Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15441
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

< ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሑ አይመስለኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሀዘን እርዳኝ፡፡ > ዳግማዊ ዐጼ ምኒልክ

Post by Abere » 28 Feb 2023, 15:14

ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ( የእምዬ ምኒልክ የክተት አዋጅ)

<እግዚአብሔር በቸርነቱ እስከአሁን ጠላት አጥፍቶ ሀገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስከአሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ፣ ሞት የሁሉ ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዜአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፡፡ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም ሀገር የሚያጠፋ ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት፣ እግዜአብሔር የወሰነልልን የባህር በር ዐልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ፣ የሰውን መድከም አይቼ እስከአሁን ዝም ብለው፣ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል፣ መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን በእግዜአብሔር እረዳትነት ሃገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሑ አይመስለኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሀዘን እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፡፡ አልተውህም፡፡ ማርያምን ለዚህም አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እሰከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ፡፡>