Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ሁሉም ነገርን እንድንናገር ይፈለጋል እንዴ?" ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

Post by sarcasm » 23 Apr 2022, 08:27

እኔ ጋዜጠኛ ብሆን ፊልድ ማርሻሉን የምጠይቀው

የሰሞኑ ከህወሓት ጋር ያላችሁ ስምምነት በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እያመጣ ነው። አሜሪካን ሆነች የተለያዩ የአለም ሀገራት አድንቀውታል። በቀጣይ ከጀነራል ፃድቃን ጋር የት ለመገናኘት አስባችኃል ? ስምምነቱ ወደ ወረቀት የሚወርደው መቼ ነው ? ... እያልኩ ነበር የምጠይቀው።

ብሬም .. አዎ በጣም ጥሩ እየሄደ ነው ይልና 🤔 በቅፅበት ምንድነው ግን የጠየከኝ ? ሁሉም ነገርን እንድንናገር ይፈለጋል እንዴ ? ብሎ ይቀውጠው ነበር 😂

ተሸንፈናል እንድንል ይፈለጋል እንዴ ? ሁሉም ይነገራል እንዴ ? አለ ፊልድ ማርሻሉ በአንድ ወቅት 😊 .. በእርግጥም ሁሉም አይነገርም።
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...