ጦርነት ለማንም የማይጠቅም ነው:: በወንድማማች መካከል ሲሆን ደግሞ የበለጠ ያቆስላል:: እንደ ዲያቆን ዶ/ር ቢንያም ያሉ ወጣት ወንድሞችን ሊያሳጣንም እንደሚችል ማየት ደግሞ ልብ ይሰብራል:: ዲያቆን ቢንያም ጦርነቱ እንዳይመጣ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም::
ከዲያቆን ዶክተር ቢንያም ጋር ከጦርነቱ በፊት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከጦርነቱ ጀምሮ ደግሞ መንገድ እስከተዘጋ ድረስ በበጎ አድራጎት ሥራዎች አብረን ነበርን:: በመከራ ውስጥ ሆኖ ሰብእናውና በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት ያልተናወጸ ውድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው::
አሁንም ቤተሰቦቹን አጥቶና ተጎድቶ ትሕትናው አልተለወጠም::
ውድ ወንድሜ አስተዋይ ጓደኛዬ ቢኒ መትረፍህን በቪድዮ እስካይ ድረስ እጅግ ተጨንቄ ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለ "ለሞት እንኳ ቀርቦ ነበርና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፥ ኀዘን በኀዘን ላይ እንዳይጨመርብኝ ለእኔ ደግሞ እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም" እንዳለው እግዚአብሔር ለአንተ ብቻ ሳይሆን እኛንም ከማንጽናናው ኀዘን ጠበቀን:: (ፊልጵ. 2:27)
የምናውቀውን ተናገርን እንጂ የማናውቃቸው ለሀገር ብዙ ነገር የሚያበረክቱ ውድ ልጆችን በየሰዓቱ እያጣን ነው::
ጦርነቱን ማስቆም የሚችሉ ሁሉ ይህንን ጥፋት እንዲገቱልን ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ እንደተማጸንነው አሁንም እንለምናለን:: እግዚአብሔር እሳቱን ያብርድልን:: ልባቸው የተሰበረውን ይጠግንልን::
"አቤቱ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ?
ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤
ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ" ሰ.ኤር. 5:21
Please wait, video is loading...