Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት የተጀመረው፤ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ “ዘግናኝ የሚባል ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ነው” የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ

Post by sarcasm » 18 Aug 2023, 16:49

ሰሜንም እንደዚህ አይደል የተገለጸው?



በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት የተጀመረው፤ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ “ዘግናኝ የሚባል ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ነው” የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ


ከተበተኑ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላት መካከል፤ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን መቀላቀላቸውን የሰላም ሚኒስትሩ ገለጹ

በአማኑኤል ይልቃል

በአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ስራ ከተጀመረ በኋላ 50 በመቶ የሚሆኑ የልዩ ኃይል አባላት “እንደተበተኑ” እና ከእነዚህ ውስጥ “አብዛኛዎቹ” ታጣቂ ቡድኖችን እንደተቀላቀሉ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ። በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት የተጀመረው፤ ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ “ዘግናኝ የሚባል ጥቃት መክፈታቸውን” ተከትሎ እንደሆነም ገልጸዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ ይህንን የተናገሩት፤ በአማራ ክልል ከሰሞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ትላንት ሰኞ ነሐሴ 8፤ 2015 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባው ካፒታል ሆቴል በተደረገ ውይይት ላይ ነው። አቶ ብናልፍ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመሩት በዚህ ስብሰባ 16 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

በውይይቱ መጀመሪያ ላይ 30 ደቂቃ ገደማ ለሚጠጋ ጊዜ ማብራሪያ የሰጡት የሰላም ሚኒስትሩ፤ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ ጋር ውይይት ለማድረግ የታሰበው “ከመንግስት በተነሳ ሀሳብ” መሆኑን ለተወካዮቹ ተናግረዋል። አቶ ብናልፍ በዚሁ ማብራሪያቸው፤ መንግስት በአማራ ክልል ያጋጠመው ግጭት “ዝም ብሎ በድንገት የተፈጠረ” ነው የሚል እምነት እንደሌለው እና “በተለያዩ ጊዜ የሚነሱ እና እየተደመሩ የመጡ ችግሮች የፈጠሩት” እንደሆነ አስረድተዋል።

continue reading at Ethiopia Insider https://ethiopiainsider.com/2023/11795/