ተራ በተራ ተነስተው የሚወድቁ የጎሳ ሹክሻኮች ለዘመነ ዘመናት ቢታክቱ እምዬ ምኒልክ ዳግማዊን ከአድዋ! ኢትዮጵያን ከምኒልክ! ምኒልክን ከልሙጡ ሰንደቅ ለመለየት ቀይ መስመር ፋውል ረጋጭ ሁሉ እንዳለፉት የኢትዮጵያ ጠላቶች ወደ ታሪክ ትቢያ ይጣላሉ !
በሚቅጥሉት 4 ቀናት ብዙ ድራማ፣ ብዙ ቲያትር እናያለን ። የኦሮሞ ተገንጣይ ልፋት ምኒልክን ከአድዋ የሚገነጥል አድዋ እንደ ክብር ምኒልክ እንደ ወራሪ ለመተረክ የሚዳክሩት አዲሱ ቆሻሻ የጎሳ ናሬቲቭ ያው እንደ ተለመደው አፍንጫቸው ላይ ይፈነዳል ።
ታላቁ መሪ መቃብሩ ውስጥ እንዳያርፍ ይህን ዘመን ሁሉ ለፉ ባከኑ ። ዛሬ የኢትዮጵያ ማነንት፣ የሕዝቧ ህልውና መገለጫው ፈተና፣ ውዝግብ፣ የማይታለፍ ቀይ መስመር የኢትዮጵያ እናት እምዬ ምኒልክ ነው ።
ደሞ ትግሉ ይቀጥላል እንጂ አድዋ በወያኔ ባንዲራ አይከበርም ። ኣድዋን አለ ምኒልክ፣ ምኒልክን አለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ወይ ፍንክች ! መንግስት የመጣል መንግስት ይሄዳል ! ማንም ይህን ቀይ መስመር ሊጥስ አይችልም !
ለሚቀጥለው 4 ቀናት ጆሮአችን በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ እንደ ሚዶነቁር ተጠባበቁ!