Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13077
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Watch: Shocking: በወያኔ ዘመን ወደ አሜሪካ የተሰደዱት አማሮች ቁጥር በጣም ያስደነግጣል

Post by Thomas H » 06 Jun 2022, 20:49

200 ሚሊዮን አማሮች ተሰድደዋል Forward to 1:30


"በሰሜን አሜሪካ ብቻ ከ 200 ሚልዮን በላይ ያማራ ስደተኞች ይኖራሉ" - አንድ ምሁር በአማራ ቲቪ ላይ እንደተናገረው
---
እኔ የምለው አቆጣጠር ተቀየረ ወይስ የማጋነኛ ፋከትር (exaggeration factor) 1000 ሆነ። ባለፈው 20 ሚሊዮን ዶላር የሚለውን 20 ቢልዮን በለው ዘገቡ። አሁን ደሞ አንዱ ተነስቶ በሰሜን አሜሪካ ብቻ ከ 200 ሚልዮን በላይ ያማራ ስደተኞች ይኖራሉ፣ ከነዚህም ወስጥ 63%ቱ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛም በላይ ያላቸው ሲሆን አማካኝ ደሞዛቸው 53,000 ዶላር ነው ብሎ ትንተና ሰጠ። የሚቆጣ ወይም የሚያርም የለም እንዴ ማንም እየተነሳ የሌለ ቁጥር እያነሳ እየጠቀሰ ሕዝብ ሲያደናግር።
እንግዲህ ልብ ይበሉ የአሜሪካ አጠቃላይ ሕዝብ ብዛት ወደ 330 ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን እንደዚህ ሊቅ ትንተና ከሆነ ከ60% በላይ የአሜሪካ ሕዝብ አማራ ነው ማለትነው። ይሄ ታዲያ አያሳስርም። አሜሪካኖችስ ይህን ቢሰሙ የሚሳቅበት ሕዝብና ሐገር አይደለም። መረጃዎች የሚያመለክቱት በአሜሪካ ዉስጥ ያለው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ስደተኛ ቁጥር ወደ ሁሉት መቶ ሃምሳ ሺገደማ የሚጠጋ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በብሔረሰብ ስብጥር የሚያሳይ መረጃ ግን የለም። ከየት አምጥቶ 200 ሚሊዮን አማራ በሰሜን አሜሪካ ይኖራል እንዳለ ለኔ በፍጹም ሊገባኝ አልቻለም። በተጨማሪም ተንታኙ እንዳለው ሳይሆን መረጃዎች የሚያመለክቱት በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ከ20% እንደማይበልጡ ነው። የአማካኝ ደሞዝንም በተመለከተ የተናገረው ምንም ማስረጃ የምይገኝለት ነው።

Source:
https://www.facebook.com/search/top?q=s ... %20guangul
Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Must Watch: Shocking: በወያኔ ዘመን ወደ አሜሪካ የተሰደዱት አማሮች ቁጥር በጣም ያስደነግጣል

Post by Sam Ebalalehu » 06 Jun 2022, 21:15

ማፈሪያ። መቁጠር የማይችል ደደብ ለምንድን ነው የተጋበዘው ለውይይት? እነደዚህ አይነት ሙልጭ ያለ ደደብ አንድ ብሄርን ወክሎ ሲናገር መስማት ያሳምማል።

Post Reply