ሥጋችሁን የሚገድሏትን አትፍሩ ፤ ነፍሳችሁን መግደል አይቻላቸውምና።
ሰማዕትነት የሚታደሉት በአምላካቸው ጥሪ የፍኖተ መስቀልን ጉዞ ተከትለው ጠላታቸው ሰይጣንን ታግለው እስከ ሞት ድረስ የታመኑት ናቸው። በዘመናችን ጥቂት የማይባሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ጥንቶቹ ሁሉ አሁንም ሃጥያት በበዛባት ምድር ላይ የሰማዕትነት ክብር እያገኙ ነው። በሊብያ በርሃ ለአሸባሪው አልቃይዳ ማተባቸውን ሳይበጥሱ በጀግንነት እና በክብር አንገታቸውን የሰጡት ኢትዮጵያዊያን ለአለም እምነት እስከየት እንደሚደርስ እንዳላሳዩ ሁሉ ዛሬም ይህ ትውልድ በትውልድ አገሩ ላይ ከሰይጣን መንግስት ከሆነው ኦሮሙማ ጋር ለእምነቱ ትንቅንቅ እያደረገ ሰማዕትነትን እየተቀበለ ነው።