Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37266
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Ethiopian Ambassador 2 Sudan ይበልጣል አዕምሮ Said:"ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ላይ ጫና እንዲያሳድር ጥሪ ቀረበ"!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 29 Aug 2022, 11:47

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ላይ ጫና እንዲያሳድር ጥሪ ቀረበ
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በዛሬው ዕለት በሱዳን ተቀማጭ ለሆኑ የመገናኛ ብዙሃን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሸባሪው ህወሓት ዳግም ስለከፈተው ጦርነት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ይበልጣል ስለ ህወሓት ፀረ-ሠላምነት የኋላ ታሪክ በዝርዝር አስረድተዋል ።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ተጨባጭ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት ወቅት አሸባሪው ቡድን የሰብዓዊ የተኩስ አቁሙን በመጣስ ከነሐሴ 18 ቀን 2014 ጀምሮ በአማራና በአፋር ክልሎች ሦስተኛ ዙር ወረራ መፈፀሙን አብራርተዋል።
በዚህ ወረራው ቀደም ሲል እንዳደረገው ሁሉ ሕጻናትን ጨምሮ የትግራይን ሕዝብ በማስገደድ በሰው ማዕበል በመዋጋት ሕዝብን ለዕልቂት እየዳረገ ነው ብለዋል።
እንደ አዲስ በወረራቸው የአማራ እና የአፋር አካባቢዎችም ሲቪሎችን በመግደልና ሕዝብን በማሸበር ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ከማድረጉ በላይ ንብረት ዘረፋ እና መሠረተ ልማቶችን በማውደም ላይ እንደተሰማራ አስረድተዋል።
አምባሳደሩ በማያያዝ ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ በዚህ አሸባሪ ቡድን ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሳይዘናጋ ከሚፈፅማቸው አረመኔያዊ ድርጊቶች እና ወንጀሎች ይቆጠብ ዘንድ አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የቅርብ ጐረቤት አገሮችም በኢትየጵያ የሚፈጠር ችግር ገፈት ቀማሽ ከመሆናቸው አንጻር የዚህን አሸባሪ ቡድን ድርጊት በማውገዝ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።