በመስከረም አበራ ላይ ያለኝ አስተያየት በዛን ግዜ ካለኝ የተለየ ነው። ያን (https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308880) በጻፍኩበት ሰዓት መስከረም አበራ ኤርሚያስ ለገሰ የነበረበት ጁንታ 360 ተበሎ ሲጠራ በነበረው ሚድያ ላይ ከክህደቱ አያሌው ጋር ሙግት ለማድረግ መስማማቷን በሰማሁብት ጊዜ ነው። በኔ እምነት (አሁንም ድሮም ለምንጊዜም) በአማራ ስም ወይም በኢትዮጵያ ስም እታገላለሁ የሚል ሰው ከክህደቱ አያሌው ጋር እንኳንስ መሟገት ይቅርና አንድ አውራመንግድ ላይ መታየት የለበትም። ክህደቱ አያሌውና ብራምጡ ነጋ በአማራ ወይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ፍጹም ቦት እንዲኖራቸው አያስፈልግም። ለነኝህ ከሃዲዎች የፖለቲካ ኦክስጅን መስጠት ተገቢ ኣይደለም። እቃወመዋለሁ አወግዘዋለሁ። ክህደቱ አያሌው ከፈለገ ርዮት የሚባለው ሚድያ ላይ ወጥቶ ከእውሩ ጁንታ ጋር ይሟገት።