By Administrator -November 4, 20220345

ሑመራ፡ ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከዞኖች ፣ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከአጋር አካላትና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ተግባራት የግምገማ መድረክ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በሑመራ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመርኃግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፤ አንኳን ወደ አማራ መነሻ ወልቃይት ጠገዴ ምድር በሰላም መጣችሁ ብለዋል።

"ጠላቶቻችን እኛን ለመከፋፈል የተለያዩ ሴራዎችን እንደሚሸርቡ ወጣቶች ተረድተው…
"የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሕዝብ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን…
"የኢትዮጵያን ጠላቶች አንድ ኾነን እንመክታለን፤ አዲሱን ዓመት በፍቅርና በተስፋ…
“እውነትን ይዞ የታገለ ሁልጊዜ አሸናፊ ነው” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዳይኾን ሲሰራበት የነበር ሕዝብ በመኾኑ ከነጻነት ማግሥት ያለ በጀት የሚንቀሳቀስ ቢኾንም፤ ወልቃይት ቁጭትና እልህ በወለደቻቸው ልጆቿ ከኪሳቸው በማውጣት የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እያከናወነች ትገኛለች ።
የክልሉ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ወደ አካባቢው በመምጣት ውይይት ማድረጉ የዞናችንን የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ያለውን ተነሳሽነት የሚያሳይ ነው ያሉት ምክክል አሥተዳዳሪው በትኩረት የተመለከታችሁትን የአማራ መነሻ መሬት ለማልማት በቁርጠኝነት ልትሠሩ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም የዞኖችና የከተማ አሥተዳደሮች የ2015 በጀት ዓመት 1ኛው የሩብ ዓመት የክንውን ተግባራትን እያቀረቡ ይገኛሉ። ተጨማሪ መረጃ የምናደርስ ይኾናል ።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ – ከሑመራ