Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል" በአለማቀፍ መድረክ አግኝቶ የጨበጣቸውን ሁሉ እንደ ዲፕሎማሲ ድል መቁጠሩ የሚነግረን ነገር ብዙ ነው።

Post by sarcasm » 19 Feb 2022, 10:26

"ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል"

ብራሰልስ በተደረገው ስብሰባ፥ የራሱን ፎቶ በመለጠፍ አብይ አህመድ በብቸኝነት እየመራ ነው።

በሁለት ቀናት ውስጥ እስካሁን ድረስ 38 ፎቶዎቹን ለጥፏል። በአለማቀፍ መድረክ አግኝቶ የጨበጣቸውን ሁሉ እንደዲፕሎማሲ ድል መቁጠሩ የሚነግረን ነገር ብዙ ነው።

በአለማቀፍ መድረክ ያገኘውን መሪ ሁሉ አብሮ ፎቶ እየተነሳ መለጠፍ፥ የቅቡልነት ድርቀት እንደመታው፣ የዲሲ ቦዘኔዎችን ሰብስቦ ፎቶ ሲነሳ የሚውለው ደመቀ መኮንን የሚመራው የውጭ ግንኙነትም በተለይ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያለው ግንኙነት ከዜሮ በታች የመወረዱና ያንን በፎቶ ፖለቲካ ለመሸፈን የሚደረግ desperation እንዳለ ግልፅ ማሳያ ነው።

ምናልባትም እኔ ይህንን ፅሑፍ እየፃፍሁ ባለሁበት ቅፅበት፥ "ከወንድሜ እገሌ ጋር..." አልያም "ከእህቴ እገሊት ጋር......" ብሎ ከአንዱ ሀገር መሪ ጋር በድንገት የተነሳውን ፎቶ ለጥፎ ቁጥሩን ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

ነገሩ፥ "ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል" ነው።

ዴቭ ዳዊት።




Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 42897
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: "ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል" በአለማቀፍ መድረክ አግኝቶ የጨበጣቸውን ሁሉ እንደ ዲፕሎማሲ ድል መቁጠሩ የሚነግረን ነገር ብዙ ነው።

Post by Horus » 19 Feb 2022, 12:28

sarcasm,
አንተና ዴቭ ዳዊት የምትባሉ ሰዎች በደምብ ያልገባችሁን ተረት አላግባብ በመጠቀም አበላሻችሁት! ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል የሚባለው ተረት ለዚህ አይሰራም። እናንተ እንደ ምትሉት ነው እንበልና አቢይ ይህን ሁሉ ፎቶ የሚለጥፈው ለራሱ ዝና፣ ለመታወቅ፣ ለፓፕሊክ ሪሌሽን ትርፍ ነው እንበል ። ያ ደሞ ሊሆን ይችላል። በጣም ትክክል ነው። ይህ ፓፕሊክ ሪሌዝን ኦፕቲክስ ይባላል፣ የራስን ጉዳይ ፕሮሞት ማድረጊያ የታወቀ ብልሃት ነው ። ይህ ሁሉ ከተረቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ። ተረቱን ካቢይ ፎቶች ጋር ያዛማደው ሰው ያማራኛ ቋንቋ ምሳሌና አግብዎ አያቅም። ይህ ተረት የሚሰራው ለሚከተለው ሁኔታ ነው ። ለዚህ ተረት ተመሳሳዩ ያልዘሩት አይበቅልም የሚለው ነው ። ያም ማለት አንተ አንድ ነገር እንዲደረግልህ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ኤክስፔክት የምታደርግ ከሆነ አንተ እራስህ ተመሳሳይ ዉለታ ወይም መልካምነት ለዚያ ሰው ማድረግ አለብህ ማለት ነው ። ሰውነትህ በጥንካሬ ዳገት እንዲያወጣህ የምትፈልግ ከሆነ ሰውነትክን ተንከባክበህ ጎመን ሳይሆን ክትፎ በቆጮ መመገብ አለብህ ማለት ነው ። ያላደረከው ዉለታ ልታገኝ አትችልም ማለት ነው ። ይህ ምሳሌ አቢይ ያገኘው እድል ተጠቅሞ ፒ አር መስራቱ ጭርሶ ከዚህ አይገናኝም። ለምሳሌ ጥናት ማጥናት የማይወድ ተማሪ ኮሌጅ ልገባ እፈልጋለሁ ሲል ያ ተረት ይተረትበታል። ያልዘሩት አይበቅልም፤ ጎመን ብቻ የሚበላ ጉልበት ዳገት አይወጣም ማለት ነው! ቋንቋ አታበላሹ!!!!

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል" በአለማቀፍ መድረክ አግኝቶ የጨበጣቸውን ሁሉ እንደ ዲፕሎማሲ ድል መቁጠሩ የሚነግረን ነገር ብዙ ነው።

Post by Abere » 19 Feb 2022, 12:44

እኔም የሆረስን ምሳሌዊ አነጋገር እጋራለሁ። አርዕስቱ እና ዝርዝር ጉዳዩ አይመሳሰሉም። ምናልባት በዚህ ቢስተካከል ይረዳ ይሆን።

1- ሰው መሳይ በሸንጎ
ወይም

2- ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ
ወይም

3- የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ

ለማለት የተፈለገው ዐብይ አህመድ አገር ቤት ውስጥ የሰው ቄራ በወለጋ ከፍቶ በአፋር እና አማራ ደግሞ ህዝብ በሽፍታ ሲታረድ ጆሮውን ደግፍኖ፥የወያኔ የበላይ ጠባቂ በመሆን የትግራይን ህዝብ የስቃይ ዘመን በማራዘም በዋናነት ሲታውቅ ፤ በባህር ማዶ ደግሞ አገራቸው ሰላም የህዝብ እንባ የማያፈስ የመልካም አስተዳደር ጣርያ ገንብተው ከሚገኙ መሪዎች ጋር እኩል ፎቶ መነሳቱ ከሆነ።

Post Reply