Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኬይርነት ፍልስፍና እና የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የጋራ ካልቸር መሰረት!

Post by Horus » 21 Apr 2022, 14:54

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መደመር የሚባለውን ሃሳቡ ሲያብራራ የጠቀሳቸው አንዳንድ መሰረታዊ (ፋውንዴሽናል) ጽንሰ ሃሳቦች አሉ። ለምሳሌ ብሄራዊ አንድ ወጥነት (ናሽናል ኢንተገሬሽን)፣ የኢትዮጵያዊያን ወንድማማችነት (ፍራተርኒቲ)፣ ሌሎች ከዚህ አነስ አነስ ያሉም የህብረትና የትብብር ጽንሰ ሃሳቦች አንስቷል።

እኔ ለብዙ አመታት ብዙ ግዜ እንዳነሳሁት በጎሳ የተለያዩት ኢትዮጵያዊያን አንድ የኢትዮጵያ ካልቸር መሰረት ናቸው የሚባሉትን እሴቶች (ቫልዩስ) ለይተን በውል ማወቅና ማዳበር አለብን ። ከዚህ ቀደም ያልኩትን ልድገመው።

አንድ፣
የካልቸር አንዱ መሰረት እምነት ነው ። ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ሃይማኖቶች አሏቸው፤ ነገር ግን ሁሉም በአንድ ፈጣሪ ያምናሉ። ስለዚህ እምነት በሚመለከት ሁሉም ጎሳዎችን አንድ የሚያደርጋቸው በአንድ ፈጣሪ ማመናቸው ነው። ይህ የመጀምሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ እሴትና የኢትዮጵያ ካልቸር መሰረት ነው።

ሁለት፣
ሌላው የጋራ ካልቸር መሰረት ወንድማማችነት ነው። በአንድ ፈጣሪ የሚያምኑ ሁሉ ሰውን የፈጠረ አንድ ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ። ስለሆነም ከአንድ ፈጣሪ፣ ከአንድ አባት የተፈጠሩ ሁሉ ወንድማማቾች ናቸው ። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዘጠና ጎሳ ቢከፋፈሉም የአንድ ፈጣሪ አባት ልጆች ወንድማማቾች ናቸው። ስለሆነም ወንድማማችነት ሁለተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ እሴትና የኢትዮጵያ ካልቸር መሰረት ነው።

ሶስት፣
ሌላው የጋራ ካልቸር መሰረት እኩልነት ነው። ጎሳዎች ወይም ስብስቦች በቁጥር፣ በስፋት፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በሃብት፣ በስልጣኔ ይለያያሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጎሳው ምንም ይሁን ምን በአንድ ፈጣሪ የተፈጠረ ስለሆነ ግለሰቦች ሁሉ እኩል ናቸው፤ ግለሰቦች ሁሉ እኩል ነጻነት እና እኩል መብት አላቸው ። ይህን የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እኩልነትን የሚበልጥ ወይም የሚልቅ ሌላ ሃይል የለም፤ ጎሳዊም ሆነ ህጋዊ። ስለሆነም የግለሰቦች እኩልነት ሶስተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ እሴትና የኢትዮጵያ ካልቸር መሰረት ነው።

አራት፣
ሌላው የጋራ ካልቸር መሰረት የስራ ክቡርነት ነው። የሰው ልጅ ከተፈጥሮው ባሻገር እራሱን በስራው የሚለውጥ ፍጡር ነው። ሰው ሰራሽ የሚባለው አለምን ሁሉ የሰራ ፣ የፈጠረ ፣ ያሻሻለ፣ ያበላሸ ሰው እራሱ በስራው ነው ። ስራ የካልቸርና የስልጣኔ ምክያት ነው ። ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ጎሳው ምንም ይሁን ምን የመጨረሻ ምንነትና ማንነቱ የሚወሰነው፣ የሚገለጸው በስራው ነው ። በስራ ክቡርነት የማያምን ክቡር ሰው ሊኖር አይችልም። ስለሆነም የስራ ክቡርነት አራተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ እሴትና የኢትዮጵያ ካልቸር ነው ።

እነዚህን አራት ግዙፍ የካልቸር መሰረቶችን ሰብስቦ የያዘው ለዘመናት የሰው ልጅ የሚፈላሰፍበት አንድ ጽንሰ ነገር በፍጥረት ሁሉ መልካምነት፣ በአለም ሁሉ ደህንነት፣ በተፈጥሮ ሁሉ ጤነንትና ሙሉነት ማመንና መተግበር ነው ። እሱም የፍጥረት ሁሉ ኬይርነት ወይም The Ethics of Well-Being of All ይባላል። ባሁን ወቅት የሰው ልጅ ንቃተ ህሳቤና ስነምግባር ደርሶበታል ከሚባለው የፍትሃ ንደፈ ሃሳብ የመጨረሻው ከፍተኛ ደረጃ ነው።

በዚህ የሰነምግባር እምነትና ፍልስፍና መሰረት እንሰሶች ልክ እንደ ሰው ደስታና ስቃይ ይሰማቸዋል፣ እጸዋቶች ልክ እንደ እንሰሳ እንክብካቤ ይፈልጋሉ፤ አየር፣ አፈር፣ ዉሃ ፣ ፍጥረት ሁሉ ደህንነት ይፈልጋል የሚለው ልሂቅ ህሳቤና ካልቸር ነው ። ይህን ስነምግባር ነው ኬይርነት የምንለው!! ኬይርነት ለኢትዮጵያ !!!

Last edited by Horus on 21 Apr 2022, 15:40, edited 1 time in total.


Abere
Senior Member
Posts: 15502
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኬይርነት ፍልስፍና እና የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የጋራ ካልቸር መሰረት!

Post by Abere » 21 Apr 2022, 15:36

ሆረስ፤

ማንኛውም ልዑላዊ አገር ብሄራዊ ባህል አለው። ኢትዮጵያም የጎጥ እና የጎሳ ስርወ መንግስት አቀንቃኝ ወያኔ እስከ መጣ ድረስ ይህ አስተሳሳሪ ገመድ ሰንሰለት የሆነው ብሄራዊ ባህል ነበርት። ይህ የጋራ እሴት የሆነው ብሄራዊ ባህል ነው ምን እንኳን የጎሳ ፓለቲከኞች ሊያጠፉት ቢሞክሩም እየተንገዳገደ ይህን 30 አመታት ያቆየን። ይህ ብሄራዊ ባህል ዛሬ በትግራይ ተሟጦ አልቆ የለም፥ ኦሮምያ ተብሎ በሚጠራው የጓሳ ክልልም እርሾው እንጥፍጣፊ እየጠፋ ነው። አሁን ይህን ህብረ-ሰረሰር (central nervous system) የሆነውን ብሄራዊ ባህል እንድያቆጠቁጥ የምናደርገው። መደመር ትርጉም የሚኖረው መዋሃድ ሲኖርበት ነው። መዋሃዱን የሚያፋጥን በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው (catalyst) አፋጣኝ አመራር ያስፈልገል። ትርጉም ያለው እርምጃ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች። ህዝብ ተቸግሮ መሪዎች ነን ለሚሉ ተመሪዎች አርዐያ እየሆነ ነው። አሁን ቄሱ በሀረር በሙስሊሞች መካከል ተገኝተው የሚይስተምሩት በጎሳ ፓለቲከኞች ህዝብ ስለተሰቃየ ነው። ቤተ-ክርስቲያን መስጊድ ተቃጥለዋል ምዕምን ታርደዋል። በተለይ በዚህ 4 አመታት ውስጥ። ውጤቱ ሲፈተሽ ትርጉም ያለው ዕርምጃ አልተወሰደም። ክልል እየተዋለደ ነው፥ ፓርላማው ያው የመለስ ዘመን ነው በጥባጩ ኢ-ህገመንግስት እንደላ ነው። የተደመረው ሃይል ሊያጠፋው አልቻለም። ምን ይሻላል።በሌላ መልኩ ወያኔዎች በውዥንበር ተጠቃሚ ለመሆን እይተሯሯጡ ነው። ህዝብ አብይን አህመድን እያወገዘ ባለበት እነርሱም እንደማናውቃቸው ሁነው አብረው ያወግዛሉ። ዐብይ አህመድ ዜሮ ተጨባጭ ውጤት በማምጣቱ የመደመር ቀመሩን ዜሮ ነው የሆነው እስከ አሁን።
ምን ይሻላል?

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኬይርነት ፍልስፍና እና የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የጋራ ካልቸር መሰረት!

Post by Horus » 21 Apr 2022, 15:49

አበረ፣
ችግሮቹን ሁላችንም እናውቃቸዋለን ። ምን ይሻላል? ብለሃል! አንዱ የመጀምሪያው የመፍትሄ ሃሳብ ሁሉም ጎሳ የኔ የሚለው የኢትዮጵያ ወጥ ካልቸር መፍጠር ነው ። ያንን ነው ከላይ ያሳየሁት ። ኬይር!

Post Reply