ሀፍረተ ኢትዮጵያ የነጃሺ ቀን በዱባይ ማዕከል አከበረች
"የነጃሺ ቀን" አገራችን በምትሳተፍበት ኤክስፖ 2020 ዱባይ ማዕከል በዛሬው ዕለት ተከብሯል።
በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ግንኙነትን እንዲሁም በእስልምና አስተምህሮ ኢትዮጵያ ያላትን ቦታ የተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ በኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ ምሁሩ ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ቀርቧል።
ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት በተባበሩት አረብ ኢምሬት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ እስልምናም ይሁን ሌሎች እምነቶች የሰው ልጆች በሰላም እና በአንድነት ተሳስበው አብረው እንዲኖሩ የሚያስተምሩ መሆኑን አውስተው ኢትዮጵያም የሁሉም እምነት ተከታዮች በጋራ የሚኖሩባት አገር መሆኗን ገልጸዋል።
በአገሪቱ ሰላም እንዲሰፍንና ልማት እንዲረጋገጥ የሁሉም እምነት ተከታይ አባቶችና አዋቂዎች ተከታዮቻቸውን እንዲመክሩና እንዲያስተምሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ስለ እስልምና እና ወደ ኢትዮጵያ የገባበትን ታሪካዊ ሂደት እንዲሁም ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጋር ስላላት ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ የእስልምና እምነትን በመቀበል ከዓለም አገራት ቀደምት መሆኗን፣ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተከታዮቻቸውን በመካና በአካባቢው ይደርስባቸው የነበረውን ግፍና እንግልት ለመከላከል ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአረብና ሙስሊም አገራት ጋር ያላት ግንኙነት በቋንቋ፣ በባህል፣ በኢኮኖሚና ንግድ፣ በተፈጥሮ ሀብት መጋራት እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የተሳሰረ መሆኑን በተመለከተም ገለጻ ማድረጋውን በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ከተለያዩ አገራት የተውጣጡት ተሳታፊዎች ለተደረገው ማብራሪያ አመስግነው ኢትዮጵያ ከእስልምና እምነት ጋር የቆየ ታሪክ እንዳላት መገንዘብ መቻላቸውን ገልጸዋል።
39የነጃሺ ቀን በኤክስፖ 2020 ዱባይ ማዕከል ተከበረ
********************

Please wait, video is loading...