Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15486
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚከፈል ዋጋ ክብር ነው።

Post by Abere » 09 Feb 2022, 10:08

ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚከፈል ዋጋ ክብር ነው።ከትግራይ ወያኔ ጋር ለድርድር የሚቀመጥ ማንኛውም ኃይል እርሱ እራሱ ጭራቅ ነው። ጭራቅ ከጭራቅ ጋር እንጅ ጭራቅ ከሰብዓዊ ፍጡር ጋር አይዶልትም። የወያኔ ታሪክ ጸረ-ህዝብ እና ጸረ-አገር እንጅ አንድም ቀን በስህተት እንኳን ሰዋዊ ሁኖ አያውቅም። የኢትዮጵያን አገራዊ እና የዜጎች ክብር ለማስጠበቅ የሚደረገው ጦርነት ሞራላዊ ነው። በሃይማኖትም ቅዱስ ነው። ይህ ጦርነት የግድ መቀጠል እና በድል እና በአሸናፊነት ኢትዮጵያዊያን ሊያጠናቅቁት ይገባል - የህልውና ጉዳይ ነው ምዕራባዊያን እና ሃሳዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንደሚሉት ሳይሆን ለኢትዮጵያዊያን ብቸኛ የዘላቂ ነጻነት እና መረጋጋት አማራጭ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ለዚህ ጦርነት የሚሰዋ ህይወት ይሁን የሚጠፋ ሃብት የዜጎች እና የአገር ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የዋለ መዋዕለ ንዋይ ነው። ጦርነትም መዋዕለ ንዋይ ነው - ጦርነቱ ፍትሃዊ ስለሆነ።