Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Lovetarik » 01 Aug 2023, 08:13

ብዙ እውቀት ያካበትክ ግለሰብ ትመስለኛለህ። የምታውቀውን በሰፊው ለማጋራት መጽሐፍ ብትጽፍ ትውልድ ይጠቀማል።
ትውልድ በፈጠራ ታሪክ እየተሳሳተ ባለበት በዚህ መጥፎ ጊዜ ትክክለኛ የአገራችንን ታሪክና ባህል በጽሑፍ ቢቀመጥ ትውልድ ይጠቀማል።

It would be a breath of air.

Horus
Senior Member+
Posts: 42691
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Horus » 02 Aug 2023, 01:04

Lovetarik wrote:
01 Aug 2023, 08:13
ብዙ እውቀት ያካበትክ ግለሰብ ትመስለኛለህ። የምታውቀውን በሰፊው ለማጋራት መጽሐፍ ብትጽፍ ትውልድ ይጠቀማል።
ትውልድ በፈጠራ ታሪክ እየተሳሳተ ባለበት በዚህ መጥፎ ጊዜ ትክክለኛ የአገራችንን ታሪክና ባህል በጽሑፍ ቢቀመጥ ትውልድ ይጠቀማል።

It would be a breath of air.
ላቭቶክ፣
አመሰግናለሁ ። ያማ አይቀርም፣ ፎርማል ትምህርቴ የፖለቲካ አይንስና ሳይኮሎጂ ነው ። የቋንቋ ኢቲሞሎጂና ፊሎሎጂ የ30 አመት ሆቢዬ ነው ። በቋንቋና አፕላይድ ሳይኮሎጂ ላይ በሺ ገጾች የሚቆጠር ማስታወሻ አለኝ ። አልፎ አልፎ ፍላሽ ድራቮች እየጠፋብኝ ከማጠፋው በተቀር ብዙ ማስታወሻ ጽፌያለሁ ። ግን ኦርጋናይዘድ ሆነው ጸድተው ላንብቢ ፊት የመቅረብ ዝግጅት ይፈልጋሉ ። እጅግ አመሰግናለሁ ለሃሳብህ :!: :idea:

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Lovetarik » 02 Aug 2023, 01:41

Honestly, your etymological and philological analysis us very impressive. ክፉ ጊዜ ሄኖ ነው እንጂ people like you are, or should have been considered national treasures.

Horus
Senior Member+
Posts: 42691
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Horus » 02 Aug 2023, 02:08

Lovetarik wrote:
02 Aug 2023, 01:41
Honestly, your etymological and philological analysis us very impressive. ክፉ ጊዜ ሄኖ ነው እንጂ people like you are, or should have been considered national treasures.
እንደዚህ እንኳን ከፍ አታርገኝ ደሞ አንጎሌ ላይ እንዳይወጣብኝ! እንተምን እንዲሁ አመሰግንሃለሁ! ተናጋሪና ሰሚ ያንድ ሳንቲም ግልባጮች ናቸውና! እግዚአብሄር ያክብርልኝ!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7364
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Naga Tuma » 03 Aug 2023, 17:47

Lovetarik:

መልከም እና ኣስፈላጊ ሀሳብ ነዉ። እኔም ከኣሁን በፊት ብያንስ ሁለቴ እዚሁ ፎረም ላይ መጽሓፍ ጻፍ ብዬዉ ነበር።

ሆረስ መጻፍ የሚችለዉ መጽሓፍ ምን ዐይነት እንደሆነም በግልጽ ይታየኛል። ምክንያቱም ሰለ አከባቢያችን ጥንታዊ ታሪክ ሁለት ተጽፈዉ ሶስተኛዉ ተንጠልጥሎ ያለ መሆኑን ኣንብቤ ስለገባኝ ነዉ። ይህን ሙላበት ነበር ያልኩት።

ሁለቱም ስለ ስደት እዉነቶች የተባሉ የጥንት ታሪክን ያስተካካሉ ናቸዉ። ሁለቱ ጀመሩት እንጂ ኣላገባደዱትም።

ኣንደኛዉ ትዉልደ እስራኤላዊ የሆነዉ ስግመንድ ፍሪዩድ በ1939 እ ኣ አ ጀርመን ሃገር ዉስጥ ያሳተመዉ ነዉ። የመጽሓፉ ስያሜ ሞሰስ ኤንደ ሞኖተይዝም ይላል።

የመጽሓፉ ድምዳሜ ሞሰስ ወይም ሙሴ የግብጽ ፈረኦን የነበረ እና ወደ እስራኤል ተሰዶ የእስራኤልን ህዝብ የተመረጣችሁ ያላቸዉ እንጂ ትዉልደ እስራኤላዊ ኣልነበረም፤ የእስራኤል ህዝብ የተመረጥን ኣላሉም ነዉ። ልብ በል።

ጀርመን ሃገር ዉስጥ እየኖረ ምን ለዚህ ምርምር ኣነሳስቶት መጽሓፊን በ1939 እ ኣ አ ለህትመት ኣበቃ የሚለዉ ሌላ ጥያቄ ነዉ።

ሁለተኛዉ መጽሓፍ ትዉልደ ግብጻዊ የሆነዉ እንግሊዝ ሃገር የሚኖር አህመድ ኦስማን በ2002 እ ኣ አ ያሳተመዉ ነዉ። የመጽሓፉ ስያሜ ሞሰስ ኤንደ አክናተን ይላል። አህመድ ኦስማንንም ምን ኣነሳስቶት ይህን መጽሓፍ ለህትመት ኣበቃዉ የሚለዉም ሌላ ጥያቄ ነዉ።

ትዉልደ ግብጻዊዉ አህመድ ኦስማን ትዉልደ እስራኤላዊ ስግመንድ ፍሪዩድ የደመደመዉን ኣልተጻረረም። ጨመረበት እንጂ። ስግመንድ ፍሪዩድ ሞሰስ ግብጻዊ ፈረኦን የነበረ ነዉ ያለዉን አህመድ ኦስማን ልክ ነዉ ብሎ ከፈረኦኖቹ መካከል አክናተን ይባል የነበረ ነዉ ብሎ ቁጭ።

በተጨማሪም አክናተን በልጅነቱ ትዬ ከተባለች እናቱ ጋር ቅርበት የነበረዉ እና ስለሞኖተይዝም ከእሷ የተማረ ነዉ ይላል። ፈረኦን ሆኖ በፖሊተይዝም ያምን የነበረን የግብጽ ህዝብ ስለሞኖተይዝም ማስተማር ሲጀምር ተቃዉሞ ገጥሞት ለስደት ተዳረገ ይላል። የመጀመርያዉ ስደቱ ከግብጽ ደቡብ ወደነበረችዉ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ነበር ይላል። እዛም እየኖረ ግዜያዊ የመሪነት ዉክልና ካገኘ በኋኣ የወካዩ እመቤት ህዝብ ኣሳምጻበት ለሁለተኛ ስደት ተዳረገ ይላል። ከዛ በኋላ ነዉ ወደ እስራኤል የሄደዉ ይላል።

እዉነተኛ ታሪክ ከሆነ የሚወደሱ የኢትዮጵያ ሴቶች እንዳሉ ሁሉ የሚወቀሱም ነበሩ ማለት ነዉ። ከጥንት እስክ ቅርብ። ሙሴን ለስደት ከዳረገችዉ እስከ ዮዲት ጉዲት።

ሁለቱንም መጽሓፎች አንዳንድ ግዜ ነዉ ያነበብኳቸዉ። ከዐመታት በፊት። የሳትኩኝ ወይም የዘነጋሁኝ ካሉ እታረማለሁ።

እንግዲህ እነዚህ ሁለት መጽሓፎች የጀመሩትን የሙሴ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ፣ እና የስደት ታሪክን ማገባደድ ተንጥልጥሎ ያለ ስራ ነዉ። ብያንስ በእኔ አስተሳሰብ።

የእስራኤል ህዝብን የመራዉን ሙሴን ትዉልደ እስራኤላዊ የኛ ኣልነበረም ካለ፣ የግብጽ ፈረኦን የነበረን አከናተንን ትዉልደ ግብጻዊ ስለሞኖተይዝም ከእኛ ህዝብ ሳይሆን እናቱ ከነበረች የተማረ ነዉ ካለ፣ ሙሴን የእኛ ማን ይበለዉ?

ካልዘነጋሁ ሁለቱን መጽሓፎች ሳላነብ በፊት ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን የጻፈዉን የኢትዮጵያ ታሪክ ካነበብኩ በኋላ ነበር ሙሴን ኣፍርካ ዉስጥ ሞስት ዋንትድ ብዬ ያለፍኩኝ።

የታየኝ እና የሚታየኝ የሆረስ መጽሓፍ ተንጠልጥሎ ያለዉን የጥንት ታሪክ ማጠቃለል ነዉ።

ለዚህ ብዙ ይጠበቅበታል። ከብዙዎቻችን የተሻለ የቃላት ታሪክ ዕዉቀት ኣለዉ። እንሾሽላ ብሎ እስከ ሶስና፣ ህና፣ እና ሱዛን ይጠቅስልሃል። ሜሶፖታምያ ብሎ ማሳ እዛ ዉስጥ ኣለ ይለሃል። ከዛ ማሲን እና ሜሳን ያስታዉሰሃል።

ማሳን፣ ማሲን፣ እና ሜሳን ምን ያገኛቸዋል ስትለዉ ጥልቅ ዕዉቀት ስለሌለህ ነዉ እንጂ ምንም ኣያገናኛቸዉ ብሎ ይከራከራሃል።

እኔ ለማኝ ነኝ። የዕዉቀት ለማኝ። ዕዉቀትን እራባለሁ። ስለዚህ ዕዉቀትን ለምኜ ሳጣ ለምኖ ያጣ ተሳድቦ ይሄዳል እንደሚባለዉ ሙልጭ ኣድርጌዉ እሄዳለሁ። እንደ እኩያዬ። ፒር ሪቪዉ ማለት ያ ነዉ። የእኩያ ግምገማ። የወንድም ግሰጻ።

ያንን መጽሓፍ ከእሱ ስለምጠብቅ ነዉ። መጻፍ ያለበት ነዉ፣ እንደ እኔ አስተሳሰብ።

መጽሓፍ ለመጻፍ ደግሞ ስሜትን ቁጭ፣ የታሪክን እዉነት ቁልጭ ማድረግ ያስፈልጋል።

ስግመንድ ፍሪዩድ ስሜትን ቁጭ ኣድርጎ ይመስለኛል ያንን መጽሓፍ የጻፈዉ። እንድያዉም ያን ያህል ስሜትን ቁጭ የማድረግ ተጽዕኖ ምንጭ ምን ነበር ብሎ መጠየቅ በጣም ተገቢ ጥያቄ ነዉ። ህዝቤን እግዝኣብሔር መርጬኣችኋለሁ ኣላለም ብሎ መነሳት ትልቅ ሰሜታዊነትን ቁጭ ማድረግ ነዉ።

ሆረስ ኣሁን ያንን ያህል ስሜታዊነትን ቁጭ ማድረግ የሚችል ነዉ? ኣይመስለኝም። ስላልመሰለኝ ነዉ ለሁለት ሺህ ዐመታት ካዘገመዉ ስሜታዊነት እምቦጭ እምቦጭ ተላቀህ ወደ ጥንታዊዉ ካህን እና ሜሶፖታምያ ፎቀቅ ብለህ የጎደለዉን መጽሓፍ ዱብ ኣድርግልን ብዬ የምለምነዉ። ግዜ ስያገኝ።

ስለ ዱር እንስሳ እና ዕፅዋት ማላመድ፣ ስለ ስደት ታሪክ፣ እና ፊደል መቅረጽ አጀማመር ጀባ ሊለን ችሎታዉ እና ቁሳቁሱ ወይም ሪሶርስስ ያለዉ ወይም ማግኘት የሚችል ይመስለኛል። ይህ ከዛሬ አስር ሺህ ዐመታት በፊት ይጀምራል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ዱር እንስሳ እና ዕፅዋትን ማላመድ ያን ያህል የራቀ ጥንታዊነት ኣለዉ።

በቅርቡ እዚሁ ፎረም ላይ ሆረስ ሜሶፖታምያ ዉስጥ ማሳ የሚል ቃል ኣለ ሳይል በፊት ጃሬድ ድያመንድ ስለጻፈዉ ጀርምስ፣ ገንስ፣ ኤንደ ስቲል መጽሓፍ ኣንብቤ ዕፅዋትን ማላመድ የተጀመረዉ ፈርታይል ክረሰንት አከባቢ ነበር ሲል ኢትዮጵያ አከባቢ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ ኣለ ብዬ የጠየኩኝ። ያለ ምክንያት ኣይዴለም። የሁለቱን አካባቢዎች የተፈጥሮ ሆሞስትያስስ ልብ ስላልኩ ነዉ።

ከዛ ብዙ ቆይቼ ነዉ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ለካ ኣንተ ነህ ንባብ የሰማሁኝ።

ለማጠቃለል የዚህን ሁሉ ግዜ እና ቁልፍ የታሪክ እዉነታዎችን ዝርዝር ኣድርጎ ዱብ ልያደርግልን ይችላል። እንዳዉም የመጽሓፉ ስያሜም ምን ሊሆን እንደሚችል ይታየኛል። የተሻሉ ስያሜዎች ሊኖሩ ቢችሉም።

ስግመንድ ፍሪዩድ ተብሎ ሞሰስ ኤንደ ሞኖተይዝም ከተባለ፣ አህመድ ኦስማን ተብሎ ሞሰስ ኤንደ አክናተን ከተባለ፣ ሆረስ ተብሎ ካህኑ አከናተን ሊሆን ይችላል ባይ ነኝ።

ዉድ ግዜያችሁን ካባከንኩኝ ይቅርታ።
Last edited by Naga Tuma on 03 Aug 2023, 18:22, edited 1 time in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15394
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Abere » 03 Aug 2023, 18:15

Prof. Horus,

I pretty sure, he might have already published several books, but this is not a convenient place to disclose each one of his publications.

Horus
Senior Member+
Posts: 42691
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Horus » 03 Aug 2023, 18:36

ናጋ ቱማ፣
ዛሬ በአማራ ሕዝብ አስደናቂ ተጋድሎ (ህያውና ባይኔ ብረት የማየው) ታሪክ ፣ የሰው ልጅ ፍርሃት አልባ ጀግንነት እየመሰከርኩ ስለሆነ ያለኝ ማይንድ ሴት ኢቲሞሎጂ ወይም ፊሎሎጂ አይደለም። ያ ሌላ ግዜ ። ሁለት ነገሮችህን ብቻ አርሜህ ልሂድ ።

አንድ፣ ከምጽፋቸው መጻህፍት ውስጥ የሙሴ ታሪክ የሚል አይኖርም ። ሙሴ ግብጻዊ ነው ወይስ እስራኤላዊ እኔን እንቅልፍ የሚነሳኝ ነገር አይደለም ። እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ሞሳ፣ ሙጣ፣ ሙጬ ማለት ልጅ ማለት ስለሆነ ወደ ጥንታዊ ግብጽ በመሄድ ራመቶ፣ ራሚሲስ፣ ቱትሞሲስ ወዘተ ከመሳሰሉት ቃላት ጋር ሰረ ቃሉ (ኢቴማው) እና ስነ ቃሉ (ፊሎሎጂው) ጋር መርምሬ ልጅ ማለት መሆን ከማረጋገጥ ያለፈ ኪዩሮሲቲ የለኝም። ራሞሲስ/ራመሰስ ማለት ወልደ ጸሃይ ፣ ወልደ ብርሃን ማለትም የጸሃይ ልጅ ማለት ነው ።

አከን አተን ሞሰስ ወይም ሙሴ ከሚለው ጋር ፍጹም አይገናኝም ። አከን ማለት በጥንታዊ ግብጽ ዛሬ በግ እዝ ካህን ወይም በእብራይስጥ ኮሃን የሚባለው ነው ። ካህን የፈጣሪ አገልጋይ ቄስ ማለት ነው ። በግብጽ የአተን አገልጋይ ወይም የአተን ቄስ ማለት ነው ። አተን ዛሬ ሰን ዲስክ የሚባለው የጻኃይ ብርሃን የሚተፋው ክብ ዲስክ ነው ። ለግብጾች ያ ነበር የዲቫይን ፓወር ምንጭ ። ራህ ለሰው ልጅ የሚደርሰው ብርሃን ነበር፣ ዛሬ ሰን ሬይ ወይም የጸሃይ ጮራ የምንለው ማለት ነው ።

የግብጽ ፈርኦኖች በምድር ላይ የዚያ አተን ወኪሎች ስለነበሩ የራህ አገልጋይ ይባሉ ነበር ምንም እንኳ ጸጉር የሚላጩት ቄሶች ስማቸው ጉሩ የሚባል የተለዩ የነበሩ ቢሆንም ። በአንድ ቃል ሙሴና አከን አተን አታደባልቅ ። አከን አተን ባንድ ፈጣሪ ጸሃይ ያመነው እሱ ብቸኛ አጼ ንጉስ ለመሆን ነው ወይስ በውነትም አለምን ሁሉ የፈጠረው ጸሃይ መሆኑን መርምሮ ደርሶበት ነው የሚለው ዛሬ ማንም ሊመልስው አይችልም ።

ሌላው የማርምህ ስለ ሜሶፖታሚያ ነው ። እኔ ሜሳ ሜዳ ማለት ነው ብዬ አላውቅም ። ሜሶ + ፖታ + ሚያ ማለት ምንም ክርክር የማያሻው ከ3 ቃላት የተቀመረ የሴም ቃል ነው ። ሜሶ ማለት መሃል ማለት ሲሆን ዛሬ በኢትዮጵያ መሶብ ይባላል ፣ ክብ ተቀምጠን መሃል አድርገን የምንበላት ሌማት ነው ። ላሀም ምግብ ማለት በሴም ቃል ። ፖታ ቦታ ማለት ነው። ዛሬ ቤት የምንለው ነው ። የላቲን እስፔስ፣ እስፔቲያል የምንለው የፊዚክስ ቃል ስር ነው ። ሚያ ፣ ማይ ማለት ዉሃ፣ ወንዝ፣ ባህር ማለት ነው ። ስለዚህ ያላልኩትን አፌ ውስጥ አታስገባ ።

ለዚህ ነው ሜሶፖታሚያ ወይም የዛሬ ኢራቅ በሁለት ወንዞች መሃል ያለ መሬት የሚባለው ታይግሪስ አዩፍርቲስ ወንዞች ማለት ነው ።

ሜሳን ሜዳ አንድ ቃል ነው ወይም የሚለው ሌላ ምርምር ነው ።

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Lovetarik » 04 Aug 2023, 03:10

Naga Yuma
I thought Sigmund Freud was a German psychologist obssrssed with relating every human condition with human sexuality. I didn't know he was also an expert in antiquity.

In any case, my wish is for Horus to write a book about ancient history of Ethiopia by using his eptimological and philological expertise.

Horus
Senior Member+
Posts: 42691
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Horus » 04 Aug 2023, 04:01

Lovetarik wrote:
04 Aug 2023, 03:10
Naga Yuma
I thought Sigmund Freud was a German psychologist obssrssed with relating every human condition with human sexuality. I didn't know he was also an expert in antiquity.

In any case, my wish is for Horus to write a book about ancient history of Ethiopia by using his eptimological and philological expertise.
ሰውዬው ስለዚህ መጽሃፍ ነው የሚያወራው! እኔ እምነት ውስጥ የተደረጉ እልፍ አይነት ማለቂያ የሌላቸው ንትርኮች አይጥመኝ። ዚግሙት ፍሮይድ ስለ ሳይኮአናሊሲስ ያለው ቲሪና ፕራክቲስ አንብቤ ብዙ ከሚላቸው ጋር አልስማማም ። ስለዚህ ዚግሙንት ስለ ሙሴ ምን እንዳለ አላውቅም ።

https://www.google.com/books/edition/Mo ... frontcover

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Lovetarik » 04 Aug 2023, 07:25

አቶ ሆረስ፣
Naga Tuma"s suggestion sounds more like a philosophical work. My suggestion is for a historical work

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10937
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by ethiopianunity » 04 Aug 2023, 16:28

I was impressed with recent development of pro Ethiopians Selam, Horus, etc until, Tplf style groups strted emerging in amara region, and those pro Ethiopians are beign tricked in supporting in the name of Amara. Is it true Amara has been persecuted under Liberation Fronts? Definitely true. Is it true they should organize to protect themselves and Ethiopia? Definitely. this is what I say damn if you do damn if you don't. Meaning Ethiopians including Amara who are pro Ethiopia are now target to break Ethiopia. The organized nature of Amara currently partial fake. Tplf groups have been living in Amara region since Tplf took over even born there since Derg time and beyone. These Tplf groups now have become "Amaras" acting as Fanos. Now I am not saying the true Fanos organized who are fighting for Welqait and Ethiopia casue, but these fake ones you can't differenticate like other ordinary Amaras, and are all over Amra and other regions even in diaspora. They will always spy, organize for the cause of Tigray/Tplf whch makes it dangerous for Ethiopia and Amara. Meles on his death bed have said to Tplf and Weyane, "Until you destroy Amara, you should never rest" That is why we see here Tigray People and Halafi Mengedi waiting for hope pp government and start coming like rabid dogs. Add Shabia also who is crying "I am pro Amara" after oganizing Tplf against Amara. Now they are faking Amara, I meant Shewa leaders of Menilik and H/Selassie and not Gojam and Gondere. In fact, it is tricking Gonder as we speak. Add to that foreigners who have been flocking into Amara since Derg tymes brainwashing Amara to die for the sake of foreign take over or resource and Nile. In fact the Weyanes who were born in Amara are the ones working with these foreigners. The action of this government is bizzare also does not seem to have interest to protect Amara or Afar and is creating rift between amara and the government. It does not even have proper media to warn and advice citizens including Amara not to be duped by such elements in Amra or other regions attacking pro Ethiopia people. Being radical like Olf and tplf, will only bite the Amara.

That being said, Horus et al may not be true Ethiopians after all and could be Amices. If not, I am suggesting and have sent comments to Horus my latest finding about the Pharoahs in Egypt, and the Stones in Gurage region called Tiya which is named after the queen Pharoah in Egypt. Him writing about his experience and findings, I would advice him as well but he should set up a project about his work by seeking people like those who mentioned he should write a book... We Ethiopians are increasinly destroying outselves by not collaborating with one another instead of seeking fame and fortunte by ourselves because Liberation Fronts created this division among Ethiopians. They must wake up!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7364
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Naga Tuma » 11 Aug 2023, 15:51

Lovetarik wrote:
04 Aug 2023, 07:25
አቶ ሆረስ፣
Naga Tuma"s suggestion sounds more like a philosophical work. My suggestion is for a historical work
Lovetarik,

I read Sigmund Freud's book Moses and Monotheism a while back. I understood it as a completely historical book. I also read Ahmed Osman's Moses and Akhenaten book a while back. I understood that one as well as a completely historical book. I have been looking for another historical book that makes their works complete.

Wikipedia has the following entry about Sigmund Freud:

Sigmund Freud was born to Ashkenazi Jewish parents in the Moravian town of Freiberg, in the Austrian Empire (now Příbor, Czech Republic), the first of eight children.

I understood it as true.
Last edited by Naga Tuma on 11 Aug 2023, 17:33, edited 1 time in total.

Right
Member
Posts: 4791
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አቶ ሆረስ Horus ለምን መጽሐፍ አትጽፍም?

Post by Right » 11 Aug 2023, 16:29

Brother Horus is impressive. His pragmatic approach to politics is exemplary.

Post Reply