በኢትዮጵያ ፖለቲካ እውነትን መናገር ሰላም መንሳት ነው
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁሉም የሚያውቀው የዘር ተኮር ጥቃትን ቡና ላይ ማውራት ይቻላል ነገር ግን በህዝብ ፊት ይህንን እውነት መናገር ግጭትን ማባባስ ነው፤ ይህንን አባባል ተቀብሎ ነው አብይ ዘር ያተኮረ ማጥቃት አትበሉ አደገኛ፤ሬሳ ላይ ዛፍ አለመትከል ግን የጠላት ወሬ ነው እያለ አብይ ፓርላማ ፊት የሚዶሶክረው :
እንደ ኢዜማ ያለ ተቃዋሚ ነኝ ባዮች መንገስት ያመነውን ጭፍጨፋ ሳይቀር ሙልጭ አድርገው የዘር ማጥፋት የለም ብለው በመካድ የነርሱን ፖለቲካ ስትራቴጂ አድርገው ወስደውታል ፤ ህዝብ ማለት የፖለቲካ ሂሳብ ማወራረጃ ነው ፤
የጅሎች ሰብሰብ በአዴን የወከውለን ህዝብ የሚመጥን ውክልና መጠየቅ ያልቻለ የፌደራሉን ቁልፍ ቁልፍ ስልጣን አይኑ እያየ በጅምላ ያሰውሰድ ፤ በአብይ የተናቀ ፤ በሀገሩ እንግዳ የሆነ የማይረባ ድርጅት የሆነው በመሽለመጥመጥ በሺታ ነው፤ አፋር አስተዳደር ወያኔ ለጭፍጭፋቸው ህጻናት ባንዲራውን ዝቅ ሲያደርግ በአድን (በድን) በክልሉ በእንኳን ባዲራው ለተጨፈጨፉ አማራዎች ዝቅ የማያደርግ የወገብ አጥንት ያለው ብኩን አገልጋይ ነው ፤ የፊደራሉ እንኳን ቢቀር ፤ ፤ አማራ የከበበው ጠላት ባይበዛ ኖሮ አንድ ቀን መግዛት የሌለበት ድርጅት ነው፤ ምክትል ጠ/ሚኒስተሩን ቦታ እንኳን አንድ ሰው እንዳይሆን ደመቀ ሌላ ቷኮ አስገብቶ አብይ እንዲያሾፍ ያደረገው ትልቁ ስንኳፋ፡ግን የራሱን ህዝብ ለማንገላታት ማንም ክልል አይወዳደረውም
አሁን አሁን እንኳን መጀመሪያ ላይ የነበረው ወኔው ተሟጦ ስላለቀ ፤ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች ብላ የቻርተሩን ህግ ጥሳ የፈለገንውን እናደርጋለን ስትል ተቋውሞ ማሰማት ያልቻለ እንደ በግ የሚጎተን ድርጅት ቢርኖር በአድን ነው የፖለቲካ መልመጥመት ውረርሺኝ
ሁሉም የሚገርመው ደግሞ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ስለአማራ መጨፍጨፍ ለመናገር ሲሽኮረሞሙ ማየት ነው ፤ ተምረናል የሚሉ ፤ ስለፖለቲካ ሳይንስ ከኛ በላይ ሰው የለም የሚሉ በሞላ መንግስት 350 ቀናንሶ ቢሆንም ንጹሃን አማራዎች መጨፍጨፋቸውን በየቀኑ እየሰሙ እንዲህ አይደረግም ማለት ክሞጋሳዎች ጋር ቅራኔ ይከተናል በሚል ፍርሀቻ እንዳልሰሙ ሲልመጠመጡ ማየት ሲሆኑ ከዚህ አይነጽ ሎሌነት ከማየት የሚያሳምም ነገር የለም፤ ያላወቁት ነገር ቢኖር ይህ የመልመጥመጥ ፖለቲካ አማራን አቃጥሎ ሌላውን የሚያሞቅ አለመሆኑን ነው፤