Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የእኔ ፊልድ ማርሻል ሀሰን ከሪሙ ነው ከቃዬው ላይ ሳይለቅ ከውጊያ ዐውድ ላይ ጥላትን ጥይት የሚያጎርሰው።

Post by Abere » 30 Aug 2022, 11:19

የእኔ ፊልድ ማርሻል ---> ሀሰን ከሪሙ ነው:: ከቃዬው ላይ ሳይለቅ ከውጊያ ዐውድ ላይ ጥላትን ጥይት የሚያጎርሰው።
ያራያ ትንታጎች ዛሬም እንደ ጥንቱ ክንዳቸውን ሳይንተራሱ ቃያቸውን አያስደፍሩም። የራያ እና የትግሬ ግብግብ ዛሬ አልተጀመረም። ዐጼ ዮሀንስ አስገድደው መሬታቸው ሊነጥቋቸው ብዙ ተጋድለዋል። ራያ ከአቅማቸው በላይ ሁኖባቸው አጼ ዮሀንስ የእንግሊዝ መንግስትን የጦር መዳርያ እርዱኝ ልመና ደብዳቤ ጽፈዋል - የራያን ህዝብ በመሳደብ አረመኔ ጋላ እና እስላም ለመውረር እና ለማስገበር በማለት። አጼ ዮሀንስ ከራያ ሽፍታ ጋር ዘመናቸውን በሙሉ እንደ ተዋጋ በመጨረሻም መተማ ሙተዋል። እንደ ሚባለውም ከሆነ መተማ ላይ በራያ ሰዎች እጅ እንደ ተበቀሏቸው ነው ይባላል። ይህ እውነት ወይም ሀሰት ሊሆን ይችላል። እውነቱ ግን አጼ ዮሀንስ ራያን መስገበር ተስኗቸው ነበር።