ወንጀለኛ መታገስ ወይስ ማደለብ?
የአብይ መንግስትና አንዳንድ ሉካንዳ ቤቶች ይመሳሰልብኛል ፣ ሁለቱም ማደለብ ይወዳሉ: የአብይ ብልፅግና ወንጀለኛ ማደለቡን ተያይዞታል ፣ ያው እንደምታውቁት ሉካንዳ ቤትማ ኮሳሳ በሬ ፍየል ፣ በግ አያርድም።
የአብይ ነገር ግን ለምን ወንጀለኞችን እያወቀ ብዙ ይታገሳል ወይም አመቺ ጊዜ ይጠብቃል? ይገባኛል አንዳንዴ መታገሱ የወንጀሉን ስር በርብሮ ለማውጣትና ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ይረዳ ይሆናል ነገር ግን ወንጀል የሰዉ ሂዎት ማጥፋት ደረጃ ከደረሰ ለርምጃ መዘግየቱ ሰለባዎችና ግንኙነት ያላቸው ህዝቦች፣ግለሰቦች በመንግስት ላይ ያላቸው ምሬትና እምነት በከባድ ሁኔታ ይሸረሸራል፣ ይሄ ደሞ በአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ትልቅ አደጋ አለው ብዬ አምናለሁ። አንዳንድ ወንጀልን እንደመደበኛ ሰራቸው አርገው ህዝብ የሚያምሱ ተውው ካልተባሉና እንደመቀጣጫነት ካልተደረጉ አሁን ከሚያጠፋት ጥፋት በበለጠ የሚመርዙት አዲስ ትውልድ ሰፍር ቁጥር አይታወቅም
TheManWhoSawTomorrow