Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ (State owned Media)
Feb 7 2022
አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐን ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ አበባ፡- አሸባሪው ሸኔ በጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐንን መግደሉን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። መንግሥት በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ወረዳው ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው ሸኔ ነጻ መውጣቱ ተገልጿል።
የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።
በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል። አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም
Please wait, video is loading...