ከEMS ጋር የነበረኝ የአንድ ዓመት ተኩል ጉዞ ማብቃቱን ለEMS ባልደረቦቼ እና ለቦርዱ በዛሬው ዕለት አሳውቂያለሁ።EMS ላይ ለሳምንታት ባለመቅረቤ በተለያዩ መገናኛ መንገዶች ጥያቄ ላቀረባችሁ ወገኖች ለሁላችሁም በተናጠል ምላሽ መስጠት ያልቻልኩት ከአቅሜ በላይ በመሆኑ ስለነበር ይቅርታ እጠይቃለሁ።ዕረፍት ላይ መሆኔን የገለፅኩላችሁም በዕርግጥም ዕረፍትም ላይ ነበርኩ።በዕረፍት ግዜው ውስጥ ነገሮችን በመገምገም የኔ ከEMS መልቀቅ ለኔም ሆነ ለተቋሙ እንዲሁም ለመላው የEMS ባልደረቦች አስፈላጊ እንደሆነ ይበልጥ በማመኔ ከEMS ጋር ያለኝ ግኑኝነት ከዛሬ ነሐሴ16/2015 ( August 22/2015) ጀምሮ ማብቃቱን እገልፃለሁ።
ሲሳይ አጌና

