ጥያቄ አለኝ! በኢትዮጵያ አንድ የሚንስቴር መስሪያ ቤት ክስ ሊመሰረትበት ይቻላል ? ውጭ አገር ግን ይቻላል። ት/ሚር 13,000 ያህል ተማሪዎችን ለፈተና አላስቀምጥም የሚል ስለ አነበብኩ
ጥያቄ አለኝ! በኢትዮጵያ አንድ የሚንስቴር መስሪያ ቤት ክስ ሊመሰረትበት ይቻላል ? ውጭ አገር ግን ይቻላል። ት/ሚር 13,000 ያህል ተማሪዎችን ለፈተና አላስቀምጥም የሚል ስለ አነበብኩ ነው። እንደ እኔ ድሞክራቲክ እና የዜግነት ፓለቲካ የሰፈነበት ከሆነ በህግ ፊት የትኛው አካል ጥፋተኛ ወይም ትክክል እንደ ሆነ የሚታወቀው በህግ እና በፍርድ ቤት ሂደት ይመስለኛል። በሚድያ በሚደረግ ፍረጃ ትክክል አይመስለኝም። ሰማይ አይታረስ፥ ንጉስ አይከሰስ አይነት አካሄድ የሰለጠነ የዜግነት ፓለቲካ እየተራመደ ባለበት ክፍለ ዘመን በፍጹም አብሮ አይሄድም። በእርግጥ ከዚህ አንጻር ዜጎች በበኩላቸው የቱን ያህል የነቁ እና የግል መብታቸውን ለመጠየቅ የተዘጋጁ ናቸው የሚለው አንድ ትልቅ ነገር። ይህ አሁን በኢትዮጵያ የምንሰማው ትምህርት ሚንስተር ውስጥ ያለው የፈተና ያመጣው አለመግባባት በሌላው አለም ቢሆን ከፍተኛ የህዝብ መነጋገሪያ ብቻ ሳይሆን የተማሪዎች ወላጆች ይሁኑ የተማዎች ማህበራት ትምህርት ሚንስቴርን ፍርድ ቤት የሚገትሩበት አብይ ጉዳይ ነው። ይህ ሂደትም አንድም ሚንስተር መስርያ ቤቱ ግዳጁን በደንብ ከተወጣ ተአማኝነቱን ያገኛል ስህተትም ከፈጸመ ከዚህ ጥፋቱ እንድማር እና ለአገሪቱ ጠቃሚ ዜጋ ማፍርያ ተቋም የደርገዋል - ያለ አግባብ የተበደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችም ፍትህ ያገኛሉ። As of now, the state of Ethiopian Education affairs is in a sate of turmoil.