Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች 17ሺሕ ያሕል ሠራተኞች ተሰናበቱ (ዶይቸ ቬለ) | በብልጽግና ሟሟ እናዝግም እየተባለ ነው

Post by sarcasm » 11 Nov 2022, 21:21

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጦርነትና የውጭ ምንዛሪ መመናመን ብቻ ሳይሆኑ የመሠረተ ልማቶች ውድመት በደረሰባቸው ቦታዎች ላይ መልሶ ግንባታ አለመከናወኑ ከአሜሪካ የቀረጥ ነፃ የንግድ እድል መታገዷ፣ ባለሃብቶች ለማልማት ፈልገው መሬት ለማግኘት ፈተና መሆኑ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲቀንስ አድርጓል ብሏል።


ኢትዮጵያ ዉስጥ በ13 የኢንዱስትሪ መንደሮች ( ፓርኮች ) ይሰሩ የነበሩ 17 ሺህ ያሕል ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸዉ እንዳሳሰበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።ዛሬ የስራ ዘገባዉን ለምክር ቤቱ የንግድ ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበዉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ግን 17ሺሕ ሠራተኛ ሥራ አለቀቀም በማለት አስተባብሏል። ቋሙ ኮሚቴው የኢንቨስትመንት ዘርፍ በብልሹ አሠራሮች መተብተቡን ፣ ብዙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከከተሞች የራቁ እና በዋናነት ለአልባሳት ሥራ በመግንባታቸው የሚጠበቀብቸዉን አልሰሩም ብሏል። የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፍሰት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት እና በሀገር ውስጥ የግብአት ዋጋ መናር ምክንያቶች ለችግር ተጋልጧል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጦርነትና የውጭ ምንዛሪ መመናመን ብቻ ሳይሆኑ የመሠረተ ልማቶች ውድመት በደረሰባቸው ቦታዎች ላይ መልሶ ግንባታ አለመከናወኑ ከአሜሪካ የቀረጥ ነፃ የንግድ እድል መታገዷ፣ ባለሃብቶች ለማልማት ፈልገው መሬት ለማግኘት ፈተና መሆኑ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲቀንስ አድርጓል ብሏል።የኢንዱስትሪ ፓርክ በድሬደዋ
በመንግሥት የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ የሠራተኞች ክፍያ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ካለመቀረፉ በላይ ፍልሰት ማሻቀቡ የማዕከላቱ ሥራ መቀዛቀዝ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ ቋሚ ኮሚቴው ምክንያቱ እንዲነገረው ጠይቋል።
"አንድ ተቋም የተረጋጋ እንዲሆን ሠራተኛው የተረጋጋ መሆን አለበት። ከዚህ አኳያ 16, 999 ሰራተኞች ለቀዋል። ምክንያቱ ምንድን ነው? " በሚል ተጠይቋልየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ይህ ቁጥር ትክክል እንዳልሆነ ለምክር ቤቱ ምክንያቱን ጭምር አስገንዝበዋል።

Continue reading https://www.dw.com/am/%E1%8A%A8%E1%8A%A ... a-63728879