Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለው የዲፕሎማሲ መንገድ 'የማጭበርበር መንገድ ነው'" ዶ/ር ኣብይ አህመድ

Post by sarcasm » 11 Jan 2022, 20:59

ዶር ኣብይ አህመድና የዲፕሎማሲ መንገዱ

በጥቅምት ወር 2013ዓ/ም ምናልባትም ከትግራይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ አስር ቀን ቀደም ብሎ ኣብይ ኣሕመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለው የዲፕሎማሲ መንገድ "የማጭበርበር መንገድ ነው፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ህጎችና ስምምነቶችም ገሚሰቹ በግላጭ እያወቀን እንጥሳቸዋለን፣ ገሚሶቹ ደሞ እያወቅን ግን ደሞ ለዓለም ማሕበረሰብ እንዳላወቅን በማስመሰል እየጣስን የሀገራችን ልማት እናፋጥናለን፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ አመራር ይህን መገንዘብና መተግበር ግድ ይለዋል" ብሎን ነበር።

ስለዚህ ዶር ኣብይ ኣሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት መመራት ያለበት በማጭበርበር ነው ብሎ የሚያምን መሪ ነው። በሰኔ ወር ከመቐለ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ቶጎጋ የተባለችው የገጠር ቀበሌ ከተማ በኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ የሰማዕታት ቀን ሆን ተብሎ ከደበደበ በሗላ፣ የሰራውን ወንጀል ለመከላከልና አጀንዳ ለማስቀየር የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባላት የትግራይ ሀይሎች ሲቪልያንን ገደሉ ብለን መግለጫ እንድንስጥ ከፌደራል መንጎስት ትዕዛዝ ወርዶ ነበር። ይህንን መግለጫ እንደማናወጣና ይልቁንስ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ሲቨላያንን ጨፈጨፈ ብለን ነው የምናወጣው ብለን ስለሞጎትንና በጉዳዩ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ስለተፈጠረ የፌደራል መንግስት ከኣዲስ ኣበባ በራሱ በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ስም "የትግራይ መከላኪያ ሀይሎች የጊዝያዊ አስተዳደር አመራሮች ገደሉ" ብሎ መግለጫ አወጣ።

በሰኔ ወር የኢትዮጵያ መከላኪያ ሃይልና የኤርትራ ሰራዊት በቅንጅት ዶር ደብረፅዮንንና ጌታቸው ረዳን በእጅ ይዘን እናስመጣለን ብሎ በቆላ ተምቤን ቁጥር ስፍር የሌለው የፈሰሰው ሰራዊት ከ 11 ሰኔ 2013ዓ/ም እስከ 21 ሰኔ 2013 ዓ/ም በትግራይ መከላኪያ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ። በዚህ የተናደደው መከላኪያ ሀይልም መላ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር አመራሮችን በአክሱም ሆቴል ውስጥ እንድንቆይና እንዳንቀሳቀስ ትዕዛዝ ከተሰጠን በሗላ፣ መጨረሻ ስዓት ላይ የፌደራል መንግስቱ ታማኝ ያላቸውን አመራሮች በአውሮፕላን አስወጥቶ እኛን ለመግደል አሴረ። ሁኖም በጊዝየው እኔ ጉዳዩን ስለነቃሁበት በራሳችን መንገድ የዕዝ ሰንሰለቱ ጥሰን ወደ ዓፋር በመኪና ወጣን። የአብዓላ ቁልቁለት እየወረድን ሳለ እንደተለመደው የፌደራል መንግስት "የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት አውጃለሁ" ብሎ ሲናገር እኛም እንደ ማነኛው የኢትዮጵያ ዜጋ በመኪናችን ውስጥ፣ በአስቸጋሪው የመንገድ ጉዞ ሁነን ሰማን። ከትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር በጉንበት ወር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የጠየቅነው ጥያቄ በጊዜው በከፍተኛ ቁጣና ዘለፋ ውድቅ እንደተደረገ ግን መላው የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ ያውቋል።

በወርሀ መጋቢት፣ሚያዝያና ጉንበት ለአውሮፓ ህብረትና ኣሜሪካ እንዲሁም ሌሎች ዲፕሎማቶች በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት ወንጀል እየተፈፀመ ስለሆነ እንዲያቁመትና፣ በተስፋፊው የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚልሻና ፋኖ እንዲሁም በኤርትራ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ፣ በትግራይ ለተፈጠረው ሰፊ ማህበራዊ ቀውስና ርሃብ መፍትሔ እንዲያበጁ ጠይቄያቸው ነበረ። ምላሻቸው በጎ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ይሄ ነው የሚባል እርምጃ ሳይወስዱ፣ 5.2 ሚልዮን ህዝባችን በከፋ ችጋር ውስጥ ገብቶ፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ ህፃናትና ሴቶች በርሀብ አለንጋ እየተቀጡ፣ ከሁለት ሚልዮን ህዝባችን ከቀየውና ቤቱ ተፈናቅሎ በመንገድና በበረሃ ወድቆ፣ ለሰባት ወራት ያለ ደሞዝ፣ መብራት፣ ስልክ፣ የባንክ አገልግሎትና መድሓኒት አቅርቦት እየተሰቃየ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከተመሰረቱበት ዓላማና ራዕይ በተቀራኒ ቁሞ የበይ ተመልካች ሁኖ ሰንብቷል። ይህንን ጉዳይ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረትና ኣሜሪካ በአስቸኳይ ተጨባጭ እርምጃ ካልወሰዱ በትግራይ የዘር ማፅዳት ወንጀል ከሚጠየቁት አካላት በግምባር ቀደም የሚቀመጡት ይሆናል።

ከአንድ ወር በፊት የትግራይ መከላኪያ ሀይሎች አዲስ ኣበባ ደጃፍ ደብረብርሃን ላይ ሲደርሱ፣ ጅቡቲ የሚገኘው የኣሜሪካ ወታሃደራዊ ሀይል አዛዥ ጀነራል ዊልያም ዛና " ቀዳሚ ዓላማችን በምስራቅ ኣፍሪካ ለሚፈጠረው ቀውስ ወታሃደራዊ ምላሽ መስጠት ነው" ሲሉ ተደመጡ።

ለገባው ሰው የትግራይ መከላኪያ ሀይል ቀፋፊውና ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ለመጣል ከተንቀሳቀሰ ከላዩ ላይ እሳት አዘንባለሁ ዓይነት መግለጫ ነው። ትናንት በሶማልያው ፕረዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስተር ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በደቂቃዎች ውስጥ "ወታሀደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል" ሲሉም ተደምጧል። ለማነኛውም ብቻውን የቆሞው የትግራይ ህዝብና መከላኪያ ሀይል ይሀ ነው የሚባል ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሳያገኝ አንድ ዓመት ኣልፎታል። በማጭበርበር ዲፕሎማሲ የሚያመልከው ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስትና አጋሮቹም፣ በግልባጭ የትግራይ መከላኪያ ሀይል የኣሜሪካ መንግስት ተላላኪ በማስመሰል ሲሱሉት እያየን ነው። ጅቡቲ የተቀመጠው የኣሜሪካ ወታሀደራዊ ሀይልም በመጥፋት አፋፍ ላይ ያለውን የትግራይ ህዝብ የሰብአዊ እርዳታ ኮሪደሮች ማስከፈት አቅቶት ቁሞ ሲያይ እየተመለከትን ነው። የኤርትራ ወታሀደሮችም የትግራይ ዳር ደንበር ጥሶ በመግባት በሺዎች የሚቆጠሩት ሴቶች፣ መንኩሴዎች፣ አረጋውያንና ልጃገረዶች ሲደፍሩ ተጨባጭ መረጃዎች በእጁ ይዞ ቁሞ እየተመለከተ ነው።

እውነታን በገባን ልክ እንደምንተነትን የሚታወቅ ነው ፡፡እውነታው ግን የምንቀይረው አይሆንም፡፡አብይ አህመውድ በአለም አቀፍ ግንኙነት እርያ ሆነዋል ፡፡ አለም የሚጠየፈው መሪ ሆናዋል ማለት ነው፡፡የአብይ ነብስ ትላንት መስኩ አይበቃኝም ብላ እዩኝ እይኝ ስትል ከርማ ዛሬ ደብቁኝ ደብቁኝ እያለች ነው፡፡ አብይ ከእንግዲህ በመንደሩ የሚፎክር ኢሳያስ አፈወርቂ ሆነዋል ፡፡ በሌላ አነጋገር አብይ አህመድ በራሱ ፈቃድ የመንደር ሽማግሌ ለመሆን መርጠዋል ፡፡ትላንት የሸለመችው ዓለም ዛሬ እሱን ለማየት የምትጠየፍ መሆንዋን ቢገባኝም ተጨባጭ እርምጃ በአስተዳደሩ ለመውሰድ ስትቸገር ግን እያየን ነው፡፡ አብይ በስልጣን የሚቆይባቸው አመታት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ዕዳ ሆኖ ይቀጥላል ፡፡ኣብይ በስልጣን እስከቆየ ድረስ አገራችን የተነጠለችና ድሀ አገር ትሆናለች፡፡

የውጭው ግንኙነት የተወሰኑት የአለም ሀገራት የተስማማባቸው ወጎች ና እሴቶችን ማክበር ይጠበቅብሃል ፡፡ አለም ጨዋ መሆንን ይጠይቃል ፡፡ ጨዋነት አንዴ ከወረደ ተመልሶ አይመጣም ፡፡ ችግሩ የአገር መሪ በአለም ሲዋረድ አገርም የሚያዋርድ መሆኑ ነው፡፡ ተወደደም ተጠላም አብይ በሰራው ወንጀል ከአለም ተገልለዋል ፡፡ የጨዋነት አቅሙ ተሟጠዋል፡፡ አለም እሱን ትጠየፋለች ፡፡ አፍሪካዊያንም ቢሆኑ አብይን ይጠየፍታል ፡፡ ከውጭ ዓለም የተገለለ መሪ ለአገራችን የሚያስከትለው ጣጣ ለመተንበይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ጎረቤት አገራትን ማየት ነው ፡፡ ቢያንስ ንአምን ዘለቀ የተባለው የባንዳ ርዥራዥ ልጅ የሚያቆለጳጵሳት ኤርትራን ማየት በቂ ነው፡፡

አብይ በትግራይ የዘር ማፅዳት ወረራ ከፈፀመ ወዲህ እየተነጠለ መጥተዋል ፡፡የፖለቲካ ልዩነት በጦሩነት ለመፍታት የሄደበት የተሳሳተ ኣካሄድ ቀድሞም ቢሆን የተወደደ አልነበረም ፡፡ ኣብይ ጦርነቱ ሲጀምር በአጠረ ግዜ ጨርሶ እጁ ታጥቦ ከደሙ ን ፁህ ነኝ ለማለት ነበር፡፡ ነገር ግን ራሱ በቀሰቀሰው ዘረኝት ወታደሮቹና ግብረ አበሮቹ በትግራይ መንደሮች ተሰምቶ የማያታወቅ የዘር ማፅዳት ግፍ ፈፀሙ፡፡ ይባስ ብሎ ቂመኛው ኢሳያስን ጋብዞ በትግራይ ህዝብ ላይ ተነግሮ የማያልቅ ወንጀል ተፈፀመ፡፡ ባሩድ የሸተተው ጎሮቤት የኣማራ ሽፍታም እንደነጋበት ጅብ ሃብትና መሬት ለመቀራመት ዘሎ ገባ ፡፡ ሁሉም በወንጀል ውስጥ ገብቶ ተነከሩ፡፡

አብይ የረሳው ነገር የፖለቲካ ወንጀል ከፈፀመ መሪ መነካካት የሚፈልግ አገር የሌለ መሆኑ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ህግ መንግስታት ዜጎቻቸውን የመግደል መብት የላቸውም ፡፡ ልእላዊነት መብት የማክበር እንጂ የመግደል መብት አያጎናፅፍም ፡፡ አብይ የሰራው ወንጀል በሁሉም ሰው መንገድ ላይ የቆመ ጋሬጣ ነው ፡፡እንቅፋት ነው፡፡ አሁን ሁሉም ወገን በስሜት ውስጥ በመሆኑ ይህን የሚያስብበት ወቅት አይደለም፡፡ ስለ ነገ የሚያስብበት ወቅት አይደለም፡፡ ነገን ግን መሸሸ አይቻልም፡፡

አብይ አህመድ በአጭር ግዜ ውስጥ የተሰጠውን ፀጋ፣ ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያላት ሀገር ይዞ፣ ዓለም የተጠየፈውን ኢሳያስ ኣፍወርቂ እግር ሂዶ የወደቀ፣ የባከነ አሳዛኝ መሪ ነው ፡፡ አለም ጨካኝ ናት ፡፡ የትላንት ከንቱ ውዳሴና ሽልማት ለማስታወስ አትገደደም፡፡ ለዚሁ ቦታ የላትም፡፡ ችግሩ በሰራው ወንጀል የመከሰስ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡እሱ የማይቀር የህግ ጉዳይ ነው፡፡ ወንጀል ስትሰራ ከአለም ትገለላለህ፡፡ ዲሞክራሲያዊ አለም ኣብይን ለመቀበል ፍቃደኛ አይሆኑም ፡፡ ከእንግዲህ አውሮፓ መሄድ የለም፡፡ መሪዎች ካልቸገራቸው በስተቀር ወንጀል የሰራ መሪን ከመጨበጥ ይሸሻሉ፡፡ወንጀል ማጠብ አይቻልም ፡፡ አብይ የመንደር መሪ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል ፡፡ የውጭ የፍይናንስ እርዳታ ፤ኢንቨስትመንት ይቀራል፡፡ ፈጣን ልማት የሚባለው ወሬ ብቻ ይሆናል፡፡ አገሪቱ የስራ አጥ መናሓርያ ትሆናለች፡፡ የአገር ካፒታልም ይሸሻል፡፡በአገር ውስጥም ቢሆን ውስጣዊ ዲሞክራሲያዊ ትብብር በአብይ ዘመን ሊከሰት አይችልም፡፡

እንዲህ ያሉ መሪዎች የህዝብን የችጋር ዘመን ያራዝማሉ፡፡የኢሳያስ አፈወረቂን ማየት ይበቃል ፡፡ ኢሳያስ ከመንደሩ ወጥቶ ቁም ነገር አይሰራም፡፡ ከአለም የተገለለ መሪ ነው፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀመ መሪ በአውሮጳና አሜሪካ ጎደናዎች ሊንሸራሸር አይችልም፡፡ ብራስልስ ፤ዋሽንግተንና ጄኔቭ መሄድ ኣይቻልም፡፡ ወደ ተጠቀሱት አገሮች የሚሄዱት እሱን የሸሹ ኤርትራዊያን ብቻ ይሆናሉ ፡፡
የከሸፈው የማጭበርበር ዲሎማሲ ስልት፣

ሰሙኑን ኢትዮጵያ ከአገዋ (AGOA) መሰረዝዋን ሰምተናል ፡፡የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሙሸንም (UNHRC) በአገራችን የተሰራው የሰብአዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ ወስነዋል፡፡ ሁለቱም ብቻ ብንወስድ የአብይ መንግስት የዲፕሎማሲ ሚዛን ምን ያሕል እንዳዘቀዘቀ መገምገም እንችላለን፡፡ቀደም ሲልም የአውሮጳ ሕብረት የሚሰጠው የፍይናንስ ድጋፍም ተሰርዘዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግንኝነት የጦር መሳርያ ከሚሸጡ በሰብአዊና ዲሞክራሲ የሚታሙና የተገለሉ አገራት ብቻ እየሆነ ነው፡፡ከቱሩክ፤ ከኢራን ፤ከሩሱያ ሊገኝ የሚችል ጦር መሳርያ ብቻ ነው ፡፡ ቱሩኮች አህመድ ግራኝን በጦር መሳርይ የረድ ወገኖች ናቸው፡፡ ሩሱያ ደርግን ስትረደ ነበር ፡፡ እኒህ አገራት የሚታወቁት በአሉታዊ ጎኑ ነው፡፡ስለዚህ አገራችን ከእነዚህ ጋር በመዛመድ ማደግ ትችላለች የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡በልመና ይቀናኛል ሲለን የነበረው አ ብይ ከአረብ በሻንጣ ሊረጠብ ይችል እነደሆነ እንጂ ለህዝብ የሚጠቅም ሊገኝ አይችልም፡፡

ከአገዋ መወገድ ያለው ትርጉም ማወቁ ተገቢ ነው ፡፡ከአገዋ መገለል የ100,000ሺ ሰራተኞች ስራ አደጋ ይወድቃል፡፡በ100 ሚልዮን የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ኣይገኝም ፡፡ መንግስት ዲያስፖራ እንዲገቡለት የሚማጠነው ገንዘብ ፍለጋ ነው፡፡ የአሜሪካን ገበያ ትኩረት አድርገው ኢንቬስት ያደረጉ ቻይናዊያን ወደ ሌላ አገር ይሰደዳሉ፡፡ቻይናዊያን የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሌላት አገር መቆየት አይፈልጉም፡፡ቻይና ስለ እኛ ብላ የምትሰራው ተጨማሪ ነገር ይኖራል ብሎ መጠበቅ የዋሕነት ነው፡፡
በአንድ ጉዳይ መስማማት ያለብን ጉዳይ ቢኖር አብይ ከአራት ኪሎ ጎትቶ የሚያወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ አለም አብይን የመጎተት ሃላፊነት የላትም፡፡ ግንኙነቱ ግን ተበላሽቷል፡፡አገር ለማዳን ከሰውየው መገላገል ነው ፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይና መከራ እየተራዘመ ያለው። ኣሜሪካ የትግራይም ኣብይ የሚመራት የኢትዮጵያም ደጋፊ አይደለችም። ሁኖም የትግራይ መከላኪያ ሀይል ከደብረብርሃን በመመለሷ የትግራይም የኢትዮጵያም ህዝብ ስቃይና መከራ አራዝማለች።

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሙሽን የአብይ ወንጀል በአለም አቀፍ ነፃ አጣሪ ቡድን እንዲጣራ መወሰኑ አብይ አሕመድ ምን ያህል እንደተገለለ ማሳያ ነው፡፡ መጀመርያ በአጀንዳ ያስያዙት ያደጉና የበለፀጉ የአውሮጰ አገራትና አሜሪካ ነበሩ፡፡ ከአብይ ጎን የቆሙት ሩስያና የተወሰኑ አፍሪካ አገራት ናቸው፡፡ውሳኔው በአብይ ሰፈር ድብ ዕዳ ነው፡፡ በመዶሻ መወቀጥ ነው፡፡ የአብይ መንግስት ገና አጀንዳው ተይዘዋል ሲባል በመግለጫ ጋጋታ ያደነቆረን ትልቅ ስጋት ስለፈጠረበት ነው፡፡ ውጤቱ በመተንበይ ብፍርሃት ተውጠዋል፡፡ የፈሰሰው የትግራይ ደም ድምፅ አውጥቶ እየጨሆ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ነፃ እርምጃ አይቻልም፡፡ ሰው ገድለህ በሰላም መኖር እንዳማይቻል አሳይተዋል የአብይ የማጭበርበር የዲፕሎማሲ መንገድም መክኗል።

ችግሩ አብይ በስልጣን እስከቀጠለ ድረስ የአገራችን መገለል የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ ነገ ወንጀለኞች ለፍርድ አሳልፍቹህ ስጡ ወደ ሚለው ሲደረስ ዛሬ ሚድያን ያስቸገሩ ጄኔራሎች የሚደበቁበት ቀን ሩቅ አይደለም ፡፡ በሰሩት ወንጀል ነገ ለአለም አቀፍ ፍርድቤት ተይዘው ይቀርባሉ፡፡

በመጨረሻም ለዚሁ ሁሉ ያደረሰን “ፍቅር ያሸንፍል” በሚል መፈክር ተሸፍኖ የመጣን ቡድን ለማስወገድ የዐለም ሀገራትና ተቋማት እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቆመጥ ማንሳት ያስፈልጋል። ይህንን ባታደርጉ ግን እኔ የምነግራቹ በግልፅ ቋንቋ ነው፣

ትግራይ ብቻዋን ሀገር ብቻ ሳትሆን አህጉር ጭምር ናት፣ ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ግን ሀገር ሳትሆን መንደር ናት!

ድል ለሰፊው ህዝብ!
20 ታህሳስ 2014 ዓ/ም






Please wait, video is loading...