-
Eripoblikan
- Member
- Posts: 3547
- Joined: 15 Sep 2019, 13:49
Re: መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የሰዎች፥ መፈናቀል፥ ያቆማል፥ ዋናው፥የሙስና፥በርም፥ ይዘጋል፤
ይህን ጉዳይ ከፓለቲካ ወገንተኝነት በጸዳ መልኩ መመልከት ይገባናል።
በመጀመሪያ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ከተማ ተብየዎች ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ነው። የሚያሳዝነው ከተማዎች የሚሰሩት ለም እና እርሻ ቦታ ላይ ነው። የስራ እድል እና ስልጣኔ የማያመጡ ከተማዎች እርሻ እየቀሙ ህዝብ የምግብ እጥረት እንድ ገጥም ዋና ምክንያት ሁነዋል። የኢትዮጵያ ከተማዎች የፓለቲካ ከተማዎች (በፓለቲካ ምክንያት የሚፈጠሩ) እንጅ በኢንዱስትሪ ወይም በንግድ ወይም በሌላ የዕድገት ተጽእኖ የሚፈጠሩ አይደሉም። አዲስ አበባ ቢሆንም በእድገት ገፊ ምክንያት የተፈጠረ ሳይሆን በዚሁ መንገድ ነው።
አሁን ESAT ዜና እየሰራ ባለበት ጉዳይ ግን ከዚህ የተለየ አስተያየት አለኝ።
በመጀመሪያ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተፈናቀሉ ናቸው ስለሚባሉት ኗሪዎችን ስናይ ከገበሬዎች ላይ ገዝተው እርሳቸው ሃላፊነት ወስደው የፈጸሙት ነው። ይህ ደግሞ ህገ-ወጥ ሊሆን ይችላል። ገበሬዎች መንግስት መሬቱን በሆነ ጊዜ ሊወስደው ስለሚችል እራሳቸው ቀድመው እየቸበቸቡት ነው። ይህ አደገኛ ሁኔታ ነው። ከተማዋ ለዕድገት በሚያመች መልኩ እንዳትቀየስ ይረዳል። እንደ ድንኳን 20 ቆርቆሮ እየመታ ከተማ ቤቴ ማለት ትክክል አይደለም - ከተማዋን እንደገና አፍርሶ ለመስራት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚፈስ የንዋይ ብክነት ይፈጥራሉ። ከወድሁ መፍረስ አለበት። ይህ ሲደረግ ግን መንግስት በዕቅድ እና በእራሳቸው ኪሳራ የገበሬ መሬት የገዙት ወገኖች እንግልት ሳይደርስባቸው መሆን ይገባዋል ባይ ነኝ። እኔ እራሷ አዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ላይ ፈርሳ መሰራት ይገባታል ባይ ነኝ። በዘልማድ የተሰሩ ብዙ ሰፈሮች ለትውልድ የሚተርፍ ኪሳራ አላቸው። በእቅድ የተሰሩት ቢሆንም ብዙ የሚቀራቸው ወይም የጎደላቸው አሉ በከተማ መስፈርት ሲታዩ። አንድ ነጥብ ግን መንግስት መሬትን እንደ ፓለቲካ ንዋይ ማየት የለበትም። እኔ ከተማዎች በመላ አገሪቱ ለእርሻ ስራ በማይጠቅሙ ቦታዎች ላይ ቢሰሩ ይሻላል ባይ ነኝ። ህዝቡ ምን አርሶ ሊበላ ነው ለም መሬት የሳሙና ቁራጭ በሚያካክሉ የብሎኬት ክምር ቤቶች ተሞልቶ። የከተማው ኗሪ ህዝብ ስራ አጥ - ስራ መፍጠር አይችል። ቁጥር 1 ቀጣሪ መንግስት ብቻ። አምራቹ መጋቢው ገበሬ ተፈናቃይ ከሆነ። በተጨማሪ አይናቸው እያየ ጆሯቸው እየሰማ በርካታ የአዲስ አበባ ሰዎች ከገበሬ ቦታ በመግዛት ገበሬውን እያፈናቀሉ ያሉ እርሳቸው ናቸው - ለምን ከንቱ ሃላፊነት ይወስዳሉ በገንዘባቸው ላይ? መንግስት ይህን በተመለከተ ህግ ማስከብር ይገባዋል። ከተማ በዕቅድ ይሰራል እንጅ በወረራ መሆን የለበትም። ESAT is playing foolish politics making sensational news. The complaint does not make much sense to me the built on their own risk. Park at your own risk you will get towed. That is what happened to these squatter settlement owners. However, towns and cities eating up farming lands should be stopped, they are eating people.
Re: መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የሰዎች፥ መፈናቀል፥ ያቆማል፥ ዋናው፥የሙስና፥በርም፥ ይዘጋል፤
ቤቶቹ፥ ህገወጥ፥ ከሆኑ፥ መጀመርያውኑ፥ መሰራት፥ የለባቸውም ። የአካባቢው፥ ህግ፥ አስከባሪዎች፥ ጉቦ፥ እየተቀበሉ፥ ነው፥ ቤቶቹ፥ የሚሰሩት፥ አፍራሾቹም፥ እነዛው፥ ጉቦ፥ ተቀብለው፥ ቤቱ፥ እንዲሰራ፥ የፈቀዱት፥ ናቸው።
መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የመንግስት፥ ስራ፥ ውሉን፥ መፈፅምና፥ ለአካባቢው፥ የሚመጥን፥ ስታንዳርድ፥ አውጥቶ፥ ቤቶች፥ ሲገነቡ፥ ያነን፥ ስታንዳርድ፥ ጠብቀው፥ እንዲሰሩ፥ መቆጣጠር፥ ብቻ፥ ይሆናል።ሰው፥ እንደአቅሙ፥ መሬት፥ ገዝቶ፥ ቤት፥ ቢሰራ፥ የኪራይ፥ ዋጋም፥ ሊቀንስ፥ ይችላል። ገበሬውም፥ መሬቱን፥ በገበያ፥ ዋጋ፥ መሸጥ፥ ይችላል።
መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የመንግስት፥ ስራ፥ ውሉን፥ መፈፅምና፥ ለአካባቢው፥ የሚመጥን፥ ስታንዳርድ፥ አውጥቶ፥ ቤቶች፥ ሲገነቡ፥ ያነን፥ ስታንዳርድ፥ ጠብቀው፥ እንዲሰሩ፥ መቆጣጠር፥ ብቻ፥ ይሆናል።ሰው፥ እንደአቅሙ፥ መሬት፥ ገዝቶ፥ ቤት፥ ቢሰራ፥ የኪራይ፥ ዋጋም፥ ሊቀንስ፥ ይችላል። ገበሬውም፥ መሬቱን፥ በገበያ፥ ዋጋ፥ መሸጥ፥ ይችላል።
Re: መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የሰዎች፥ መፈናቀል፥ ያቆማል፥ ዋናው፥የሙስና፥በርም፥ ይዘጋል፤
ይህ ትክክል ሃሳብ ነው። መሬት እንደ ማንኛውም ሃብት እና ዕቃ የግል እና በነጻ ገበያ ሊሸጥ ይገባዋል። ይህ ግን አሁን ባለቺው ኢትዮጵያ ሁኔታ የቀደመው የደርግ ስርዐት ስላበላሸው እንደት አድርጎ ማስተካከል እንደሚቻል አስቸጋሪ ያደረገው ይመስለኛል። ወደ ቀድሞው አይነት ሰፋፊ ይዞታ እና ለልማት አመች ሁኔታ ለመመለስ አሁንም የግድ የመንግስት እጅ እንድገባ ያስገድዳል። አሁን እራሱ የግል የሚባሉ መሬቶች በእራሱ በመንግስት የተቸሩ ናቸው። በመሬት ይዞታ ደረጃ የኢትዮጵያ መሬት የማልማት ዕድል ተቀብሮ የተበላሸው በደርግ ጊዜ ነው - መሬት ለአራሹ ያጠፋው ጥፋት ትውልድ ሊመልሰው አልቻለም። በምዕራቡ አለም እንደምናየው ግለሰቦች ሰፋፊ መሬት በማያዛቸው ለልማት እጅግ አመች ናቸው። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ እና የመሬት ይዞታ ለውጥ ያስፈልጋል።ያ እስካልሆነ ድረስ መሬት ነፍስ-ወከፍ በማደል በብጥስጥስ ማሳ ላይ በማስፈር እድገት ሊመጣ አይችልም። መሬት የግል መሆን አለብት ትክክል - ግን እንደት የግል ማድረግ ይቻላል። ነፍስ ወከፍ እንደ ደርግ ቁራጭ መሬት በስሙ በመስጠት? አይመስለኝም። እንደ እኔ የ20-30 የሚደርሱ የገበሬዎች መሬት እንደት ለ1 ገበሬ ይሆናል ከዚያም ለልማት እና እድገት መሬት ተመቻቻለች ነው። ይህን ማድረግ እጅግ አስቸጋሪ ነው - ግን የግድ ይላል።
Axumezana wrote: ↑04 Jan 2023, 11:56ቤቶቹ፥ ህገወጥ፥ ከሆኑ፥ መጀመርያውኑ፥ መሰራት፥ የለባቸውም ። የአካባቢው፥ ህግ፥ አስከባሪዎች፥ ጉቦ፥ እየተቀበሉ፥ ነው፥ ቤቶቹ፥ የሚሰሩት፥ አፍራሾቹም፥ እነዛው፥ ጉቦ፥ ተቀብለው፥ ቤቱ፥ እንዲሰራ፥ የፈቀዱት፥ ናቸው።
መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የመንግስት፥ ስራ፥ ውሉን፥ መፈፅምና፥ ለአካባቢው፥ የሚመጥን፥ ስታንዳርድ፥ አውጥቶ፥ ቤቶች፥ ሲገነቡ፥ ያነን፥ ስታንዳርድ፥ ጠብቀው፥ እንዲሰሩ፥ መቆጣጠር፥ ብቻ፥ ይሆናል።ሰው፥ እንደአቅሙ፥ መሬት፥ ገዝቶ፥ ቤት፥ ቢሰራ፥ የኪራይ፥ ዋጋም፥ ሊቀንስ፥ ይችላል። ገበሬውም፥ መሬቱን፥ በገበያ፥ ዋጋ፥ መሸጥ፥ ይችላል።
Re: መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቀድ፥ የሰዎች፥ መፈናቀል፥ ያቆማል፥ ዋናው፥የሙስና፥በርም፥ ይዘጋል፤
አሁን፥ ባለንበት፥ ሁኔታ፥ የግለሰብና( የገበሬን) ጨምሮ፥ የመንግስት፥ ይዞታ፥ ይታወቃል። ግለሰብ፥ ያልያዘውና፥ የማይገብርበት፥ መሬት፥የመንግስት፥ነው። መንግስት፥በግለሰቦች፥ እጅ፤ ያለውን፥ መሬት፥ መሸጥ፥ መለወጥ፥ ቢፈቅድ፥ በመንግስት፥ እጅ፥ያለውም፥ መሬት፥ እንደሁኔታው፥ ለግለሰቦች፥ አሁን፥ እንደሚደረገው፥ በሊዝ፥ ቢሸጥ። ስታንዳርድ፥ ያልጠበቀ፥ግንባታንም፥ ቢቆጣጠር፥ ሰዎች፥ በየጊዜው፥ ከመፈናቀል፥ ከኪሳራ፥ይድናሉ።