ይህ የአሜሪካው ዳኛ እና ፍርድ ቤት በጥቂቱ የሚከተሉት ወንጀሎች ላይ ምን ይፈርዱ የሆን?
1) ልጇን በብዙ ጥይት ከገደሉ በኋላ አናት በልጇ አስከሬን ለረጅም ደቂቃዎች ሳታለቅስ እንድት ቀመጥ ባደረጉት ላይ፤ [ የኦሮሞ እናት መከራ ያስታውሱ]
2) ባል የኋልዮሽ በገመድ ከወንብር ጋር ታስሮ ሚስት በደረሱ ልጇቿ ፊት በመንጋ ስትደፈር - የግብረ-ስጋ መጫዎቻ አሻንጉሊት ስትሆን። [ የቡራዮ ጋሞዎችን ዋይታ ያስታውሱ]
3) እርጉዝ ነፍሰ-ጡር እናት ሆድቃዋ በሳንጃ ተቀድዶ ጽንሱ ወጥቶ ሲበላ ወይም ሲጣል [ የወለጋ አማራዎች እንባ ያስታውሱ]
4) በአደባባይ በጠራራ ጸሀይ መቀጣጫ የሆኑ እና ከተማውን ጥለው የትም እንድ ሰደዱ በድንጋይ ተወግረው የተገደሉት ምስኪኖች ሞት [ አዋሳ ከተማ የወላይታ ለቅሶ ያስታውሱ]
5) ከአሜሪካን አገር በእንግድነት ለሚገባው መቀበያ ይሆን ዘንድ በሻሼመኔ ከተማ እንዴ መስዋዕትነት በግ በእንጨት ላይ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ነፍሱ እስኪ ወጣ እያጨበጨቡ ትርኢት የታደመበት [ የሻሼመኔ የግፍ ጥግ ያስታውሱ]
6) በጎንደር ማይ-ካዲራ ቤታቸው ተዘግቶ በድቅድቅ ጨለማ አንገታቸው የተቀላ - ቤት ተዘግቶ በእሳት የነደዱት አማራዎች [ የወልቃይት ሁመራ ግፍ ያስታውሱ]
7) ሰላማዊ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎች በሌሊት ቤታቸው ላያቸው ላይ በዶዘር የፈረሰባቸው - ልጆቻቸውን በጅብ ተነጥቀው መከራ የወረደባቸውን
9) የወሎ ግብር ከፋይ ዜጋ በእራሱ ገንዘብ በተገዛ የጦር መሳርያ በ 3 ምልልስ (ዙር) የታሰበበት መንግሳትዊ ወረራ፤ግድያ፤ዝርፊያ፤ ጥቃት የተፈጸመበትን [ 450 ቢልዮን ሃብት ውድመት ያስታውሱ ]
10) ወዘተ......... [ ህልቆ መስፈርት የሌላቸው የ31 አመታት ግፎችን ሁሉ ያስታውሱ]