በሰሜን ሸዋ ግንባር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ኦህዴድ ያሰለፋቸው አብዛኛው የጋምቤላና የደቡብ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች በሚያሳዝን ሁኔታ አየሞቱ እንደሆነ መረጃውን አጋርተው በጋምቤላና ደቡብ የምትኖሩ ወላጆች እነዚህ አሁንም መከላከያ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል እንዲቆጠቡ ምክር እንዲለግሱ አሳስበዋል::
በተያያዘ ዜና በርካታ የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአማራ ህዝብ ላይ ጥይት አንተኩስም በማለት መከላከያውን በመሰናበት እየለቀቁ ሌሎችም ከነሙሉ ትጥቃቸው ሸሽተው እየጠፉ መሆኑና ይህም በኦሮሞ ጀነራሎች የሚዘወረው የመከላከያ አመራር ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መደናገጥ ክፍፍልና ውዝግብ እንደፈጠረ ታውቋል::
በዛሬው ውሎ በ አማራ ግዛቶች በተለያዮ ቦታዎች የቀለጠ ጦርነት ሲደረግ ውሏል:: በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር የያዘውን ግዙፍ መልክዐምድር ያለውን የአማራ ህዝብን በጦርነት ማንበረከክ አይቻልም:: ይልቅ አገዛዙ ውድቀቱን እያፋጠነው ነው:: በጎጃም በጎንደር በወሎና በሸዋ የፋኖ ቁጥር ብቻ 13 ሚልዮን የሚደርስ ይታወቃል:: የአማራ ህዝብ ላለፉት 5 አመታት በኦሮሚያ ዞኖች በተለይም በወለጋ ብቻ 30 ሺሕ ያህል በግፍ ተጨፍጨፈዋል::
ይህ በሌሎች ቦታዎች ማለትም በቤነሻንጉል በሻሸመኔ በሀረር ወዘተ ያለውን ጭፍጨፋ ሳይጨምር ነው:: አንድ ሚልዮን የሚደርስ ተፈናቃዮች በደብረ ብርሃናና ሌሎች ከተሞች እስካሁን ድረስ በመጠለያ ጣቢያ ፈሶ ይገኛል:: አማራ እየተዋጋ ያለው ይህን አረመኔያዊ ግፍና ስቃይ ስላንገፈገፈው ብቻ ነው:: አማራ ይህን ሰቆቃ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም የክተት አዋጅ አውጆ የጨፍጫፊውን አብይ አህመድ ሰራዊት እየተፋለመው ይገኛል::