገድ አለበት ። አንድ የነጻ ሕዝብ ሌላ የተፈጥሮ ምብትና ግዴታ ይህን የመሰለ ውሸተኛና ባለጌ የመሪነት አስመሳዮችን ማስወገድ ነው ።

ርትዕ በሌለበት ሁሉ ሌብነት አለ።

ከፍትህና ርትዕ በተጨማሪ ያሉት ዝባዝንኬዎች ሁሉ ዝም ብሎ የስርዓቱ አሸክታቦች ናቸው ።

ሆረስ ዐይነ ብርሃን

Post Reply