Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ኦነጉ አብይ አህመድ ኢትይጵያ ያለባትን እዳ ከ30.36 ቢሊዮን ዶላር ወደ 56.6 ቢሊዮን ዶላር አሳደገው!!

Post by Wedi » 25 Jul 2022, 15:04


ኦነጉ አብይ አህመድ ወደ ስላጣን ከመጣ በኋላ ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ከ30.36 ቢሊዮን ( በ2020 ዓም የነበር) ወደ
56.6 ቢሊዮን ዶላር (2022 ዓም) አድጓል!! ኦነጉ አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ያለባትን እዳ 3 አመታት ውስጥ ከነበብን እዳ 26 ቢሊዮን ዶላልር በመጨመር አሁን ያለብንን እዳ ወደ 56.6 ቢሊዮን አሳድጎታል ማለት ነው!!

ቢቢሲ አምርኛ ይህን አስመልክቶ የሰራውን ሙሉ ዘገባ ከዚህ ላይ አንብበው!!
********
ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ ስንት ነው? ዕዳዋን ባትከፍልስ ምን ይከተላል?

22 ሀምሌ 2022

የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣት ይዟል።

የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር።

ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ።

የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ።

እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር።


Read more https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0gy1yvdpzo