Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum



Union

Re: ታላቁ የግንቦት ምድረ ከብድ አቦ ንግስ 10 ቀን ብቻ ቀረው !!

Post by Union » 01 May 2022, 21:49

አንቺ ሴት ብር እያልሽ ተጣላሽ ከሰው
ብርሽን አስማምቶ አብይ ወሰደው
ፓርላማ አስገብቶ አስለፈለፈው

ለብርሽ ከሞትሽ አይሰማሽም ጌታ
ሁለት ያጣ ሆነሻል የማታ የማታ

Selam/
Senior Member
Posts: 17957
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ታላቁ የግንቦት ምድረ ከብድ አቦ ንግስ 10 ቀን ብቻ ቀረው !!

Post by Selam/ » 01 May 2022, 23:07

Horus - Where exactly is this church located?
Horus wrote:
01 May 2022, 20:57





Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ታላቁ የግንቦት ምድረ ከብድ አቦ ንግስ 10 ቀን ብቻ ቀረው !!

Post by Horus » 01 May 2022, 23:38

Selam/
ምድረ ከብድ በደቡብ ሶዶ ነው ያለው ። ቡዬ ከሚባለ የሶዶ ዋና ከተማ ጥቂት ደቂቃዎች በምስራቅ ነው ያለው ። እኔ ከአያቴ ሌላ ቅድመ ቅመ አያቶቼ ሁሉ የተቀበሩት እዚያ ነው ። ገዳሙ የተሰራው በ1460 አም ነው ። ቅዱስ አቦ (አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) ግብጻዊ ነበሩ። ዝቋላ አቦን፣ ምድረ ከብድ አቦ፣ አዳዲ ማሪያምን፣ ዳዮ አቦና ሌሎች ብዙ ያገራችን ገዳሞች ያቆሙ ትልቁ የሃይማኖት አባታችን ናቸው ። እስከ አርባ ምንጭ ድረስ ያስተማሩ ናቸው። እንደ ምታየው ግራኝ መሃመድ ዙሪያችን ሁሉ ሲያሰልም ያልቻለው አንድ ሕዝብ የዚያ አካባቢን ነው። አያታችን ሲነግረን የዚያ አካባቢ ዋሻ ሁሉ የተቆፈረው በግራኝ ዘመን ነው። ለምሳሌ ምደረ ከብድና ዝቋላ የሚያገናኝ ዋሻ ነበር ይባላል። ከዝቋላ ብዙ አይርቅም ምድረ ከብድ ላይ ቆመህ መላው ዝዋይን በቅርብ ርቀት ታየዋለህ ። ቦታው ከባድ የውሃ ችግር ስለ ነበረው ብዙ አልለማም ነበር። አሁን ብዙ ትኩረት እያገኘ ነው በጣም ደስ ብሎኛል ። ቅዱስ አቦ የተቀበሩት እዚያ ነው ። የግንቦት ንግስ ለዕረፍት መታሰቢያቸው ነው የሚነግሰው። ሌሎች ብዙ አቦዎች አሉ ፣ያው በጥቅምት አቦ በመስቀል መጨረሻ ቀን በጥቅምት 5 ነው የሚነግሱት ። ትልቅ የፈረሰ ጉግስ ቀን ነው። ምድረ ከብድ ማለት በክስታኔኛ ክቡር ምድር ማለት ነው ።

Post Reply