Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጉራጌ ክልል ግንድ

Post by Horus » 14 Apr 2022, 01:56

ቅርንጫፍ አለ ግንድ አይበቅልም። ግንድ የሌለው አዲስ ትውልድ ሙጃ ነው። ባህል የሌለው ዘመናዊነት አባት የሌለው ወፍ አራሽ ኩበት ነው። ጉራጌ ክልል መሆኑ የመቼ ጉዳይ ነው። የጥንቱ ጉራጌ፣ የዛሬው ጉራጌም ሆነ የነገው ጉራጌ ሰብስቦ አንድ አድርጎ፣ አንድ ግዙፍ ዝግባ፣ አንድ ግዙፍ ዛፍ፣ አንድ ውብ አበባ አድርጎ የያዘውና የሚይዘው የጉራጌ ሴራ ነው። የዚህ ሴራ ፈጣሪና ጌቶች የጉራጌ ባሊቅ፣ የጉራጌ ጉርዛዘ፣ የጉራጌ ሰነቻዎች፣ የጉራጌ ሽማግሎች ናቸው ።

ዘመናዊ ጉራጌ፣ የጉራጌ ራስ ገዝነት በሉት የጉራጌ ክልል መንግስት የሚቆመው በማንኝውም የዘመኑ ፖለቲካ ካድሬ ላይ አይደለም! የጉራጌ ባሊቆች፣ የጉራጌ ጉሩዎች፣ የጉራጌ አባቶች ሴራ ላይ ነው የዘመናዊ ጉራጌ ስርዓት የሚቆመው! የመላ ጉራጌ፤ በቤተ ጉራ ያለው፣ በመላ ኢትዮጵያ ተዘርቶ ያለው፣ እና በመላ አለም የተበተነው ዲያስፖራ ጉራጌ ሁሉ እንደ አንድ ግንድ ቅርንጫፍና ቅጠል ሰብስቦ አንድ የሚያደርገው የጉራጌ ባህላዊ የሴራ ሸንጎ ነው! ያ ነው የጉራጌ ጉባኤ !! እሱም የጉራጌ ሴራ ጉባኤ ይባላል። ኬይር ዬሁን!!!

Last edited by Horus on 14 Apr 2022, 02:27, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጉራጌ ክልል ግንድ

Post by Horus » 14 Apr 2022, 02:25

በጉራጌ አባቶች ባህል አንድ በምድርና በሰማይ መካከል በህዝብና ህዝብ ሆነ በሰውና በሰው መሃል ለተነሳ ግጭት ወይም ችግር ከተራ ጠብ እስከ ነፍስ ግድያ ላሉ ግጭቶች ሁሉ የጉራጌ ሴራ ባሊቆች (ሽማግሎች) ከ3 ግዜ በላይ አይሰበሰቡም!!! በጉራጌ ሴራ ማንኛውም ችግር በ3 ጉባኤ ይፈታል!! ይህ መሰል እጅግ ሃያልና ጥልቅ ስልጣኔ ነው በዛሬ የካድሬ ድንቁርና ተተክቶ የመስቃንና ማረቆ ግጭት ላይ ካድሬዎች 28 ግዜ ተሰብስበው ያልቻሉትን የጉራጌ ሽማግሎሽ የፈቱት!!! ይህ ስርዓት ነው ሙሉ በሙሉ መመለስ ያለበት !! ጉራጌ በስሜትና በወጣትነት አፍላ በሚፈሉ ጎረምሶች አትመራም፤ በዊዝደምና ልምግ በከበሩ ባሊቆች ተመርታ ወጣቱ ትውልድ የዚያ ዊዝደምና ብልሃት ሃይልና ነዳጅ ጉልበት ይሆናል ! ያ ነው ሴራው፣ ያ ነው ስርዓቱ !! ኬርይ ዬሁን !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጉራጌ ክልል ግንድ

Post by Horus » 14 Apr 2022, 02:43




Post Reply