Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሌብነትና የማዐት ስነምግባር

Post by Horus » 14 Oct 2022, 13:49

ዛሬ እኛ ኢትዮጵያዊያን የማዐትን ትክክለኛ ትርጉም ለውጠን ከመጥፎ ነገርና መከራ ጋር አያያዝነው እንጂ ድሮ ጽንሰ ሃሳቡን ለፈጠሩት ትንታዊ ግብጾች ማዐት (መዐት) ማለት በእውነትና ፍትህ ሚዛን ላይ መለካት ነበር ። ዛሬ ግሪኮች ፈጠሩት የሚባለው የሞራልና ኤቲክስ ህግጋት ወይም ከዚያ በፊት ለሙሴ ተገለጹ የተባሉት አስርቱ ትዕዛዛት ሁሉ ከቀምጥ የተኮረጁ የ42 ማዐት ህግጋት ናቸው ። ሁሉ ነገር ግንድ አለው ! ሁሉ ነገር ስር አለው! ለመሆኑ ዛሬ ላይ ያለው አበሻ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በእውነትና ፍትህ ሚዛን ላይ ቢለካ ስንቱ ሚዛን ይደፋል? አዋቂው ሌባ ነው! ህጻኑ ኮራጂ ነው:idea: :idea: :idea: