Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethioscience
Member
Posts: 4102
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

Where is ENDF‘s fake field marshal, as Afar children attacked by Agame terrorist????

Post by ethioscience » 06 Feb 2022, 04:28

አፋር ለምን በትግሬ ወራሪ ተጠቃ?
ጌታቸው ሽፈራው

የሕወሓት የሽብር ቡድን፣ እግሩን ደደቢት ላይ ከተከለ ጀምሮ በዋንኛ ጥላትነት በፈረጀው ዐማራ ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ዐዲስ ነገር ባለመሆኑ ብዙዎችን አያስገርምም። ዛሬ ግን፣ ከዐማራም አልፎ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በከፋ ሁኔታ ሰለባ እያደረገ ነው። በዚህም አፋር፣ የጥቃቱ ገፈት ቀማሽ ሆኖ ከርሟል። በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት መከላከያ ሠራዊቱ ባለበት እንዲቆም ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፤ የትግሬ ወራሪ ቡድን ‹ለሰላም ስል ከአፋር እና ዐማራ ክልል ወጥቻለሁ› እያለ የሀሰት ፕሮፓንዳ በሚነዛበት ወቅት ጭምር፣ አፋር ላይ ተደጋጋሚ ወረራ እየፈጸመ መሆኑ መሬት የረገጠ ሃቅ ነው። ንፁሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ ሳይቀር እየተጨፈጨፉ መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች በግላጭ ያሳያሉ።
ነገሩን ግራ-ገብ ያደረገው ሕወሓት በአንድ እጁ፣ ለበርካታ አገር መንግሥታት "ጦርነቱን አስቁሙልን" እያለ የተማጽኖ ደብዳቤ እየላከ እና በሚዲያ ሰላምን አብዝቶ እየሰበከ፤ በሌላኛው እጁ፣ በርካታ ታጣቂዎቹን ወደ አፋር ክልል ልኮ ወረራና ጭፍጨፋ እየፈጸመ መሆኑ ነው።
እዚህ ጋ፣ ‹አፋር ለምን ተጠቃ?› ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው፡፡
"አፋር እንኳን ተኮሰብን?!"
የወራሪው ቡድን እብሪተኞች ቀድሞም ለአፋር መልካም አመለካከት አንዳልነበራቸው አይካድም። በተለይ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የአፋር ሕዝብ ያለው ስር-ሰደድ አቋም ምቾት አይሰጣቸውም። በድኀረ-83ቱ የሽግግር ወቅት ሱልጣን እንፍሬ አሊሚራ "የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ግመሎቻችንም ያውቁታል፤" ያሉበት ዝነኛ ንግግር፣ ስለ ሰንደቅ ዓላማም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲወሳ ለሚኮሰኩሳቸው የትግራይ ገዥዎች ዐማራን እንደሚወቅሱበት ሁሉ፤ የአፋር ጠንካራ ኢትዮጵያዊነትንም የትምክት አስተሳሰብ አድርገው እስከ መውሰድ መድረሳቸው ይታወቃል።
ነገር ግን፣ ይህንን የአፋር ሕዝብ መሰረታዊ የፖለቲካ ባሕል በሌሎች ጉዳዮች ሸፋፍነው የሚፅናኑበት አላጡም። ኢትዮጵያን ከልቡ የሚወደውን የአፋርን ሕዝብ በዳር አገር "ትምከተኛ"ነት በመፈረጅ፣ ስጋትነቱ እንዲቀንስልቸው ማድረግ ችለው ነበርና። በዚህም፣ ወደ ዋናው የማዕከላዊ መንግሥቱ ሥልጣን ድርሽ እንዳይል አግደው ሲያበቁ፤ ማኀበረሰቡንም ልክ እንደ ሌሎቹ "አርብቶ ዐደር" በሚል ንቃተ-ህሊናውን ሲያጣጥሉ፤ የክልሉን ገዥ ፓርቲ ደግሞ “አጋር ድርጅት” ብለው በመግፋት፣ ‹ኢትዮጵያን መውደድ የትም አይደርስም› ዐይነት ጨዋታ ሲጫወቱ ቆይተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ በማኀበረሰቡ ስም የሚነግዱ ወያኔዎችን በአስተዳዳሪነት እና በአማካሪነት በመመደብ፣ አፋርን ከኢትዮጵያዊ ፍቅሩ ለመነጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። ለዚህም ነው፣ የ“ትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትሕነግ)” ከአራት ኪሎ ሥልጣኑ ሲባረር፣ ክልሉን ሲገዙ የነበሩ የአመራር አባላትም አብረው ከአፋር ወደ መቀሌ ሲሸሹ በብዛት የታዘብ ነው።
የሆነው ሆኖ፣ የትግሬ ወራሪ፣ የአፋርን አገር ጠባቂነት የሚያንኳስሱ ተግባራትን ሲከውን ከመኖሩ ባሻገር፤ ጥሬ ሃብቱንም እየዘረፈ በራሱ ካድሬዎች በማስተዳደር አፋርን መጠቀሚያ አድርጎት መቆየቱ የቅረብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ በርግጥ፣ ይህ ዐይነቱ አካሄድ፣ በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ የተፈፀመ መሆኑ አይዘነጋም። በጥቅሉ ግን፣ አፋር፣ በትግሬ ወራሪ አዕምሮ ውስጥ ያለው ቦታ ሁለት ነው፡፡ አንዱ፣ የአፋርን ድንግል ሃብት መቦጥቦጥ ሲሆን፤ ሁለተኛው፣ ለወደፊቷ የትግራይ ሪፐብሊክ አማራጭ መተላለፊያ ኮሪደር ማድረግ ነው፡፡ ይህ ስግብግብነትም፣ አፋር አገሩን ከማንኛውም አቅጣጫ ከሚሰነዘርባት አደጋ ለማዳን ያለውን ብርቱ አቋም አስረስቶት፣ ለታሪካዊ ስህተት አጋልጦታል።
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የትግሬ ልዩ ኃይል መከላከያ ሠራዊቱን በድንገት ሲያጠቃ፣ ከአፋር ሕዝብ የጠበቀው፡- ቢቻል ይህን ክህደት ደግፎ ከጎኑ እንደሚቆም፤ ካልሆነ ግን ‹በዝምታ እየተመለከተ ያሳልፈኛል› ብሎ ነበር። አፋር ግን፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመውን ክህደት አውግዞ፣ ከኢትዮጵያ ጎን ሲቆም ጊዜ አልፈጀበትም። ይኼኔም፣ ለማኀበረሰቡ ጥልቅ ንቀት የነበረው የሽብር ቡድኑ በሊቀ-መንበሩ ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በኩል በቴሌቪዥን የአፋር ሕዝብን በጅምላ ለመሳደበ አላመነታም። የአገር ሉዓላዊነትን በማስከበሩ ረገድ አኩሪ ታሪክ ያለው ማኀበረሰብ መሆኑንም ረስቶ፣ "አፋር እንኳን ተኮሰብን!" ብሎ ንቀቱን በግልጽ አሳይቷል። ባለፉት ዐመታት በነበረው የእጅ አዙር የትግሬ አገዛዝ አፋርን እንደማይተኩስ፣ ራሱንም አገሩንም እንደማይጠብቅ አድርገው መውሰዳቸው፣ ከጥቅምት 24 በኋላ ስህተት እንደሆነ የተገለጠላቸው ይመስለኛል።
አፋርን ከኢትዮጵያ የመነጠል ሴራ
የሕወሓት ሰዎች በራሳቸው ካድሬ እየገዙ፣ ሃብቱን እየበዘበዙ ጀግንነቱን የረሱት አፋር፣ ኢትዮጵያ ላይ ወረራ ሲፈጽሙ ተቃርኗቸው በመቆሙ፣ በጠላትነት ፈርጀውት ሌላ ስልት መንደፍ ነበረባቸዋል። ይኸውም፣ የአፋር ማኀበረሰብ በኢትዮጵያዊነቱ ተስፋ ቆርጦ፣ ሌላ ማንነት ፍለጋ እንዲቅበዘበዝ ማድረግ የእቀዱ ዋንኛ ጭብጥ ነው። የትግሬ ወራሪ ጫካ በገባበት ወቅት፣ አገር ቤት ካሉ ሁለት አመራሮቹ እና ውጭ ያሉ ወኪሎቹ ጋር በዙም የተወያየበት መረጃ ሾልኮ ወጥቶ በ“ፍትሕ መጽሔት”ም ትንተና ተሠርቶበታል። ይህ ሾልኮ የወጣው የውይይት መረጃ እንደሚያስረዳው፣ በሽብር ቡድኑ ክፋት ከታሰበላቸው የኢትዮጵያ ማኀበረሰቦች አንዱ የአፋር ሕዝብ መሆኑን ነው። አፋር ላይ ግጭቶችን በማስነሳት፣ በሚደርስበት ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ተስፋ ቆርጦ ጅቡቲ እና ኤርትራ ከሚኖሩ አፋሮች ጋር መሆንን እንዲመርጥ እና ከኢትዮጵያ እንዲነጠል መሥራት እንዳለባቸው መወሰናቸውን ያትታል። በዚህም፣ ኢትዮጵያን ለሉዓላዊነቷ የሚቆምላት አንድ ጠንካራ ሕዝብ እንድታጣ ማድረግ እንደሚቻል ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ መደምደሚያቸው ‹አፋር ከኢትዮጵያ ሲነጠል፣ የኖረበትን እሴቱን ማጣቱ የማይቀር ነው› ከሚል የመነጨ ይመስል።
የሕወሓት መሰሪ ፍላጎት፣ በዚህ ሂደት አፋርን ከኢትዮጵያ መነጠል ብቻ ሳይሆን፤ ከኤርትራም ሆነ ከጅቡቲ ሕዝብ ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ የባከነና ሲዋልል የሚኖር እንዲሆን ማድረግንም ይጨምራል። ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ያጣ እና ሌላ ማንነት ፍለጋ የሚከላወት ሕዝብ ደግሞ፣ ስጋት ካለመሆኑ በዘለለ፤ እንዲያውም የትግሬ ወራሪ፡- በኢትዮጵያ ላይ፣ በኤርትራ ላይ፣ በጅቡቲ ላይ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ላይ፣ በኦሮሞ ላይ፣ በዐማራ ላይ… ‹ለማነሳሳት መጠቀሚያ ይሆነኛል› ብሎ አስልቷል። የሽብር ቡድኑ እና አጋዦቹም ይህንን በአፋር ላይ ያቀዱትን ለማሳካት ብዙ ጥረት አድርገዋል። በሕልውና ዘመቻው የአፋር ሕዝብ ያሳየው ጀግንነት ግን ዓላማቸውን የሚያመክን እንጂ፤ የሚያሳካ እንዳልሆነ በበቂ አስተምሯቸዋል።
ስለዚም፣ ስልት ቀይረው አፋርን በቀጥታ ማጥቃት ነበረባቸው፤ አድርገውታልም፤ እያደረጉትም ነው።
"አፋር ላይ ሂሳብ ማወራረድ"
የትግሬ ወራሪ መከላከያ ሠራዊቱን ከመታ በኋላ፣ በተደረገው የመልሶ ማጥቃት ጫካ ሲገባ፣ መሰባሰቢያ ያደረገው በዐማራ እና በኢትዮጵያ ላይ ጥላቻን በስፋት መንዛት ነው። የአፋር ሕዝብም ከዚህ የጥላቻ ቅስቀሳ ነፃ አልነበረም። ልዩነቱ በዐደባባይ ዐማራ ላይ እንዳደረጉት፣ አፋር ላይም በስፋት አለመቀስቀሳቸው ብቻ ነው። ቡድኑ ጫካ እያለ ዋና ዓላማው፣ ዐማራ ላይ ሂሳብ ማወራረድ እንደነበረ በግላጭ ተናግሯል። ከቆላ ተንቤን በ“ተአምር” ወደ መቀሌ ከተመለሰ በኋላም፣ እንደፎከረው ዐማራ ክልልን በመውረር ንፁሃንን ጨፍጭፏል፤ ሀብት ንብረት ዘርፏል፣ አውድሟል፤ ሴቶችን ዕድሜ ሳይመርጥ ደፍሯል። ክልሉንም ሠላሳ ዐመት ወደኋላ ለመለሰ ውድመት ዳርጓል፡፡
ይህንን የጭካኔ ድርጊት በአፋር ሕዝብም ላይ ፈጽሞታል። ‹አፋርን በኃይል በመያዝ የኢትዮጵያን ጉሮሮ አንቄ፣ ብችል እንደ 1983ቱ ዐዲስ የፖለቲካ ሥርዐት አስቀምጣለሁ፤ ይህ ካልሆነ ግን፣ የበላይነቱን ይዤ ለድርድር እቀመጣለሁ› ብሎ ሲንቀሳቀስ፣ የአፋር ፀጥታ ኃይሎች እና ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ተባብረው አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ በገቡ ተሳቢ መኪናዎች ጠቅጥቆ ወደ አፋር የላካቸው ወጣቶችም፣ የአሞራ ራት ሆነው ቀርተዋል። በተደጋጋሚ በሞከረው ወረራ ‹ጠንካራ› ብሎ የለያቸው ተዋጊ ኃይሎቹ ሳይቀር እንዳልነበር ሆነውበታል። በወረራ ከቀያቸው ያፈናቀላቸውን ህፃናት እና ሴቶች የተጠለሉበት የተፈናቃዮች ጣቢያ ላይም ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ከ240 በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል፣ ሴቶቹን ደፍሯል፣ ከተሞችን አውድሟል፡፡ ይህም ሆኖ፣ የአፋር ሕዝብ እና መከላከያ ሠራዊቱ በጀግንነት ተዋግተው ሕልሙን አጨልመውበታል።
ሕወሓት፣ ምንም እንኳ "አፋር እንኳን ተኮሰብን" ብሎ በይፋ የንቀት መግለጫ ከሰጠ በኋላ፣ "ሂሳብ ማወራረድ" እቅድ የነበረው ቢሆንም፤ በዳግም ወረራው የደረሰበት ኪሳራ፣ በአፋር ላይ የበለጠ ጭላቻና ቂም እንዲይዝ አንዳደረገው መረዳቱ አያዳግትም። ለዚህም ነው፣ በአንድ በኩል፣ ‹ከአፋር እና ዐማራ ክልል ሠራዊቴን አውጥቻለሁ› እያለ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ፤ በሌላ በኩል፣ እንደገና አፋር ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ የከፈተው። የዚህ ወረራ ዓላማ አፋር ላይ ሂሳብ በማወራረድ፣ ማኀበረሰቡን መስበርና አንገት ማስደፋት ነው። ራሳቸው የትግሬ ወራሪ ወታደራዊ አመራሮች እና ፖለቲከኞች፣ “የወረራው ዓላማ ልካቸውን መስጠት ነው፣ አርፈው እንዲቀመጡ ማድረግ ነው፣ ከአሁን በኋላ እንዳይወሩን ማድረግ ነው…" እያሉ በይፋ እየተናገሩ እንደሆነም ልብ ይሏል።
በዚህ ላይ፣ የሽብር ቡድኑ፣ አፋር ላይ ክፉ እቅድ ሲቀምር ቆይቶ፣ ለተግባራዊነቱ ሰበብ ፍለጋ የተለያዩ ስሁት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥቷል። አንዴ "አርፈው ካልተቀመጡ እናሳያቸዋለን"፤ ሌላ ጊዜ "የአፋር ሽማግሌዎች ያሳርፉልን" እያለ ሂሳብ ማወራረድ ለሚለው የቂም በቀል ዓላማው ሲያመቻቻቸው ከርሟል። የአፋር ሽማግሌዎችም የትግሬ ወራሪ ላወጣቸው የሽንገላ "ያሳርፉልን" መግለጫዎች፣ "እየጨፈጨፋችሁን ያላችሁት እናንተ ናችሁ" ብለው መልስ መስጠታቸው ይታወቃል። መግለጫና ልምምጡ የሀሰት እንደነበረ የሚያስረግጠው ደግሞ፣ የትግሬ ወራሪ በዚህ ጥቃት፡- ህፃናትን፣ እናቶችን እና አዛውንቶችን ዋንኛ ሰለባ ማድረጉን ስንመለከት ነው።
አፋር፣ ለምን ተጠቃ?
የትግሬ ወራሪ ቀደም ሲል አፋርን አንደ ጓሮ አትክልቱ ሲያየው መቆየቱ ይታወሳል። ጨውን ጨምሮ፣ የተለያዩ ማዕድኖቹን አፍሶ ወደ መቀሌ ከወሰደ በኋላ፣ እዛው አቀነባብሮ ሚሊዮኖችን ያተርፍበት እንደነበረም አይዘነጋም። አዋሽ የሚያለማውን መሬት ለራሱ ባለሃብት ሰጥቶ እና የኮንትሮባንድ ንግዱን ተቆጣጥሮ አለቅጥ ከብሮበታል።
"ለውጥ" ከተባለ በኋላ ደግሞ አፋር፣ እንደ ሶማሌ ክልል ሁሉ፣ ከሕወሓት ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር ከማመወጣቱ ባሻገር፤ ኢትዮጵያን ለማጥቃት በቀላሉ የማያልፈው ቀጠና መሆኑ ከንፈር አስነክሶበታል። በመጀመሪያው ዙር ወረራ ማይካድራ እና አካባቢው ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የፈፀመው የትግሬ ወራሪ፤ በሁለተኛው ወረራ መተላለፊያ ለማድረግ ‹አያዋጣኝም› በሚል የኢትዮ-ጅቡቲን መንገድ ለመዝጋት እና ወደ አዲስ አበባም ለማለፍ ለወረራ የመረጠው አፋርን ነው። ወረራው በተጠናከረበት ወቅት፣ መገንዘብ እንደተቻለው ‹ጅቡቲ ያለው የአሜሪካ ጦር በኢትዮጵያ ጣልቃ ይገባል› ብሎ ተስፋ አድርጎ የነበረ መሆኑን ነው።
በመጀመሪያው ወረራ አመራሮችን ወደ ጅቢቲ ለማስመለጥ፤ እንዲሁም በሁለተኛው ወረራ ጅቡቲ የነበሩ አመራሮቹን እና ታጣቂዎቹን ወደ አገር ቤት ለማስገባትም ጥረት አድርጓል። በርግጥ፣ ከአፋር ጆግራፊ አኳያ ለእነዚህ ዓላማዎቹ አፋርን መውረር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ማመኑ ስህተት አልነበረም። በሌላ በኩል፣ መከላከያ ሠራዊቱን ከተጠቃበት ጊዜ አንስቶ፣ አፋር ክልል የፀጥታ ኃይሉን ማጠናከር ጀምሯል። በዚህ ላይ፣ በሁለተኛው ዙር የትግሬ ወራሪን መትቶ በመለሰበት ጦርነት ተፈትኖ የበለጠ መጠንክሩ ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ፣ በሽብር ቡድኑ ዘንድ የአፋር ጥንካሬ፣ ‹በቀጣይ ትግራይ እንደፈለገች የምትወጣበትና የምትገባበት ጓሮዋ መሆኑን ያስቀራል› በሚል ስጋት፣ አፋርን አጥቅቶ ማዳከም እንደ ዋነኛ ስልት እንዲያዝ አድርጓል። በድብቅ ስብሰባው በተጋለጠው መረጃም፣ አፋርን ከኢትዮጵያ መነጠል ባይቻል እንኳ፣ ለኢትዮጵያም ለራሱም የማይቆም አድርጎ ለማዳከም ተደጋጋሚ ጥቃት ለመፈፀም ማቀዱ በጉልህ ሰፍሯል።
ታሪካዊው የአፋር ሕዝብ ጠላት
ቀደም ሲል የትግሬ ወራሪ ዐማራ ላይ ሲያደርገው እንደነበረው፣ በስፋት አይናገረው እንጂ፤ የአፋርን ኢትዮጵያዊ አቋም በትምክተኝነት የሚፈርጀውና የሚጠላው መሆኑ ይታወቃል። በርግጥ፣ ተገንጣይነት እና የአፋር ኢትዮጵያዊነት ከድሮም ሁለት የተለያየ አቅጣጫ ላይ የተቀመጡ ተቀራኒ የፖለቲካ አስተሳሰብ ዐምዶች መሆናቸው እውነት ነው። ሕወሓት ወደ ሥልጣን ሲመጣ እና ኢትዮጵያን የባሕር በር ሲያሳጣ፣ አፋርንም ከቆየ ታሪኩና ከፍታው ለማውረድ ጥረት አድርጓል። ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅትም፣ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አፋርን ሃብቱን በመመዝበር፣ ከመሃል ፖለቲካ በማራቅ፣ በሞግዚት በማስተዳደር ከአርብቶ ዐደርነት ያለውጣ እና የመሳሰሉት ስያሜዎች በመስጠት ወደኋላ ለማስቀረት ብዙ አሴሯል።
"ለውጥ" ከተባለ በኋላ ደግሞ፣ በስሙ እየማሉ መቀሌ ተቀምጠው ግጭት የሚጠምቁ ቡድኖች ከተቋቋመባቸው ክልሎች መካከል አፋር አንዱ ነው። በዚህ በትግራይ ኢኮኖሚ ራሱን መመገብ በማይችልበት እና ሌሎች ተገንጣዮችን በቀጥታ ማገዝ ባልቻለበት እንኳ፣ ትግራይ ውስጥ ሆነው መግለጫ የሚሰጡ አፋርኛ ተናጋሪ ወያኔዎች እንደነበሩ ታዝበናል።
ከዚህ ባሻገር፣ ትሕነግ ‹ተቃዋሚ› ብሎ ያደራጃቸው የትግሬ ጽንፈኛ ቡድኖች የአፋር ግዛት ላይ ‹የይገባኛል ጥያቄ› በተደጋጋሚ በማቅረብ፣ በክልሉ የግዛት አንድነት ላይ አደጋ እንዲደቅኑ ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎም፣ በሰሞኑ ወረራ "ከቀይ ባሕር አፋሮች ጋር ሆነው ወጉኝ፣ የኤርትራ ሠራዊት ጋር ሆነው አጠቁኝ…" እያለ እንደ ሕዝብ ፈርጆ፣ "ሂሳብ አወራርዳለሁ" የሚል በቀለኝነቱን ቀጥሏል። በዚህም፣ በስደተኛ ካምፖች፣ በመስጊዶች… ወዘተ ላይ ከፈፀመው ጭፍጨፋ በተጨማሪ፤ እናቶችን፣ ህፃናትን እና አዛውንቶችን በከባድ መሳሪያ በማጥቃት ላይ ነው።
የትግሬ ወራሪ አመራሮች በየሚዲያው ስለ ድርድር በሚያወሩበት በዚህ ወቅት፣ በአፋር ክልል ኪልበቲ ዞን በንፁሃኖች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ የክልሉ መንግሥት ‹የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው› ሲል መግለፁ ይታወቃል። ይህ የሽብር ቡድን በአፋር ላይ የከፈተውን ሌላ ዙር ወረራና ጭፍጨፋ ተቃውመው ሰልፍ የወጡት የአፋር ክልል ነዋሪዎችም የትግሬ ወራሪን "ታሪካዊ የአፋር ሕዝብ ጠላት ነው" የሚሉ መፈክሮችን አንግበው በዐደባባይ ሲያወግዙ ሰንብተዋል። በርግጥም፣ የትግሬ ወራሪ ከአፋር ጋር ያለው የአስተሳሰብ ልዩነት፣ በአፋር ሕዝብ ላይ ያቀደው ዓላማ እና ሲፈጽመው የኖረው ወንጀልና ደባ፣ የአፋር ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

(የቀጠለ……)

ይሁንና፣ የሽብር ቡድኑ፣ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ በዘመተበት ወቅት መከታ የሆነውን የአፋር ሕዝብ እንደገና ነጥሎ ሲያጠቃ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚገባውን ትኩረት እየሰጡት አለመሆኑ ግርታን ፈጥሮብኛል፡፡ ከዚህ አኳያም፣ ሁሉም አገር ወዳድ ሕዝብ ዓይኑንም ጆሮውንም አፋር ላይ አድርጎ፣ ወራሪውን ቡድን ለመደምሰስ በመረባረብ ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።


(ፅሁፉ በትናንት የፍትሕ መፅሔት ላይ የታተመ ነው)