By Finfinne Times
በነገራችን ላይ TDF አፋር ክልል ላይ የያዛቸውን ስትራቴጂካዊ መሬቶች ለቅቆ ማፈግፈጉ የፖለቲካው ሜዳ መተማመንን የሚያሳይ አንዱ ክስተት ነው።
TDF ያፈገፈገበት አንዱ ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ለማመቻቸት ቢሆንም .. ውሳኔው ግን ከወታደራዊ ግምገማና ስጋት አንፃርም ይመዘናል።
ምክንያቱም ከአብኣላ መቀሌ በመኪና ጉዞ የሚፈጀው 1:30 ብቻ ገደማ ነው። ታዲያ የትግራይ ሰራዊት ድንበሩ ውስጥ ሆኖ የሚመጣ ጠላትን ከመጠበቅ ወደፊት በመሄድ ስትራቴጂካዊ ቦታ ይዞ ቢጠብቅ የተሻለ አስተማማኝ ሁኔታ ይፈጥር ነበር።
ነገር ግን TDF የሰብዓዊ እርዳታ መግባቱ ላይ ማጠንጠኛውን አድርጎ ከወታደራዊ ስትራቴጂ ጋር የተያያዘ ውሳኔ አድርጓል።
ሁለት ነጥቦች መረሳት የለባቸውም ..... የመጀመሪያው የፌደራሉ መንግስትና TDF ከስምምነት ላይ የደረሱት የሰላም ውል ሰበዓዊነት ላይ ያጠነጥናል .. ስለዚህ የፖለቲካ ወይም ሌሎች ስምምነቶች ገና አልተነኩም።
ሁለተኛው ደግሞ ... በፖለቲካው ሜዳ መተማመን ባለብህ ሰአት ትተማመናለህ .. የምትተማመነው አንተ ካለህ አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ብሎም ከጠላትህ አንፃር የተሰላ ነው።
አንዳንዱ ብልፅግና አይታመንም ፣ አብይ መሰሪ ነው ፣ ምናምን ማለት ፖለቲካ ይመስለዋል። ነገር ግን የአብይ አለመታመን ሳይሆን ዋናው ነጥብ ያንተ የሀይል ሚዛን ፣ አቅም ፣ ስትራቴጂ ፣ የፖለቲካህ መንገድ ፣ ወታደራዊ ሀይል ፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነትህ ወዘተረፈ ነው።
እነዚህን አማራጭ ካርዶች እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ካወክ ፣ ከጠላትህ አንፃር ማስላት ከቻልክ .. በፖለቲካው ሜዳ አይደለም ከአብይ ጋር ከሴጣን ጋር ልትተማመን ትችላለህ።
ምክንያቱም አንተ የምትቆመው እራስህን ተማምነህ በአቅምህ ልክ ተደራጅተህ እንጂ .. በባላንጣህ እምነት ላይ ተንጠልጥለህ አይደለም።
አንዳንዱ አክቲቪስት ፖለቲካን የቤተሰብ ጉዳይ አድርጎት "አላምንም አትታመንም" .. ሲል ያስቀኛል ... ባሻዬ እየተማመንን !!
Finfinne Times
https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155
