ኢትዮጵያ የሚባል ዕየቆመ ነው። የኣብይ መንግስት ኢትዮጵያን ኣፍርሧታል ለምን ህዋሃት ከተሸነፈ ጀምሮ ኣገሪቱ ወደ ኣንድነት ከማረግ ይልቅ ከህዋሃት የበለጠ ልዩነት ዕየጠነከረ መቷል። ደቡብን ተውት፣ ቀፎና ከተሸነፈ በነፃውጪዎችና በፕሮተስታንት ከዋዠቀ ኣመታት ኣልፎታል። የመጨራሸው የቀረው የነበረው በዘረኝነት ያልተደራጀው የነበረው ኣማራው ነበር። በህዋሃትና በኦነግ ጥቃት ምክንያት የግድ ወደ ዘረኛነት ኣምርቷል። ኣውቀው ኣማራውን የሚያጠቁት በዘረኝነት ዕንዲደራጅና ስለ ኢትዮጵያ ዕንዳያስብ ነው፣ ይህም ተሳክቷል። የውጭ ሃይሎችና በሻብያ የሚመራው ነፃ ውጭዎች ትልቅ ስኬታማን ኣግኝተዋል። ኣሁን የሚጠብቁት ወጣቱና ትውልዱ ስለዘራቸው ዕንጂ ስለ ዒትዮጵያ ኣላማም የላቸውም። ኣዲሱ ትውልድ ኢትዮጵያን ለዘላለም ኣንዱ ዕስከሚያሸንፍ ድረስ ዕልቂትና ወይም በርግጠኝነት የተበታተነ ኣገር ዕንዲኖር በመንግስት፣ በህዝብና በነፃውጭዎች ዕየተሰራ ነው።
ኣብይ መንግስትን ይሚረዱ ስለኢትዮጵያ የሚሰራ መስሏቸው ኣንድ ጥያቄ ኣለኝ። የት ሄዱ የዖነግ መሪዎችንና ታጣቂዎች፧ ዕነ ዳውድ ኢብሳ፣ ወዘተ ከሻብያ ስልጠና በሗላ ከኣስመራ ዕልልል ተብሎ ገብተው ወደ ወለጋ ሄዱ። በነዋሪዎቹ ላይ ብዙ ግድያ ኣደረሱ። ኣብይ መንግስት ኣይደለም ዳውድ ኢብሳንና ኦነጎችን በመስገባት፣ ህዝብን በዚህ ታጣቂዎችና መሪዎች ተባባሪ በመሆን ኣገር ውስጥ ኣስገብቶ ብቻ ሳይሆን ሰው ሲገደል ኣበባ ይተክል ነበር ልክ ዕንደ ሌባ ነገሮችን ከህዝብ ለመደበቅ። ስለዚህ ኣብይ ደጋፊዎች ኢትዮጵዊ ነን የሚሉት ዕንዴት ነው፣ ኣይደለም ህዋሃት ፴ ኣመት ኢትዮጵያን በግፍ ሲገዛና ሲለያይ፣ ሌላ ግፈኛ ኦነግን ኣገር ውስጥ ኣስገብቶ የበለጠ ግድያና ልይነትን ዕያባሰ ስለሆነ፣ ለምን የዚህ መንግስት ደጋፊዎች ሌላው ይቅር፣ ስለ ኦነግ፣ ዳውድ ኢብሳ ወለጋ ውስጥ ምን ዕያደረጉ ዕንደሆነ የማይናገሩት። ዕራሳቸው በዘር ባካባቢው መምሰል ስለ ተጠመዱ ነው፧ ዝም ካሉ ኣብይ መንግስት ገንዘብና ማምረት ስለሚፈልግ፣ በዛ ትደራጅተው መስራት ስለሚችሉ፣ ለዚህ ነው ዝም ያሉት፧ ዕነዚህ ነፃውጪዎች ህዋሃትና ኦነግ ትውልዱን ወደ ጥላቻ ዕያዳረጉት ዕውነት በሰላም ኣገር መገንባት ይቻላልን፧ መልስ