Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አንድ ነገር ሲደጋገም ሳይንሳዊ እና ነባር እውነት ይሆናል። በ3ኛው ዓለም በተለይም አፍሪካ የሰላም ውይይት የማይፀና የማለዳ ጤዛ ነው። ገዥ አይደለም። ለአማራ ፋኖ ያለኝ ምክር ባለህበት ጽና

Post by Abere » 03 Nov 2022, 11:00

አንድ ነገር ሲደጋገም ሳይንሳዊ እና ነባር እውነት ይሆናል። በ3ኛው ዓለም በተለይም አፍሪካ የሰላም ውይይት የማይፀና እንደ ማለዳ ጤዛ የሚጠፋ ነው። ገዥ አይደለም። ለአማራ ፋኖ ያለኝ ምክር ባለህበት ጽና ብቻ ነው።አማራ ከዚህ በኋላ በውታፍ ነቃዮች እና በካድሬዎች የተዋቡ የቃላት እና ድስኩር ጋጋታዎች ቢዘናጋ እና ዕርስት ህዝቡን መልሶ ቢነጠቅ እውነትም ተላላ ሞኝ ነው። የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደልም። እራስህን ከውታፍ ነቃዮች እና አስመሳይ ሽማግሊዎች እና የሃይማኖት አባቶችነን ባይ አጭበርባሪዎች ጠብቅ። አቋቋሙን አይተው ብትሩን አያያዙን አይተው ጭብጦውብ ቀሙት እንድሉ ዳግመኛ መነሁለል ጸያፍ ነው። የገመትከው ቀርቶ ለማመን የሚያዳገት ነገር አይተሃል ከአባቶችህ ከተማ አድስ አበባ ለመግባት ፓስፓርት ተጠይቀሃል- ምንም ነገር አይሆንም ብለህ አትጠብቅ። ተጠንቅቀህ ጠብቃቸው - የዱላህን መርዛማነት ቀምሰውታል።