Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15448
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ብልጽግና ወልቃይት ሁመራ እና ራያን መንካት ማለት በእራሱ ግንባር ላይ የመሳርያ ምላጭ እንደ መሳብ ነው።

Post by Abere » 06 Jan 2023, 16:22

ብልጽግና ወልቃይት ሁመራ እና ራያን መንካት ማለት በእራሱ ግንባር ላይ የመሳርያ ምላጭ እንደ መሳብ ነው።የአማራ ህዝብ በደሙ ያስመለሳቸውን እርስት ለመንጠቅ የሚፈልግ ማናቸውም ሃይል ድጋሜ ደም ለማፍሰስ የተዘጋጀ መሆን አለበት። ደሜን አፈሳለሁ አጥንቴን እከሰክሳለሁ የሚል ሃይል ካለ ብቻ በግልጽ የአማራ ጠላት ነው አማራ ተገድዶ አፈሙዙን ወደ እርሱ ያዞራል። ማንም ምድራዊ ሃይል የአማራን ህዝብ አስገድዶ መንጠቅ ይሁም ማጭበርበር አይችልም። እነኝህ እርስቶች ለአማራ ህዝብ ቀይ መስመሮች ናቸው። ምንም አይነት ቁማር አይበላቸውም። መንግስት እራሱ ወንበደ ከሆነ ብቻ በውንብድና ሊሞክር ይችላል - ግን ሰላም ማምጣት አይችልም ውርደት ግን ያተርፋል። የተዘጋ ፋይል እከፍታለሁ ያለ ወንበደ መንግስት የእራሱን የውድቀት መቃብር ብቻ ይከፍታል።በተጨማሪ አንዳንድ ተላላኪ የብልጽግና ከፍተኛ ባለስልጣን ነን የሚሉ እንደ ሬደዋን ሁሴን ወዘተ አይነቶች ለትዝብት ባይወድቁ ይሻላቸዋል። የሌባ ተባባሪ በመሆን የሌባ ቋንቋ ባይናገሩ ይመረጣል። በአማራ ላይ ለ31 አመታት ሲጠዘጥዘው የነበረ ቁስል መነካካት ለእራሳቸው ሲሉ ቢተውት መልካም ነው። አማራ በእራሱ ረዥም መራር ትግል ጅምላ ጭፍጨፋ እና የጅምላ መቃብር ድንጋይ ፈንቅሎ ተነስቶ አሁን ወልቃይት ሁመራ እና ራያ ላይ እየኖረ ነው። 4 ኪሎ አይደለም የሚፈልገው በእርስቱ ላይ መኖር ነው።