Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ሱሌማን አብደላ

Post by Revelations » 08 Jul 2022, 01:35

ሱሌማን አብደላ | July 7, 2022

አሜሪካ ሞት የበዛደሁ እኛ መሞት የለብንም። ዋናው ጥያቄ የሞትን ብዛት በቀመር አስልቶ መቅረብ አይደለም። ታንክም ባንክም በራሪ አየርም ኢንተለጀንስም የተቆጣጠረ የአንድ የአገር መሪ በፍጹም አገሪቱ ላይ የሞቱትን ሰዎች ከነ ሱማሌያና ከነ አሜሪካ ጋር አባዝቶ ወንጀሉን ማሳነስ አይችልም። ነውርም ነው። የመረጠውን ህዝብ ሲቪል ገበሬን እያስበላ ድክመትን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ወደ ሌሎች አገሮች ሞት ብዛት ህዶ ቀመር መስጠት የመሪነትን ማንነት የሚያሳጣ ነው።

ወያኔኮ ስልጣን ይዞ በዚህ ቁጥር ልክ ንፁሀን ዜጋ አልተጨፈጨፈበትም። አንድ ወለጋን ነፃ ማውጣት አቅቶን አሜሪካ የሞተው ከኢትዮጵያ ሲሰላ የኢትዮጵያ ትንሽ ነው ብሎ ማለት በሰው ነፍስ መቀለድ ነው። አጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተጠየቁትን ጥያቄ አለዝበው ለማለፍ የሄዱበት ቀመር በህዝብ ዘንድ ያላቸውን አመኔታ የሚቀብር እንጅ አንድም ነጥብ ጥለው የሚያልፉበት አይደለም። መሆን የነበረበት ከአሜሪካ ሞት ጋር ቀመር መስራት ሳይሆን ቆሞ ይቅርታ በአቅም ማነስ በአመራር የውሳኔ እንዝላልነት ዜጎቻችንን አተናል ሁለተኛ አይለመደንም ብሎ ቆሞ ይቅርታ መጠየቅ ነበር የሚሻለው።

ከአሜሪካ አንፃር ከሱማሊያ አንፃ የወሎን እናትና አባቶች፣ ህፃንና ወጣቶች ሞት በዚህ መልኩ መቅረብ የለበትም። ታንክ ይዤ አየር ሀይል ይዤ ወታደር ይዤ 120 ሚሊዮን ህዝብ ከጎኔ አሰልፌ የተገደሉትን ዜጎች ሞት እውቅና ሰቶ ከአሜሪካ አንፃር እየተባለ ለስሌት ማቅረብ የመጨረሻ ነውር ነው።
.
እርስዎኮ የተቀመጡበት ቦታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሁለተኛው የውሳኔ መስጫ ቦታ ነው። በንግግራቸው ውስጥ ገዳዩ ሸኔ አሉ። ሸኔ የሚመራው እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ነው ብለዋል። ያው አልሸባብ ሶማሊያ ላይ ስለሆነ መቀመጫው እያሉ ሲያለዝቡ ነበር አመራራቸው ውስጥ ያለውን ጨፍጫፊ ቡድን ለህግ ማቅረብ ለምን ፈሩ።

4 አመት ሙሉ አንድ ዞን ላይ ይሄ ሁሉ ህዝብ እየተጨፈጨፈ አይደለም አንዲት ብልሹ ካሳየ መጀመሪያ መጠየቅ ያለበት የክልሉ መንግስትና የፀጥታ ሀላፊው ከዛም እርሰዎ ነዎት። ተጠያቂነትን ለማጥፋት ሞትን በሌላ አገር የሞት ብዛት ጋር እያወዳደሩ በቁልስ ላይ በርበሬ ሲነሰነሱ ነው የዋሉት።

መንግስት ሆነው አካባቢው ላይ ያለውን አማፂ ከቻሉ በሰላማዊ ድርድር መፍታት ካልተቻለ በሀይል ሚዛን በልጦ በማሸነፍ ልክ ማስገባትን ትተው ለሞቱት ችግኝ እንተክላለን አሉ። መሪ ሆነው ለተገደሉ ዜጎች መልሳቸው ይሄ ከሆነ ከዚህ በላይ አሳፋሪ ንግግር የለም። ችግኝ ፍትህ አይሆንም። ችግኝ ገነት አያስገባም። የሞተ ሰው ጥላው በምድር ላይ የሰራቸው ጥሩ ስራዎች እንጅ ችግኝ አይደለምደ
.
እናም አሁን አሁን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይዘዋቸው ለህዝብ በሚሰጡት ማብራሪያ በህዝብ ዘንድ ያላቸው አመኔታ እየወረደ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሦስት መሰረት አለው። ትግራይ አማራና ኦሮሞ ነው። አሁን ያለው ብልፅግና ግን መሰረቱን እየነቀለ ነው። ነገ ይሄንን ህዝብ ለአመፅ አደባባይ ቢጠሩት ይወጣል። አማራም ይሁን ትግራይ ኦሮሞም ይሁን ሱማሌው በመንግሥት ላይ ያለው አቋም አንድ አይነት ነው።

ይህንን ለማየት የሦስቱም ብሔር አቀንቃኞች አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር በእርስዎ መንግስት ላይ የሚሰነዝሩት ተቃውሞ ተመሳሳይ ነው። የፖለቲካ ፍላጎትና ልዩነታቸው ይለያያል እንጅ በብልፅግና መንግስት ላይ ያላቸው አቋም ግን አንድ ነው።

የእርሰዎ መንግስት በዚህ አቋሙ ከቀጠለ (ከዲፕሎማሲ ነፃ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ነፃ ከሰላም ማስፈን ነፃ ከሉአላዊነት ማስከበር ነፃ ህዝብን አንድ አድርጎ ከመምራት ነፃ በሌብነት የታከነ ስረአት ሆኖ ከቀጠለ አደጋው እየከፋ እንጅ እየቀነ አይሄድም። ጠቅላይ ሚኒስቴር ከተጠቀሙበት ይሄ ሀሳብ በህዝቡ ዘንድ ቁልጭ ብሎ እንደሚታይ አምነው መፍትሔ እንዲፈልጉ ይጠቅማቸዋል እንጅ አይጎዳቸውም። አክቲቪቲቪዝም ማለት ጭፍን ደጋፊም ጭፍን ተቀዋሚም መሆን አይደለም። በህዝብ ዘንድ ያለውን ጥሬ ፍላጎት ለይቶ ማሳወቅና ማንቃት ነው። የተረዳ ይጠቀምበታል።

Post Reply