Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13073
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ሰበር ዜና: ከ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያለው ልማታዊው ባለ ሃብት በቁጥጥር ሥር ዋለ

Post by Thomas H » 13 Jul 2022, 23:11

"በመጨረሻው ዘመን ሌባ በሌባ ይነሳል፡፡ ትንቢቱ ተፈፀመ፡፡"
ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ሥር ዋለ:: የአገሪቱ በጀት እሱ ቤት ውስጥ ነው የተገኘው


















በተጨማሪም በኮሚሽነሩ ቤተሰቦች ላይ በተደረገ ማጣራት፦
1ኛ - የኮሚሽነሩ ወንድ ልጅ ኢያሱ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት በተላለፈ ገንዘብ መኪና ተገዝቶለት ይህንኑ መኪና መልሶ ኤልሻዳይ የገዛው መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፤ እንዲሁም ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኤልሻዳይ ድርጅት ፀሀፊ ስም በወር 15 ሺህ ብር በተከራየው ሙሉ ጊቢ ውስጥ የሚኖር መሆኑን መረጃ ደርሶ፤ በቤቱ ውስጥ የተባለው የኮሚሽነሩ ልጅ መኖሩን ወርሃዊ ክፍያውንም ኤልሳሻዳይ ድርጅት እንደሚከፍልለት በሰውና በሰነድ ተረጋግጧል::

2ኛ- የኮሚሽነሩ ሴት ልጅ ወ/ሮ ሚኪያ ምትኩ ካሳ በኤልሻዳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጣሪ ሳትሆን በኤልሻዳይ ድርጅት ፔሮል ውስጥ ስሟ ተካቶ ለ1 ዓመት ያክል በወር አምስት ሺህ ብር ደመወዝ በባንከ በኩል ሲከፈላት እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። እንዲሁም ከኤልሻዳይ ድርጅት የባንክ ሂሳብ ብር 800 ሺህ ብር ወደ ሚኪያ ምትኩ በተለያዩ ጊዚያት ገቢ መሆኑን በሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራም በማጣራት ላይ ይገኛል::

3ኛ- የኮሚሽነሩ ባለቤት በወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ስም ከእንይ ጀኔራል ቢዝነስ ሪል እስቴት (በወኪል የማነ ወ/ማሪያም በርሄ አማካኝነት (የኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ) ከኤልሻዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ጥቆማዎች ላይም ማጣራት እየተካሄደ ስለመሆኑ

4ኛ- የኮሚሽነሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ከኤልሻዳይ ድርጅት 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር በሲፒ.ኦ ገቢ በሆነላት ብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ብቻ በተደረገ ማጣራት በኤልሻ ድርጅት እና የኮሚሽነሩ የቅርብ ጉዳይ አስፈፃሚ በሆኑ ግለሰቦችና የወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት 7 ቤቶች የገዛች መሆኑ በተጨማሪም ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ስም የተገዙ ቤቶችን በተመለከተ ሙሉ ውክልና ለኤልሻዳይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ የማነ ገ/ማሪያም ውክልና ሰጥተው የተገኙ መሆኑን ይህ ቀሪ የማጥራት ስራ የሚቀረው ቢሆንም መመሳጠር መኖሩን ያስረዳል። እንዲሁም ከእነዚህ ሰባት ቤቶች መካከል አንዱን አቶ የማነህ ገ/ማሪያም በተሰጠው ውክልና መሰረት ከወ/ሮ ኢቲኮ አጌቦ ጆሀር ለአቶ ምትኩ ካሳ መሸጡን ይህ ሽያጭ ሲፈፀም አቶ የማነ ገ/ማሪያም ሀሰተኛ መታወቂያ፣ ሀሰተኛ ፎቶ መጠቀሙን ተረጋግጧል።

5ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ሚኖሩበት ቤት ቁጥር በማስመዝገብ እና የሌላን ሰው ፎቶግራፍ በመጠቀም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በስማቸው አሰርተው የተገኙ መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል፣ ቤተሰባዊ ግንኙነቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ 18 አመት ባልሞላው ልጅ መሀመድ አብዲልፈታህ አብዱላሂ በተበለ ስም ከእንይ ጅኔራል ቢዝነስ ሪል እስቴት ከኤልሳዳይ ድርጅት ሂሳብ ወጭ በተደረገ ገንዘብ በብር 8,306,737.75 የቦታ ስፋት 388.75 ካሬ ሜትር የሆነ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ የተገዛ መሆኑን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል::