Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42670
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አበረ፤ ከዛሬ ጀምሮ የምንሰማችው አዳዲስ ቃላት የኦሮሞ ፋኖ! የሸዋ ፋኖ! የደቡብ ፋኖ የሚሉ ይሆናሉ!

Post by Horus » 14 Sep 2023, 21:41

ሺመልስ አብዲሳ ሸገር ከተማ ብሎ መሬታቸው የቀማቸው የገላን፣ ሰበታ፣ ወዘተ ኦሮሞች አምርረው ተቃውመው ሺመልስ በኃይል ጸጥ እንዳሰኛቸው ይታወቃል። ልክ እንደ ከረዩ ኦሮም እነዚህ ያዲሳባ ዙሪያ ኦሮሞችም የኦሮሞ ፋኖ አቁመው ካማራ ፋኖ ጋር ሆነው መሬታቸውን እንደ ሚያስመልሱ ግልጽ ነው ።

ስለዚህ የአማራ ፋኖ ፖለቲካ ክንፍ ይህን ሁሉ እስትራተጂ በትክክል መቀየስ አለበት ! ኦሮሞች ለአቢይ ዙፋም በገፍ እንደ ማይሞቱ ከወዲሁ በአማራ ውስጥ የተረጋገጠ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 15385
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አበረ፤ ከዛሬ ጀምሮ የምንሰማችው አዳዲስ ቃላት የኦሮሞ ፋኖ! የሸዋ ፋኖ! የደቡብ ፋኖ የሚሉ ይሆናሉ!

Post by Abere » 15 Sep 2023, 12:04

ሆረስ፤

ተጨባጭ እውነታዎች ተንዠርግገው በስለዋል አሁን የእነ ሽመልስ አብዲሳን መውደቅ የማይጠባበቅ እና ጠጠር መጣል የማይፈልግ የህበረተሰብ ክፍል የለም። ግን እንደት እና የት ላይ የሚለው ብቻ ነው ያዘገዬው። በነገራችን ላይ የሸዋ ኦሮሞ የኦሮሙማ መጠቀሚያ እንጅ በምንም መልኩ ኦሮምያ ተብሎ ከተሰበሰው ትርጉም አልባ ቅልቅል ተጠቃሚ አይደለም። ተጎጅ ነው - ሁሉ ነገር ከሸዋ ኦሮሞ ተነጥቆ ለኦሮሙማዎች የግል ጥቅም ይሰጣል - ስለዚህ የሸዋ ኦሮሞ ጊዜ ጠብቆ ከፋኖ ጋር መቆሙ አይቀርም። ሌሎችም እንድሁ በተለይም የጥንቱ የሸዋ ክፍለ ሀገር አውራጃ የሆኑ ጎሳዎች ጉራጌ፤ ሃዲያ፤ከምባታ፤ ወዘተ በቅርቡ ፋኖዎች ሁነው ብቅ ይላሉ። የሸዋ ህዝብ በአንድ ላይ "እኛም ፋኖ ነን" በማለት ደማቋን የኢትዮጵያ አረንጓደ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ያውለበልባሉ። ፋኖነት ስር እየሰደደ እና እየተጠናከረ ነው - የኦነግ እና ወያኔን የበሰበሰ ጉማጅ ስር መንግሎ የመጣሉ ሂደት ይሳካል።

ይህን ያለውን እውነታዊ ተጨባጭ እና መልካም አጋጣሚ ፋኖ በደንብ ሊጠቀምበት ይገባል። ማለትም በሸዋ ክፍለ ሀገር አውራጃዎች የፋኖነት ስልጠናና እና አደረጃጀት፤ የትጥቅ ስራዎችን ማከናወን። ሽመልስ አብዲሳ ሊጨፈልቃቸው የፈለገው እና እያሰቃያቸው ያሉት ጎሳዎች እራሳቸውን እንድከላከሉ ማስታጠቅ፤ ማስለጠን፤ ማደራጀት ተገቢ እርምጃ ይሆናል።

Horus wrote:
14 Sep 2023, 21:41

Post Reply