ልጅ ሆኜ ስለፋኖ እንደ ቀልድ ነበር ስሰማ ያደኩኝ። ያ ፋኖ ነበር፣ ያ ባንዳ ነበር ሲባል። ፋኖ ጎበዝ አርበኛ፣ በሃገሩ ዉስጥ የሸፈተ፣ የሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት ግዜ በነፃነት ለነፃነት የቆመ። በጦርነቱ ግዜ ንጉሰ ነገስቱ ለስደት ተዳርገዉ ወራሪ የሃገሩን ዋና ከተማ ሲወር የፋኖ ልብ በነፃነት ነበር የቆመዉ። ኣይዴለም?
በዜና እንደሚሰማዉ የዘንድሮ ፋኖም ለህዝቡ ነፃነት ነዉ ያመጸዉ። ኣይዴለም፧?
ስለዚህ ፋኖ የዘላለማዊ ነፃነት ምልከት እና ምሳሌ ነዉ ማለት ኣይቻልም?
ከተቻለ መለኮታዊ ምልክት ኣለ ከተባለ፣ ዘላለማዊ የሆነ ምድራዊ ነፃነትም ኣለ ከተባለ ምልክቱም ምሳሌዉም ፋኖነት ኣይዴለም? ይህ ነዉ የፋኖነት ፊኖምነን።