Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7442
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ክብር እና ነዉር፣ ድሮ እና ዘንድሮ

Post by Naga Tuma » 15 Jul 2022, 20:25

መለከት፣ እዚህ ፎረም ላይ ስለ ነዉር የጻፍከዉን በኣድናቆት ኣንብቤ እኔም ስለ ክብር እና ነዉር፣ ድሮ እና ዘንድሮ ትንሽ ጣል ማድረግ ኣማረኝ። ስለነዉር ቀይ መስመር ከሚባለዉ በፊት ነዉ የሰማሁኝ። ዛሬ ድረስ የበለጠ የሚገባኝ ቀድሜ የሰማሁት ነዉ።

መለከት መለከት፣
ትላንት የቤቴ፣
የዛሬ ጎረቤቴ፣
የቡና ጥሪ ናፍቄቴ (ጎረቤትን ኑ ግቡ ቡና ጠጡ የሚባልበት ሃገር ነዉ ያደኩኝ)

እነዚህን አረት መስመሮች ከቋጠርኩኝ ሰንብቻለሁ። እንደገና እዚህ ኣመጣሁት።

ድሮ ከፀሎት በላይ ምን ኣለ ክብር ነበር። ኣይዴለም?

ዘንድሮ ከስራ የበለጠ ፀሎት የለም ከብር ነዉ። ኣይዴለም? ፀሎት ኣያስፈልግም ማለት ኣይዴለም። የተረጋገጠ እዉነት መናገር ክብር እንጂ ነዉር ኣይዴለም ለማለት ነዉ።

ድሮ ስደት ተከብሮ ነበር፣ ዘንድሮ ፅናት ይከበራል። አይዴለም?

በዚሁ ኣጋጣሚ ክጥቂት ሳምንታት በፊት የቋጠርኩትን ልጨምር።

ፍዳ ጠንቶባቸዉ መዉለድ እርም ይሁን ሳይሉ ከኢትዮጵያ ተነጥለዉ የኢትዮጵያን ባህል ኣምቀዉ የቆዩት የኤርትራ እናቶች እንዴት ናቸዉ? ደህና ናቸዉ? ባህሉን ኣምቀዉ መቆየታቸዉን የደርግ ዘመን እዛ የኖሩት ኢትዮጵያዊያን ከመሰከሩት የሰማሁኝ ነዉ።