ሦስተኛው አብዮት በኢትዮጵያ ሊፈነዳ ነው። አምላክ አብዮቱን መልካም ገድ የያዘ ያድርገው።አሜን!
የመጀመሪያው አብዮት የአርሶ አደር ባለገር ገበሬውን እንባ አለብስም እምብየው እኔ የባለባቱ ወገን ነኝ ብለው በድሃ ገበሬው ጫንቃ ላይ ሲቀማጠሉ የነበሩትን ዐጼ ኀይለስላሤን ከመንበረ ዙፋናቸው አሽቀንጥሮ የጣለው ነው። ይህ አብዮት ብዙዎችን በልቷል። መልካም አጋጣሚ ተፈጥሮ በስግብግቦች ምክንያት መጥፎ አጋጣሚ ሁኖ በታሪክ አለፈ።
ሁለተኛው አብዮት የትግራይ የጎሳ ስርወ-መንግስት ወይም በተለምዶ ህወሓት/ወያኔ ተብሎ የሚጠራውን የጎሳ መዥገር ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ ነቅሎ ጥሎ ያባረረው ነው። ይህ ዐብዮት የ27 አመታት የማያቋርጥ የህዝብ ትግል በተለይም የአማራ እንድሁም ዘግይቶም ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ በዋናነት ያመጡት አብዮት ነው። የጎንደር እና የወልድያ ወጣቶች ትግል በተለይ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። ወያኔ ተስፋ እንድቆርጥ ምክንያት የሆኑ ፋናዋጊ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ዙሪያ ቄሮ ወጣቶችም የተሰካ ተሳትፎ አድርገዋል። ይህም የአገሪቱ አለመታደል ባህል እና ልማድ ሁኖ የበግ ለምድ ባጠለቁ ኦነጎች ተነጥቆ የኢትዮጵያን ህዝብ በታሪክ ታይቶ እና ተሰምቶ ከማያልቅ ውርደት እና ዕልቂት አስገባት - ለምለሟ ኢትዮጵያ ማለታችንን አቁምም ቄራዋ ኢትዮጵያ እያልን ነው። የበግ ለምድ ያጠለቁት የኦነግ ኦሮሙማ ስርወ-ጎሳ በ3 አመታት ውስት ገምቶ እና በስብሶ ያ ከህዝብ ፍቅር እና ድጋፍ ያገኝ የነበረው ጠፍቶ ብዙዎች አፍንጫቸውን ቆንጥጠው ከበሰብሰው ስርዐት እየራቁ ነው።
ሦስተኛው አብዮት የኦሮሙማ የጎሳ-ስርወ መንግስት ላይ በቅርቡ የሚፋፋም መሆኑ ግልጽ ነው። የኦሮሙማ የጎሳ ስርወ መንግስት በተለየ መልኩ የትግራይ እና አማራ ህዝብን ረቂቅ እና ስውር በሆነ መንገድ በማሰቃየት በየተራ በመፍጀት አንዱን በአንዱ ላይ በማነሳሳት የወደቀውን የወያኔ ከንቱ ትርክት እንደ ሚጠቀመው አድማጭ በመቀያየር ኑሮን ምድራዊ ሲኦል አድርጓል። ብዙሃኑ ትግሬ በተሳሳተ የወልቃይት-ሁመራ እና ራያ ትርክት እና ስርቆት ተማርኮ ዘላቂ ጥቅሙን ረስቷል። ይሁን እንጅ ውሸት እና ስንቅ እየዋለን ሲያድር ይቀላል ነው እና ሁመራ-ወልቃይት እና ራያ የትግራይ እንዳልሆነ ብዙዎች እያመኑ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ ትግራይ ሙሉ ተጣቃሚ የሚሆነው በኢትዮጵያ እንጅ በወረዳ እና አውራጃ አለመሆኑን ትምህርት እየሆነ የመጣ ይመስላል -ከአንዳንዶች እንደ ሚሰማው። ይህ ማለት ትልቁን ምስል ትግሬዎች ዘግይተውም ቢሆን ተረድተዋል - ምንም እንኳን በጎጠኛው ወያኔ ግዞት ስር ቢሆኑም። በሌላ መልኩ በግምት 7 ሚልዮን የሚሆነው የአድስ አበባ ህዝብ በቀጥታ የኦሮሙማ የጎሳ -ስርወ መንግስት ሰለባ ነው። ዛሬ ቅድም አያቱ አዲስ አበቤ የሆነ የአድስ አበባ ወጣት ስራ እና መኖሪያ አጥቶ ከባሌ እና ከአሩሲ አዳሩን ገስግሶ የገባ ኦሮሙማ ኦነግ የቢሮ እና የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንድሁም ባለ ስልጣን ነው። ታዲያ ይህ የታመቀ በደል ሊፈነዳ እና አብዮቱም ኦሮሙማን ሊበላ እንደሚችል ግልጽ ነው። ጸሎታችን ሦስተኛውን አብዮት መልካም ገድ ለአገራችን ያምጣልት ነው።